>

የጋሽ ታዴዎስ ታንቱ ዋስትና ታገደ (ጌጥዬ ያለው)

የጋሽ ታዴዎስ ታንቱ ዋስትና ታገደ

 

ጌጥዬ ያለው

ሐቀኛው ጋዜጠኛና የታሪክ ጸሐፊ ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ በ15 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የሰጠው ብይን በጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ታግዷል። በዋስትናው ጉዳይ አከራክሮ ብይን ለመስጠት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ለፊታችን ሐሙስ ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ለጧት 3 ሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። በተመሳሳይ በእዚያው ዕለት የእስር ፍርድ ቤቱም መዝገቡን ለመመልከት ሌላ ቀጠሮ ይዟል።

ከሳሽ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ በመጠየቁ ነው ክርክሩ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሄደው። ከሰኔ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ አዛዎንቱ ጋዜጠኛ ያለ አንዳች የሕግ አግባብ በፖሊስ እምቢተኝነት ብቻ ታስረው መቆየታቸውን ጠበቃቸው አዲሱ ጌታነህ ተናግረዋል።

Filed in: Amharic