>

ዘመን የማያጠፋው ፋኖነት - ህብረቱ ፣ እምነቱ እና እውነቱ (ጌንመ ዘብሔረ አዲስ አበባ)

ዘመን የማያጠፋው ፋኖነት – ህብረቱ ፣ እምነቱ እና እውነቱ

 

ጌንመ ዘብሔረ አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ አንፀባራቂ ታሪክ ከተከናወነባቸው በርካታ ክንውኖች አንዱ የፋኖ አርበኛ ልጆቿ የአምስቱ ዓመት የአልገዛም
ባይነት የአርበኝነት ተጋድሎ ታሪካቸው ነው፡፡ ይህን እልህ አስጨራሽ ትግል እና ጣሊያንን ድል የማድረጉ ሚስጥር
ከቀደሙት አባቶቻቸው የአድዋ እና መሰል ድሎች የተወረሰ ለመሆኑ አሌ የማይባል ሀቅ ነው፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያ
በጣም ከምትታወቅበት ነገሮች አንዱ ክብሯን እና ታሪኳን ከእንዱ ትውልድ ወደ ሚቀጥለው ትውልድ በቅብብሎሽ
ማስቀጠል መቻሏ ነው፡፡
ይህ የአምስቱ ዓመት የአርበኝነት ተጋድሎና ድል ዝም ብሎ በፀሎትና በልመና የመጣ አልነበረም ፤ በብዙ መስዋዕትነት
፣ ህይወት ፣ አካል ፣ ትውልድ እና ዘመን ተገብሮበት የተገኘ እንጂ፡፡
ለምሳሌ ጣሊያን ለወረራ ጦርነቱን ስትጀምር ወደ ጦር ግንባራት ይዛው የገባችውን የጊዜውን ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች
ከኢትዮጵያዊያን አርበኞች ከያዟቸው መሳሪያዎች ጋር በጥቂቱ ብናነፃፅር እንኳን፡-
‹‹ በጣሊያን በኩል የነበሩ የጦር መሳሪያዎች
360,000 ወታደር ፣ 3 ሚሊዮን ቶን የሚመዝን የጦር መሳሪያ ፣ 30,000 የጭነት እንስሳት ፣
65,000 መኪናና ሞተር ባይስክል፣ 50,000 መንገድ ሰሪዎች፤
ጀነራል ደቦኖ መረብን ተሻግሮ ወረራውን ሲጀምር በውጊያው ላይ ያሠለፈው ኃይል፡-
510,000 ወታደር ፣ 500 የጦር አውሮፕላኖች ፣ 782,320 ጠመንጃዎች ፣ 23,251 መትረየሶች ፣
2,608 መድፎች ፣ 2,000 ታንኮች ፣ 1,289,416,100 ጥይቶች ›› [1] ሲሆን
‹‹ በኢትዮጵያ በኩል የነበሩ የጦር መሳሪያዎች
725,000 ሰራዊት (25,000 ብቻ የሰለጠነ) ፣ 400,000 ጠመንጃዎች ፣ 3,500 መትረየሶች ፣
200 መድፎች ( ለአንድ መድፍ 500 ጥይቶች ) ፣ 7 ታንኮች (ያለ ጥይት) ፣ 15 አብራሪ የሌላቸው
አውሮፕላኖች (ከ8 ወር ነዳጅ ፍጆታ ጋር ) ፣ 40,000,000 ጥይቶች እና 50 ከባድና ቀላል ፀረ-አውሮፕላን
(ኦሪስኮን መትረየስ) ››ነበር፡፡
ጣሊያን እነዚህን ሁሉ መሳሪያዎችን ይዛ በተጨማሪም ለሆዳቸው፣ ለገንዘብ እና ለሥልጣን ያደሩ ብዙ ሺህ ባንዳዎችን
አሰልፋ ኢትዮጵያን ለአምስት ዓመታት ብትወርም እንኳን እንደ ሌሎቹ አቻ የአውሮፓ ሀገራት ቅኝ መግዛት ሳትችል
በጀግኖች አርበኞች ድል ተመታ አንገቷን ደፍታ ወጥታለች፡፡ ይህ ለጥቁር ህዝቦችም ጭምር አኩሪ ታሪክ ሆኖ
