>

በክስ ላይ ክስ እየተደራረበበት ያለው  ተመስገን ደሳለኝ   (ታሪኩ ደሳለኝ) 

በክስ ላይ ክስ እየተደራረበበት ያለው  ተመስገን ደሳለኝ  

ታሪኩ ደሳለኝ 

↘️ በመጀመሪያ ጋዜጠኛ ተመስገን ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት በዩትዩቦች ይጠቀማል አለ፤

+ ሲደመር

↘️ ከአስር ቀን ቀጠሮ በኋላ በዩትዩብ ሳይሆን በፍትሕ መፅሔት ይጠቀማል አለ፤

+ ሲደመር

↘️ ፍርድ ቤቱ ይሄን ተከትሎ በዋስ እንዲወጣ ወሰነ፤

+ ሲደመር

↘️ይሄን ተከትሎ የፖሊስ መርማሪዎችና አቃቤ  ህጎች ይግባኝ ብለው ወንጀሉ ውስብስብና ሌሎች አባሬዎች አሉ አለ፤

+ ሲደመር

↘️ፍርድ ቤቱም ሰኔ 2/2014 በዋለው ችሎት ደግሞ ፖሊስ 8 ቀን ወስዷ ምርምሮ ለሰኔ 10/2014  በድጋሚ ያቅርባቸው ብሎ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ወሰነ::

+ (ሲደመር)

↘️ የሰኔ 10/2014 ቀጥሮ ቀርቶ ለሰኔ 7/2014 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳልኝ ከ5 ቀናት በኋላ ፍርድ ቤት ቀርቦ አቃቤ ህጎቹም የተመስገን ፁሁፍ ወታደራዊ ሚስጥሯች ፅፏል:: ፁሁፍን ተከትሎ ሞትም ተከስቶ ሊሆን ይችላል የሚል አዲስ ክስ አምጥተዋል::

+ ሲደመር

የዛሬን ሰኔ 22/2014 ዓ.ም  ክስ አዋልደዋል::

ሦስት የተለያዩ ክሶችን አነባብረው አዋልደዋል::

#ክሶቹም

1ኛ. በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 44(1) (2) እና 336(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ፤ 2ኛ. በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 44(1) (2) እና 337(1) ፤ 3ኛ. በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 44 (1) 2) እና 257 (ሠ) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ፡፡

ወንጀል ክስ የቀረበበት ሲሆን ፤ አጠቃላይ ክሶቹ ” ምስጢራዊ ወታደራዊ መረጃዎችን በማውጣት ፣ የሐሰት ወይም የሚያደናግራ ወታደራዊ መረጃ በማውጣት እንዲሁም ህዝብ ያለውን አቋም የሚያፈርስ መረጃ በተከታታይ እትሞች ለህዝብ እንዲሰራጭ በማድረጉ በፈፀመው መገፋፋት እና ግዙፍ ያልሆነ ማሰናዳት ተግባር ወንጀል ተከሷል” የሚል ነው።

( መንግስት ከ33 ቀን በኋላ ለተመስገን “የመከላከያ ሰራዊትን ሚስጥር በማውጣት” የሚል አዲስ ክስ አዋልደ)

ፍርድ ቤቱም አዲሱን ክስ ሰምቶ በዋስትናው ላይ ብይን ለመስጠት ለአርብ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓም ቀጠሮ ሰጠ::

↘️  ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ   ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቢገኝም ዳኛ የለም በመባሎ ለሰኞ ሰኔ 27/2014 ዓ.ም ከሰዓት 9 ሰዓት ተቀጥረ::

↘️  ሰኔ 27/2014 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፍርድ ቤት ቀርቧ #በ100 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ  1ኛ ፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች የፌደራል ከፍተኞው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል።

(በእለቱም 27/2014 1ኛ ፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ  በ100 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ መሰኑን ተከትሎ ለዋስትን የተጠየቀውን ብር ተይዞ የመፈቻ ወረቀቱን ተሞልቶ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (ሦስተኛ)  የተመስገንን ፍቺ የሚያስፈፅም አካል የለም በማለት ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን  ሳይፈታው አሳደረው)

↘️  ሰኔ28/2014ዓ.ም ፖሊስ ጋዜጠኛን ተመስገን ደሳለኝን ባለመፎታቲ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ቀረበ

( የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፍርድ ቤት ትዕዛዝን በመተላለፍ ጋዜጠኛ ተመስገንን አልፈታም ስላለ  “የተከበረው ፍርድ ቤት በ27/10/2014 ዓ.ም የሰጠውን ትዕዛዝ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በኩል ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲደርሰው እና የክፍሉ ኃላፊ ኮሚሽነር ጸጋዬ ባልቻ ተገደው ቀርበው እንደመፍቻው ትዕዛዝ መሰረት ያልፈጸመበትን ምክንያት እንዲያስረዱ እንዲታዘዝልኝ”  ተጠየቀ::  ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ ትእዛዝ ለመስጠት ለሰኔ  29/10/2014 ዓ.ም ጠዋት ቀጠሮ ሰጠ።

↘️  ሰኔ 29/2014 የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሃላፊዎች የሉም በማለት የፍርድ ቤት ትዕዛዝን አልፈፅምም በማለት ጋዜጠኛ ተመስገንን በሕገወጥ መንገድ አስሮ ይዞ የሚገልፀውን አቤቱታውን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፀረ ሽብር ጉዳዮች ችሎት ፤የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮምሽነር ሀሰን አርጋው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲፈጽሙ ፤ ወይም ያልፈፀሙበት ምክንያት ካለ ቀርበው እንዲያስረዱ፤ ለነገ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ቀጠሮ ሰጠ።

↘️  ሰኔ 30/2014 የአበባ ፖሊስ ኮምሽን  ሀላፊ  የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ፀረ ሽብር ችሎት ቀርበው  የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን የዋስትናው ብይን በፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የታገደ ስለሆነ ሊፈፅም እንደማይችል ተናገሩ።

የልደታው ችሎቱም ያልተፈታበትን ይሄን የጠቅላይ ፍ/ቤት ምክንያት ተቀብሎ አሰናበተ።

በዚህ መሠረት ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዋስትና ሊፈታ አይገባም ክርክር ላይ ይግባኙን ለማድመጥ ለሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ቀጠሮ ሰቷል።

↘️  የዛሬውን ቀጠሮ ደግሞ እንጠብቃለን ……….

Filed in: Amharic