>

ታዴዎስ ታንቱ በቀጠሯቸው መሰረት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ - ፍርድ ቤቱ ጌጥዬ ያለውን በተገኘበት እንዲታሰር አዝዟል።

ታዴዎስ ታንቱ በቀጠሯቸው መሰረት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ

-ፍርድ ቤቱ ጌጥዬ ያለውን በተገኘበት አዝዟል

-ተመስገን ደሳለኝ ለሐምሌ 13 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል

 ኢትዮ ሪፈረንስ

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ባለፈው ችሎት በሰጠው ቀጠሮ መሰረት የእነ ጋዜጠኛ ታዴዎስ ታንቱን መዝገብ ለማከራከር ዛሬ ሐሙስ ሀምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ተሰይሟል። ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ እና ጠበቃቸው አዲሱ ጌታነህ በችሎት የተገኙ ሲሆን ፖሊስ አዛወንቱን ጋዜጠኛ ጋሽ ታዴዎስ ታንትቱን ሳያቀርባቸው ቀርቷል። የፊታችን ሀምሌ 20 ቀን እንዲቀርቡም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረው ታዴዎስ ታንቱ የክስ መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ እና ፖሊስ 2ኛ ተከሳሽ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለውን አስሮ እንዲያቀርብ ነበር። ሆኖም በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተከናወነ ያለው የይግባኝ ክርክር ብይን ባለማግኘቱ የክስ መቃወሚያውን ማስቀረት አልተቻለም።

ጋሽ ታዴዎስ በዋስትና ከእስር እንዳይፈቱ ዐቃቤ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ በመቃወም የጋሽ ታዴዎስ ጠበቃ አዲሱ ጌታነህ ዝርዝር ማብራሪያ በፅሁፍ ለፍርድ ቤቱ አስገብተዋል። በቀጣዮቹ ቀናት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ብያኔ ይጠበቃል።

በእነ ታዴዎስ ታንቱ መዝገብ ሁለተኛ ተከሳሽን ፖሊስ በመኖሪያ አድራሻው ፈልጎ እንዳጣው ለእስር ፍርድ ቤቱ አስረድቷል። በቀጣዩ ቀጠሮ ጌጥዬ ያለውን በተገኘበት ይዞ እንዲያቀርብም ፍርድ ቤቱ አዝዟል።

በተያያዘ ዜና በጋዜጠኛ  ተመስገን ደሳለኝ ዋስትና የዋስትና ክርክር ላይ ብይን ለመስጠት የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ችሎቱ የይግባኝ ክርክሩን አዳምጧል።

Filed in: Amharic