የተመዘገበው ድላችን ዝም ብሎ በወኔ ብቻ የመጣ አይደለም ይልቁንስ አርበኞች ከጠላት ይመጡ የነበረውን የመለያየት
ተንኮል ቀድሞ በመረዳትና ተንኮሉን በመበጣጠስ፣ በአንድነት፣ በህብረት፣ በመተጋገዝ፣ በጋራ በመቆም፣ በፍቅር
በመተሳሰብ፣ እና ለኢትዮጵያ ባላቸው ጥልቅ ፍቅር የተነሳ ለመሆኑ በርካታ የሀገርም ይሁኑ የውጪ መፅሐፍት ከትበውት
ይገኛል፡፡

ምንም እንኳን የጣሊያን ፋሺስታዊ መንግስት በባንዳዎች እየታገዘ የቁርጥ ቀን ልጆቿን በዘር (በብሔር)፣ በአካባቢ፣
በሀይማኖት ከፋፍሎ ህብረታቸውን ለመናድ ብዙ ርቀት ቢጓዝም እንኳን አርቆ አስተዋይ ነበሩት አርበኞች ብሔር፣ ዘር፣
ሀይማኖት ሳይለያቸው በህብረት እና በጋራ በመተጋገዝ በአንድነት መቆማቸው ለወራሪው የራስ ምታት ነበር፡፡
ይህ በጋራ መቆም እና መናበብ መቻላቸው ትልቁ ጥቅም አርበኞች ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላኛዉ የሀገሪቱ ክፍል በነፃነት እና
በእምነት ለመንቀሳቀስ ከማስቻሉም ባሻገር ጠላት ላይ ጥቃት ለመፈፀም ፣ ስንቅ እና ትጥቅ እንደልባቸው
ለማዘዋወር ብሎም የጠላት ሀይል ሲያመዝን አፈግፍጎ መሸሸጊያ
ስፍራ ማግኘት መቻላቸው ነበር፡፡ ስለዚህም ለፋሺስታዊ የጣሊያን መንግስት እንደዚህ ዓይነቱን ከቦታ ወደ ቦታ
የመዘዋወር እንቅስቃሴ ሊቆጣጠሩት እና ሊመክቱት ያልቻሉት ከባድ ጉዳይ ከመሆኑም ባሻገር ለውድቀታቸው መሰረታዊ
ጉዳይ እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ሰንደውት ይገኛል፡፡
ለማስረጃ
“ባላንባራስ (ራስ) አበበ አረጋይ (አባ ገስጥ) ከመንዝ ወደ ሰላሌ-ጃርሶ ጉዞ ላይ እንዳሉ ውልጮ ላይ ደርሰው ስለ
ግንደብረት (በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በምዕራብ ሸዋ የምትገኝ ከተማ ናት) አገሬውን ሲጠይቁ ባላንባራስ ዐያሌው
ጓንጉል የሚባል ቀድሞ የደጃዝማች አቻሜለህ ጭፍራ የነበረ ባንዳ በጣሊላኖች ተሸሞ ሕዝቡን እያስገደደ የጦር መሳሪያ
በመግፈፍ ላይ እንደ ሆነ ተነገራቸው፡፡ ህዝቡም እርሱን (ዐያሌውን ) ተዋግተው እንዲያባርርላቸው መጠየቃቸውን
ገለጹላቸው፡፡ ባላንባራስ አበበ አረጋይ በቀረበው የአገሬው ጥያቄ ላይ አቻ የአርበኛው ሰራዊት መሪዎች ጋር መክረው
"ይህንን በህዝብ ላይ የወደቀ ከባድ ሸክም ማስወገድ ይገባል" በሚል ውሳኔ ላይ ደርሰው ተንቀሳቀሱ፡፡ ሰኔ
15/1929 ዓ.ም. ቀን ወደ ግንደብረት ተጉዘው ሙገር የተባለውን ወንዝ ተሸግረው ሰፈሩ፡፡” [2]
“እነ ሻለቃ መስፍን በተሰለፉበት ግንባር በግራ በኩል በጫካ ውስጥ እያሸመቀ ሌላ ጦር ስለመጣ አባ ገስጥ ቦታ ይዘው
ተፋለሙት፡፡ ሻለቃ መስፍንም ባላንባራስ ዐያሌውን ተኩሰው በደረቱ ለቀቁበት፤ የጌታቸውን ሬሳ ለማንሳት ሲግተለተሉ
