>

የቴዎድሮስ ካሳሁን / ቴዲ አፍሮ / የምስጋናና የውግዘት መልእክት....!!!

የቴዎድሮስ ካሳሁን / ቴዲ አፍሮ / የምስጋናና የውግዘት መልእክት….!!!

የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም በየዓመቱ ሐምሌ 7 ቀን የሚውለውን የልደት በዓሌን በማስመልከት ላለፉት ረዥም ዓመታት በኢትዮጵያ ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በመገኘት ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት ለመታደግ ደም በመለገሰ ሰብአዊ ተግባር ለምትፈፅሙ የልብ አድናቂዎቼና ወዳጆቼ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናዬን እያቀረብኩ፤ በዘንድሮው ደም የመለገስ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት ባልተገባ ሁኔታ ለገጠማችሁ መጉላላት የተሰማኝን ኅዘን ስገልፅ ይህን ፍፁም ሰብአዊ ሕይወት የማዳን መርሐ ግብር በተገቢው ሁኔታ እንዳይከናወን ክልከላ ያደረጉ መንግሥታዊ አካላትን በጥብቅ በማውገዝ ነው።

በተጨማሪም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት መልካም ምኞታችሁን በተለያየ መንገድ ለገለፃችሁልኝ ክቡራን ወገኖቼ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ።

ፍቅር ያሸንፋል

ቴዎድሮስ ካሣሁን ( ቴዲ አፍሮ)

Filed in: Amharic