>

አሸባሪው አገዛዝ ይሄንን የሙስና አጀንዳ የወረወረበት ምክንያትና ዓላማ!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

አሸባሪው አገዛዝ ይሄንን የሙስና አጀንዳ የወረወረበት ምክንያትና ዓላማ!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው


አሸባሪው አገዛዝ ይሄንን የሙስና አጀንዳ አሁን ያመጣበት ምክንያትና ዓላማ ሦስት ነው፦

1ኛውና ዋነኛው እንደምታውቁት አሸባሪው አገዛዝ ባለው የአማራን ዘር የማጥፋት ዓላማና ግብ ወገኖቻችንን በየስፍራው በአረመኔያዊ ግፍ ከጨፈጨፈና የተረፉትንም ካፈናቀለ በኋላ ለተፈናቀሉት ወገኖቻችን አስፈላጊውን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት አያደርግም፡፡ የማያደርግበት ምክንያት ደግሞ ግልጽ ነው፡፡ ተፈናቃይ ወገኖቻችንን ስቃይ ላይ በመጣል በረሃብና በሕመም ለመፍጀት ነው፡፡ አገዛዙ አሁን ይሄንን ሰውየ የጦስ ዶሮ በማድረግ ይዘርፍ የነበረ አድርጎ ያመጣው “ከጭፍጨፋ ለተረፉ ወይም ላመለጡ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ተገቢው እርዳታ የማይደረገው ለምንድን ነው???” ለሚለው የሕዝብ ጥያቄ “ለተፈናቃዮች ተገቢው እርዳታ የማይደርሰው ለእነሱ ሊደርስ የሚገባውን እርዳታ ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ከግብረአበሮቹ ጋር ሆኖ እየዘረፈው ስለነበረ ነው!” ለማለት ነው!!!

አገዛዙ ግን ላፈናቀላቸው ወገኖቻችን እንኳንና ከራሱ እጅ እርዳታ ሊያደርግ ይቅርና ከወገን ወይም ከሕዝብ ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የተሰበሰበውን የዓይነት እርዳታዎች እንኳ በካድሬዎቹ እየዘረፈና በመጋዘን በእሳት እያቃጠለ በማውደም ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን እንዳይደስር ሲያደርግ እንደቆየ የምታውቁትና የአደባባይ ምሥጢር ነው!!!

2ኛው ምክንያትና ዓላማ ደግሞ የሲሪላንካ ሕዝብ በሙሰኛ መንግሥታቸው ላይ በወሰደው እርምጃ የተመሰጠው ሕዝባችን “እኔም በዚህ አሸባሪና ሙሰኛ አገዛዝ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ ልውሰድ!” እንዳይል በሙስና ላይ የዘመተ መስሎ በመታየት የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ለመሥራት ወይም ሕዝብን ለማታለል ነው!!!

3ኛ. አጀንዳ ለማስቀየስ ወይም ሕዝቡ ትኩረቱን በአረመኔያዊ ግፍ አገዛዙ ከጨፈጨፋቸውና ካፈናቀላቸው ወገኖቻችን ላይ እንዲያነሣ ለማድረግ ወይም ለማስቀየስ ነው!!!

ለማየት ያብቃቹህ አገዛዙ አጀንዳው ግቡን ከመታለት በኋላ ቆይቶ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ የቆየ ሲያስመስል ይቆይና “ኤልሻዳይ የተባለው ድርጅት ኮሚሽነሩን በሙስና ለማጥመድ በማሰብ ኮሚሽነሩ በማያውቁት ሁኔታ በእናታቸው፣ በባለቤታቸውና በልጆቻቸው ስም የመኖሪያ ቤቶችን ገዝቶ ለማማለል ሞከረ እንጅ የተከበሩ ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ ምንም የሚያውቁት ነገር አልነበረም!” ብሎ ወይም ሌላ ተመሳሳይ ምክንያት በመስጠት ሰውየውን ነጻ ይለቀዋል!!!

እንጅ በወያኔ/ኢሕአዴግ ሥርዓት ውስጥማ ሙስና መሥራት እኮ ግዴታ ነው እንጅ ውዴታ አይደለም እኮ፡፡ ከዐሥር ዓመታት በፊት ይሄንን ጉዳይ በዝርዝር ጽፌላቹህ ነበር፡፡ አገዛዙ የሚሾማቸውን ግለሰቦች በሙስና እንዲነከሩ የሚያደርግበት ምክንያት በሕዝብ የተጠላ ከመሆኑ የተነሣ የሚቀርበው ስለሌለ በዚህ በሙስና ጥቅም በማማለል አገልጋይ ለማግኘት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሚሾማቸውን ግለሰቦች በሙስና ማኖ ካስነካና የወንጀል ሪከርድ ከያዘባቸው በኋላ በዚያ እያስፈራራ ዘለዓለማቸውን እሱን ሲያገለግሉት እንዲኖሩ ለማድረግ መሆኑን በዝርዝር ጽፌላቹህ ነበር!!!

እናም ሙስናማ ለአገዛዙ የወጥመድ መሣሪያውና የግዴታ ተግባሩ ነው እንጅ ወንጀል ባለመሆኑና ከሥርዓቱ ባለሥልጣናት ከዚህ ነጻ የሆነ አንድ እንኳ ሰው የሌለ በመሆኑ በምንም ተአምር ቢሆን አገዛዙ በሙስና ላይ ሊዘምት አይችልምና በማይመስል ነገር አትጃጃሉ!!!

አቶ መለስ ዜናዊ “እስካልተያዙ ድረስ ስርቆትም ሥራ ነው!” ማለቱን አታስታውሱም እንዴ??? አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ በሆኑበት ሥርዓት ማን ነው ማንን “ሰርቀሃል!” ብሎ የሚይዘው??? ስለሆነም ሥርዓቱ እራሱ ሙስና ነው በሙስና ላይ ሊዘምት አይችልም!!! ሌባን ሌባ ሊወነጅለውና ሊከሰው አይችልምና!!!

Filed in: Amharic