200 የሚሆኑትን የአርበኞች ጥይት እራት ሆኑ፡፡ የአርበኛ ሠራዊት ጉዞውን ቀጥሎ በማግስቱ ካቺሴ ከተማ ደርሶ
ከተማይቱን እና ዙሪያውን ተቆጣጠረ፡፡ በቃሬዛ የመጣው የባንዳው አለቃ ዐያሌው አስከሬን ካቺሴ ከተማ መሀል
ተሰቀለ፡፡” [3]
“አብርሃም ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም የካቲት 12/1929 ዓ.ም. በአ/አ ገነተ-ልዑል ቤ/መንግስት በአዶልፍ
ግራዚያኒ ላይ ቦንብ ጥለው በከባዱ ካቆሰሉት በኋላ ፋኖ ሞገስ አስገዶም ቀጥታ የሄደው ወደ ባላንባራስ አበበ አረጋይ
ወዳሉበት መንዝ ሲሆን አብርሃም ደቦጭ ደግሞ በደብረ ሊባኖስ አድርጎ ወደ ባላንባራስ አበበ አረጋይ ወዳሉበት መንዝ
በመሄድ ከጓደኛው ሞገስ አስገዶም ጋር ተገናኝቷል፡፡”[4]
“በሰኔ 29/1929 ዓ.ም. ጠላት በቅምቧት በደጀን በገበያ በሸበል በረንታ የነበረውን "ደንበኛ " በሙሉ
አከተተው፡፡ (ደንበኛ የሚባለው "የመንግስት" የደንብ ብረት የያዘ ነፍጠኛ ነው) ቀኛዝማች ስማ ነገዎ አዝማች ሆኖ
ይህን ሁሉ አስከትቶ አባይ ወረደና አባራ ጂወርጊስ ሰፈረ፡፡ ሀሳቡ እነ በላይ ዘለቀ ወደ ጫቀታ እንዳይሻረጉ በር በሩን
ለመዝጋት ነበር፡፡ ምን ዋጋ አለው እነ በላይ ዘለቀ ቀኛዝማች ስማ ነገዎ ያደረበትን ባለበት ከበቡት፡፡ ሲነጋም ስማ
ነገዎን ከነወንድሞቹ ደመሰሱት፡፡ ” [5]
የበረሃዉ መብረቅ ጀግናው አርበኛው ጀነራል ጃገማ ኬሎ በስራቸው ከነበሩት 6 ሺህ ተዋጊ ሰራዊት ውስጥ ከኤርትራ፣
ከትግራይ፣ ከአማራ አካባቢዎች የመጡ ነበሩ፡፡ የበረሃዉ መብረቅ ከሸዋ እስከ ጅማ፣ ጎጃም፣ ወለጋ፣ አ/አ

በመዝመት "ጃገማን ጥሩት " እየተባሉ በርካታ ምሽግ ሰብረዋል፡፡ ከእነ ደጃዛማች ገረሱ ዱኪ እና ወ/ሮ ሸዋ-ረገድ
ገድሌ ጋር በመሆን የኢትዮጵያን አርበኞች እስከ መጨረሻው መርተው ጣሊያንን ከምድሪቱ ጠራርገው
አስወጥተዋል፡፡[6]
ከላይ በጥቂቱ ለመጥቀስ የተሞከሩት ታሪኮቻችን የሚያሳዩን ቀደምት እናት እና አባት አርበኞች ምን ያህል ከአንድ
ክፍለሀገር ወደ ሌላ ክፍለሀገር ሳይሰለቹ እየተዘዋወሩ በጋራ በመተጋገዝ ጠላት ጣሊያንን ብቻ ሣይሆን ለጣሊያን ያደሩ
ባንዳዎችንም ጭምር ምን ያህል ለነፃነታቸው ይታገሉ እንደነበር ብሎም የድሎቻቸው ሚስጥር እንደነበሩ ዋቢ
ምስክሮቻችን ናቸው፡፡

ወራሪው እና ፋሺስቱ ጣሊያን ተሸንፎ አንገቱን ደፍቶ ከኢትዮጵያ ምድር ከወጣ ከ50 ዓመት በኋላ የጣሊያን አሽከር
የባንዳዎች ልጆች ስብስብ የሆኑት ወያኔዎች በነጮች እና በአረቦች እርዳታ፣ በአሻጥር እና በተንኮል በ1983 ዓ.ም
መንበረ ሥልጣኑን እንደያዙ የመጀመሪያ ሥራ ያደረጉት የባንዳ አባቶቻቸዉ ጌቶች (ጣሊያኖች) ያቃታቸዉን የከፋፍለህ
ግዛ ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግ ነበር፡፡ በዚሁም መሰረት በዋነኝነት ኦነግ የተባለዉን ለኦሮሞ ነፃነት እታገላለሁ የሚልን
