>
5:33 pm - Thursday December 5, 6295

በወለጋ የተጨፈጨፉትን ለማሰብ በተጠራ  የሀዘን ቀን ይልቃል  አጣዬን ጨምሮ ሰሜን ሸዋን በማስጨፍጨፍ ላይ ነው!!! * ()ወንድወሰን ተክሉ)*

በወለጋ የተጨፈጨፉትን ለማሰብ በተጠራ  የሀዘን ቀን ይልቃል  አጣዬን ጨምሮ ሰሜን ሸዋን በማስጨፍጨፍ ላይ ነው!!!

* ወንድወሰን ተክሉ*

በወለጋ በሁለት ሳምንት እድሜ ውስጥ የተጨፈጨፉትን ከ4ሺህ በላይ አማራዊያንን እልቂት ለመዘከር ታስቦ በተጠራው ሀገር አቀፍ የሀዘን ቀን ባሕርዳር ላይ ተጎልቶ የአማራ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ነኝ የሚለን ይልቃል ከፋለ አጣዬን ጨምሮ አጠቃላይ ሰሜን ሸዋን በማስጨፍጨፍ ለጌታው የኦሮሙማው ኦህዴድ መራሹ ብልጽግና ቡድን እንደገጸበረከትነት አቅርቧል።

በሰሜን ሸዋ አጣዬና አካባቢው ከትናንት ጀምሮ እየሆነ ያለው ነገር – አገኘሁ ተሻገር ከዓመት በፊት አጣዬ ከተማን ባስወደመበት ስልትና ውሳኔ ይልቃል ከፋለ በአካባቢው ተጠናክረውና ተደራጅተው ያሉትን የሰሜን ሸዋ

ኋይል እያደነ ያሰረውን ካሰረ የገደለውንም ከገደለ በኋላና አካባቢውን ካጸዳ በኋላ እሱ ከሚገዛው አማራ ክልል በተነሱ ታጣቂዎች ከትናት ጀምሮ እስከዛሬዋ እለት ድረስ ከፍተኛ ጭፍጨፋና ውድመት እየተካሄደ ነው።

ለይስሙላ ያህል በአካባቢው ያሰማራውን የአማራ ልዩ ኋይል በመከላከያው በስተጀርባ በማስደብደብና የተቀረውን ደግሞ ዲሺቃ ካሊበርና መሰል ከባድ የቡድን መሳሪያን በገፍ በታጠቀው ታጣቂ ቡድን ያለርህራሄ አስቀጥቅጦ የልጆቻችንን እሬሳ በየጢሻውና በየመንገዱ ለጅብና ለአሞራ ሲሳይ ሰጥቶት ይገኛል።

ይህ የሰሜን ሸዋ ወረራና ጭፍጨፋ በአማራ ክልላዊ መንግስት ስር ያለ ቀጠና እንደመሆኑ መጠን እና ጨፍጫፊዎቹም እንደ ወለጋው በኦነግ ሸኔ ስም የሚጠሩ ሳይሆን እዚያው አማራ ክልል ውስጥ ባለው የኦሮሚያ ዞን ውስጥ ተደራጅተው ሰልጥነውና ታጥቀው የመጡ የአማራ ክልል ኦሮሚኛ ተናጋሪ ታጣቂዎች በመሆናቸው ለዚህ የጭፍጨፋና የወረራ ዘመቻቸው ሁኔታውን አመቻችቶ በማዘጋጀት የፈቀደላቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት ነኝ ባዩ ይልቃል ከፋለና እሱ የሚመራው ካብኔት ናቸው።

ሁላችሁም የጭፍጨፋውን መጠን እና ይዘት ትረዱት ዘንድ ወታደራዊ ስልጠና ወስዶና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ታጥቆ የተሰማራን ከመቶ በላይ  የአማራ ልዩ ኋይል አባላት የተገደሉበት የጭፍጨፋና የወረራ ዘመቻ – ምንም ያልታጠቁ ንጹሃን ነዋሪዎች ምን ያህል ሊጨፈጨፉ እንደሚችሉ መገመት ይቻላችኋልና  ይልቃል ከፋለ በሕዝባሽችን ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃትና ጉዳት እጅግ ከባድ ነው።

ለምሳሌ ያህል-  በአጣየ ከተማ ስር በምትገኘውና አርሶ አምባ በምትባል ስፍራ  ውስጥ ያሉት አምስት ቀበሌዎች በሙሉ  ሙሉ በሙሉ  መውደማቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

የይልቃል ከፋለ አለቆች አቢይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ በወለጋ ላይ መጠነ ሰፊ የጭፍጨፋ ዘመቻ ባካሄዱበት ሁኔታ በግዛቴ ውስጥ ያለውን ክፍል ደግሞ እኔ ላጽዳላችሁ በማለት ይልቃል ከፋለና ግብረዓበሮቹ ሰሜን ሸዋን እያስጨፈጨፉ ይገኛሉ።

ማንም አማራ በዚህ በሰሜን ሸዋ ወረራዊ ጭፍጨፋ ጣቱን በሽመልስ አብዲሳ ላይ ከመቀሰር ጭፍጨፋው እየተካሄደበት ያለበትን ግዛትና አካባቢን በፕሬዚዳንትነት እየመራሁ ነው የሚለን ይልቃል ከፋለ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ መሆኑን ነው መረዳት የሚገባን።

በወለጋና በኦሮሚያ ሽመልስ አብዲሳ (የኦሮሚያ ብልጽግና ኦህዴድ-ብልጽግና ) በሰሜን ሸዋ ይልቃል ከፋለ (የአማራ ብልጽግና ብአዴን-ብልጽግና) እየተፈራረቁና እየተቀባበሉ አማራውን እየጨፈጨፉት ሲሆን ይህም ጭፍጨፋ ጨፍጫፊዎቹና አስጨፍጫፊዎቹ በስልጣን ላይ እስካሉ ድረስ በመጠኑና በይዘቱ ይበልጥ እየጨመረ የሚሄድ እንጅ ፈጽሞ የማይቆም መሆኑን እያንዳንዱ አማራ ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል።

የአማራን ጭፍጨፋ ለማስቆም መላው አማራ በነፍጥ በጥይት በትጥቅ በአመጽና በሁሉም ዓይነት የመታገያ መንገድና ስልት ተጠቅሞ በጨፍጫፊዎቹና አስጨፍጫፊዎች ኦህዴድ-ብአዴን መራሹ የብልጽግና ፋሺስታዊ ስርዓትን ታግሎ ከተቀመጡበት መንግስታዊ በትረስልጣን ካልመነገላቸው በስተቀር የአማራ መጨፍጨፍ ይዘቱና መጠኑ እየጨመረ የሚሄድ ነው።

ይህንን ዓይነቱን ትግል ለማካሄድ ደግሞ ብቸኛውና በእጃችን ያለው ፋኖነትና ፋኖአዊ አደረጄጀት ብቻ ነው!!!

• ጋሻ መልቲ ሚዲያ

Filed in: Amharic