>
5:01 pm - Thursday December 3, 6601

የቄስ ሞገሴ ነገር... !!! (አቻምየለህ ታሪኩ)

የቄስ ሞገሴ ነገር… !!!

አቻምየለህ ታሪኩ

ቄስ ሞገሴው ብርሀኑ ነጋ ከልሳኑ ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ የመንግሥትና የብል[ጽ]ግና መዋቅር አለመየቱ በምርጫ ተብዮው እንዲሸነፉ እንዳደረጋቸው ተናግሯል። የመንግሥትና የብልጽግና ፓርቲ አለመለየቱ በምርጫው እንዲሸነፉ እንዳደረጋቸው ያሳያል ያለውን ባለ40 ገጽ ጽሑፍ ማዘጋጀቱንና ይህንን የኢዜማ ግምገማም መንግሥት ተብዮው ጭምር እንዲያውቅ እንዳደረገ ነግሮናል።

የመንግሥትና የፓርቲ መዋቅር አለመለያየቱን ለኢዜማ ሽንፈት ምክንያት እንደሆነ የነገረን ብርሀኑ ነጋ ለመሸነፋችሁ ዋናው ምክንያት ተቃዋሚ ፓርቲ ሆናችሁ ሳለ ከምትታገሉት ገዢ ፓርቲ ጋር አብራችሁ በመስራታችሁና እናንተንና ገዢውን ፓርቲ በመምረጥ መካከል ልዩነት ባለመኖሩ የተነሳ ነው ያልተመረጣችኹት የሚሉ ሰዎች አሉ ተብሎ ሲጠየቅ  ግን “እኛ የምንሰራው ከመንግሥት ጋር እንጂ የብል[ጽ]ግና ፓርቲ ጋር አይደለም” ሲል አዘጋጀነው ያለውን ባለ 40 ገጽ ግምገማ ባፍጢሙ የሚደፋ ተቃራኒ መልስ ሰጥቷል።

ልብ በሉ! “እኛ የምንሰራው ከመንግሥት ጋር እንጂ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር አይደለም” የሚለን ብርሀኑ ነጋ ነው 180 ዲግሪ ተከርብቶ በምርጫ የተሸነፍኹት የመንግሥትና የፓርቲ መዋቅር ባለመለየቱ ነው የሚለን። አበው ድሮ «ቀጣፊን ሲረቱ፣ በወንድሙ በእህቱ» ይሉ ነበር። ዘንድሮ ግን  «ቀጣፊን ሲረቱ በራሱ በአንደበቱ»  ሆኗል። ቀጣፊን ሁሉ እንዲህ እንደብርሀኑ ነጋ የራሱ አንደበት ያደናቅፈዋል።

Filed in: Amharic