ድርጅትን እና እራሱ የፈበረካቸዉን የፖለቲካ ድርጅቶችን በመያዝ አዲስ ሕገ-መንግስት አቋቋመ፡፡ በረቀቀዉም ሕገ-
መንግስት መሰረት 14 ክልሎች ተዋቀሩ፡፡ ክልሎችም ራሳቸዉን በራሳቸዉ እንዲያስተዳድሩ፣ በማንኛዉም ሁኔታ
ክልሎች ለክልሉ ዜጋ ብቻ በሚመስል መልኩ እንዲዋቀር ተደረገ፡፡ ስለዚህም ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ከክልል ክልል
ተንቀሳቅሶ መስራትም ይሁን መኖር በክልሎች ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ብቻ ሆነ፡፡ ማዕከላዊው መንግስቱ ዜጎችን
በክልላቸዉ ብቻ ገደባቸዉ፤ ከአንዱ ክልል ያለ ማህበረሰብ ሌላ ክልል ያለን ኢትዮጵያዊ ወገኑን እርዳታ ቢሻ እንኳን ያለ
ማዕከላዊው መንግስቱ ይሁንታ እንዳይችል ሆነ፡፡ በዚህም ምክንያት ክልሎች ህዝቦቻቸዉ ከሌሎች ክልል
ወንድሞቻቸዉ ጋር ህብረት እንዳይኖራቸዉ ተደርገዉ በተናጠል በነበረዉ አፋኝ መንግስት ሲረገጡ እና ሲሰቃዩ ኖሩ፡፡
ከ2007 ዓ.ም. በፊት በሁሉም ክልሎች በወያኔ ኢህአዲግ መንግስት ላይ ብሶቶች ቢኖሩም ትግላቸዉ ግን ዉስጥ
ዉስጡን በተናጠል ስለነበረ በፋሺስታዊዉ መንግስት በቀላሉ እና ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ትግላቸዉን ያኮላሸዉ እና
ያመክነዉ ነበር ( ምርጫ 1997 ልብ ይልዋል)፡፡
ከ2007 ዓ.ም. በኋላ ግን የህዝቡ የትግል ስልት ቅርፁ በመቀየሩ እና ህዝቦች በጋራ በመናበብ (የኦሮማራ ጥምረት
ልብ ይልዋል) በኦሮሚያ ቄሮ፣ በአማራ ፋኖ፣ በደቡብ (በጉራጌ ዘርማ በሲዳማ ኤጄቶ)፣ በአፋር፣ በሱማሌ እና
በሁሉም ክልሎች ወጣቶች እየተናበቡ ባካሄዱት ዋጋ ያስከፈለ ትግል በ2010ዓ.ም. ከዉስጡ በተነሱ የለዉጥ
ሀይሎች ከሥሩ ተገንድሶ ወደ ጎሬዉ ልሄድ ችሏል፡፡
በህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶች እና በሀገራዊ ግንባታ ላይ መልካም ነገር ይሰራል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት አዲሱ በነ አብይ
አሕመድ የሚመራዉ የብልፅግና መንግስት ውሎ እያደረ ህዝቦችን ከማቀራረብ ይልቅ ማራራቅን፣ አንድነትን
ያጠናክራል ሲባል መለያየትን አጠንክሮ ይሠራ ጀመር፡፡ ባህሪውም የአባቱ የኢህአዲግ መመሪያውም የወያኔው ሕገ-
መንግስት ሆነ፡፡ መገለጫዉም የአያቶቹ ጣሊያዊያን እና የወላጁቹ ወያኔን ግብር መድገም ሆነ፡፡ ሌብነት፣ ዘራፊነት፣
ተረኝነት፣ ውሸታምነት ፣ ዘር አጥፊነት፣ ተራ የፖለቲካ ቁማርተኝነት፣ አደርባይነት፣ ህዝብ ከፋፋይነት፣ ህዝብ እና ህዝብ
ደም እንዲቃባ አድራጊነት ፣ ሁሉ የኔ ባይነት፣ ወራሪነት፣ ግዛት አሰፋለሁ ባይነት፣ ቅርስ እና ታሪክ አጥፊነት ዋነኛ
መገለጫቸዉ ሆኑ፡፡
ይህ የአፓረታይድ መንግስት ኢትዮጵያዊነትን አምርሮ የሚጠላ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን አምርሮ የሚቃወም ፣ ወያኔ
በትግራይ ህዝብ ላይ ያደርግ እንደነበረዉ የኦሮሞን ህዝብ ከአጎራባች ክልሎች ጋር ግጭትን በመፍጠር ተነጥያለሁ ብቸኛ

ነኝ ብሎ እንዲያስብ እና እንዲሰጋ ለማድረግ ተግቶ የሚሰራ ቡድን ሆነ፡፡ ይህ ቡድን የህዝቦችን አንድነት እና ህብረት ከራሱ
የፖለቲካ ጥቅም አንፃር ብቻ የሚመዝን ስለሆነ ለዘመናት በአንድነት የኖረን ህዝብ በአንድነት እንዳይቆዩ በተራ አሻጥር
እያለያየ የሚገኝ ቡድን ሆነ፡፡
ለምሳሌ የደቡብ ክልልን መመልከት ይቻላል፡፡ የኦነጉ እነ ሌንጮ ለታ እና የኦህዴዱ እነ አባ ዱላ ገመዳ ( ዳግማዊ
ሥብሀት ነጋ) ቡድን ለኦሮሙማዊ ፖለቲካቸዉ ተፈፃማነት እንቅፋት ይሆንብናል ብለዉ ከአማራዉ ባልተናነሰ ሁኔታ
በግንባር ቀደምትነት የፈረጁት የደቡብ ሕዝቦችን ነበር፡፡ “ይህ የደቡብ ሕዝቦች ክልል በ2018 እ.ኤ.አ የሕዝቡ ብዛት
20,768,000 እንደነበረ እና የመሬት ቆዳ ስፋቱም ከሀገሪቱ 10% እንደሚሸፍን አንዳንድ ጥናቶች ያሳያሉ::”

እንደ አፓርታየዱ እና ፋሺስታዊ መንግስት ግምገማ ከሆነ ይህ የደቡብ ክልል ሕዝብ አስተሳሰቡ ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊ
እና እንደ ክልል ደግሞ ፈፅሞ ደቡባዊ ስሜት ያለዉ ነዉ የሚል ነበር ፡፡[8]
ስለዚህም ሊያራምዱ ላስቡት የግዛት ማስፋትም ይሁን በጉልበት ሀገሪቱን ለመምራት ትልቅ እንቅፋት ይሆንብናል ብለዉ
ስላሰቡ እንደ አያቶቻቸዉ ጣሊያዊያን እና እንደ ወላጆቻቸዉ ወያኔዎች የክልሉን ሕዝብ የእርስ በእርስ ህብረታቸዉን እና
አንድነታቸዉን ለመናድ ተግተዉ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
በዚሁም መሰረት ክልሉን የመበታተን ሴራ ሲዳማን በማስገንጠል ሥራቸዉን ሀ ብለዉ ጀመሩ፡፡ ስለዚህም ጌዲዮ
ከሌላዉ የደቡብ አካል ተነጠለ ለብቻዉ ተቀመጠ ( ለነገ ምን አስበዉለት ይሆን? እግኢአብሔር ይወቀው) ፡፡ ቀጠሉና
የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ብለዉ ሁለተኛ ክልል ፈጠሩ፡፡ገና ይቀጥላሉ፡፡
ከዚህ የደቡብ ክልልን ከመነጣጠል በተጨማሪም በአማራ ክልል ወያኔ አዳፍኖ ያስቀመጠውን የአገውን እና የቅማንትን
የማንነት የሚል ጥያቄ በማስነሳት ክልሉ ህብረት እንዳይኖረዉ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ በአፋር እና በሱማሌ ክልሎች መካከል
በቦታ ይገባኛል ፀብ እንዲቀሰቀስ በማድረግ ለነገ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ህብረት እንዳይኖር ተግቶ በመስራት ላይ
ይገኛሉ፡፡ እነዚህ እንደምሳሌ ተጠቀሱ እንጂ ብዙ የምንዘረዝራቸዉ ነበሩ፡፡
እነዚህ ሂደቶች እንደሚያመለክቱት ፋሺስታዊ መንግስት በሀገሪቷ ዉስጥ ህዝቦች በጋራ እና በአንድነት መቆማቸዉን
ይፈራል ፣ እንደ አያቶቹ ጣሊያዊያን በ5 ዓመት የአርበኞች የህብረት ትግል እንደተባረረዉ እና እንደ ወላጆቹ ወያኔዎች በ4
ዓመት የወጣቶች (ፋኖ + ቄሮ + ዘርማ + ኢጄቶ +…..) የህብረት ትግል እንደተባረረዉ የህዝቦች በጋራ መተባበር
የዉድቀቴ መሠረት ነዉ ብሎ ስለሚያስብ ከቶዉንም የህዝቦችን ህብረት እና አንድነት ከቶውንም አይፈልገዉምም
አይፈቅድምም፡፡
የአፓረታይዱ እና ፋሺስታዊ የሆነው የፌድራል መንግስቱ ለምን የህዝብን አንድነት አይፈልግም ለምንስ የአማራን ፋኖ
ማጥፋት ፈለገ
እንደሚታወቀው መንግስት በመጀመሪያ ተጋርጦበት የነበረውን የወያኔ ጥቃት ለመመከት ሲል በህልውና ዘመቻ ስም
ጥሪ ሲያደርግ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን በግንባር ቀደምትነት ከፊት የተገኙት የጥቃቱ ቀጥተኛ ተጠቂ የነበሩት የአማራ
እና የአፋር ልዩ ሀይል፣ የአማራ እና የአፋር ሚሊሻ፣ እንዲሁም የአማራ ፋኖ ነበሩ፡፡ እነዚህ የአማራ ፋኖዎች ጥሪው
ከመተላለፉ በፊትም ይሁን ጥሪው ከተላለፈ በኋላም እራሳቸውን በትጥቅም ይሁን በሎጂስቲክ እንዲሁም ወታደራዊ
ስልጠናዎችን በራሳቸው ወጪ ሲያደራጁ እና ስምሪት እየሰጡ አኩሪ ጀብዱ መፈፀማቸው እና የወያኔን ባንዳ አይሆኑ
ቅጣት ቀጥተው ብሎም የተለያዩ የመዋጊያ መሳሪያዎችን በመማረክ እራሳቸውን ወደ አንድ ከፍታ ማሸጋገራቸውን

ዓለም የመሰከረው ሀቅ ነው፡፡ በነበሩባቸውም የተለያዩ አውደ ውጊያዎች አኩሪ ገድል ፈፅመው በድል አድራጊነት ወደ
ቄያቸው ተመልሰዋል፡፡ ለፈፀሙትም ትልቅ ተጋድሎ የፌድራል መንግስቱም ትልቅ ምስጋና በየሚዲያው ሲቸራቸው
እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡
የፋኖ አናብስቶች ምንም እንኳን በድል አድራጊነት ክልላቸውን ነፃ አድርገው በአካል ወደ ቄያቸው ቢመለሱም
አዕምሯቸው ግን ፋታ በማይሰጥ ጉዳይ የተወጠረ ነበር፡፡ ምክንያቱም የአፋር ወንድሞቻቸው፣ እህቶቻቸው፣ አባቶቻቸው
እና እናቶቻቸው በወያኔ ባንዳዎች ተወርረው መከራቸውን እያዩ ስለነበር ነው፡፡ ይህም ከቀደምት አባቶቻቸው የተወረሰ
ኢትዮጵያዊ የፋኖ አርበኝነት ስብእና ነው፡፡
ስለዚህም የማለዳ አብሪ ኮኮቦቹ ፣ ፋኖ አናብስቶቹ ሁሉ ከያሉበት ሆነው በሀሳብ በመግባባት በጋራ አንድ ውሳኔ ላይ
ደረሱ እርሱም ወደ አፋር ወንድሞቻቸው ለእገዛ ድጋሚ መዝመት፡፡ ወስነውም አልቀረም ለአፋር ወንድሞቻቸው
እንደርስላችኋለን ጠብቁን የሚል መልዕክት አስተላልፈው ወደ አፋር ለመሄድ በዝግጅት ላይ እንዳሉ በመንግስት በኩል
አትሄዱም ለአፋር መከላከያ ሠራዊት ይላካል በማለት በፌድራል መንግስቱ ተከለከሉ፡፡ ይባስ ብሎም ህብረትን
የሚጠላው መንግስት ለምን ይህንን ዓይነት ጥያቄ አነሳችሁ ብሎ ጥርስ ውስጥ አስገባቸው ፡፡
ነገር ግን አናብስት ፋኖዎች ከአፋር ወንድሞቻቸው ጎን በመሆን ጠላትን ለመፋለም እና በጋራ ድል ለማድረግ
መጠየቃቸውን አላቆሙም ነበር፡፡ የፌድራል መንግስቱም በዘዴም ይሁን በተንኮል ወደ አፋር ክልል እንዳይዘልቁ
በመከላከል የአፋርን ህዝብ ለብዙ ስቃይ እና መከራ እንዲጋለጥ እንዳደረጋቸው ብዙዎች ያምናሉ ፡፡ አሁንም ጦርነቱን
ለብቻው እንዲጋፈጥ አድርጎት መከራውን እንዲበላ እያደረግው ይገኛል፡፡
ግን ግን
 የሠራዊት ሀይል እጥረት አለብኝ ብሎ የተናገረ መንግስት፣ የህልውና ችግር ተጋርጦባኛል ብሎ በየሚዲያው
የለፈፈ መንግስት ለምን ይሆን የአማራ ፋኖዎች ለአፋር ወንድሞቻቸው አጋዥ ሀይል እንሁን ብለው ሲጠይቁ
የከለከላቸው ?
 በህልውና ዘመቻው ወቅት ላስመዘገበው ገድል የተመሰገነው ፋኖ ለምን ይሆን ከጊዜ በኋላ በመንግስት በኩል
በአደገኛ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የገባ?

የአማራ ፋኖዎች የአፋር ወንድሞቻቸውን ለማገዝ በማሰብ እና መስዋትነት ለመክፈል በመነሳታቸው የፌድራል መንግስቱን
ለምን አሳሰበዉ?
የፌድራል መንግስቱ (የኦሮሙማዉ ኦነጋዊ ወ ኦህዴዳዊ ፋሺስታዊ መንግስት) የአማራ ጀግና ፋኖዎች ወደ አፋር ዘልቀዉ
የአፋር ወንድሞቻቸዉን ለማገዝ መነሳታቸዉን እና ወያኔን በህብረት እናጥፋ ማለት ለምን ተቃወመ፡፡ ለምንስ ብሎ
ነዉ ያሞገሰዉን ፋኖ ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ የፈለገዉ የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳት ተገቢ ጉዳይ ነዉ፡፡
የአማራ ፋኖዎች ወደ አፋር ወንድሞቻቸዉ ዘልቀዉ አገዙ ማለት በአማራ ክልል ውስጥ የጎንደር፣ የወሎ፣ የሸዋ እና
የጎጃም ፋኖዎች የፈጠሩት ህብረት እና አንድነት በሁለቱ የክልል ህዝቦች መካከል ተመሰረተ ማለት ነዉ፡፡ ህብረት እና
አንድነት መጣ ማለት ደግሞ የዘመኑ የየክልሉ አርበኞች እንደልባቸዉ ከአማራ ወደ አፋር እንዲሁም ከአፋር ወደ አማራ
፤ ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መዘዋወር ቻሉ ማለት ነዉ፡፡ ይህም ህብረት ወደ ሌሎቹም ክልሎች መዛመቱ የማይቀር

መሆኑ አሌ የማይባል ሀቅ ነዉ፡፡ ስለዚህም ከላይ እንደጠቀስነዉ የ5ቱ ዓመት የአርበኝነት ትግል ተመልሶ መጣ ማለት
ነዉ፡፡ ኢትዮጵያን የሚሉ የእዚህ ዘመን ወጣት አርበኞች እንደልባቸዉ ከአጋዥ ወንድሞቻቸዉ ጋር ተገናኙ ማለት ነዉ፡፡
የወያኔ የክልል ድንበር ግንብ ላያቆማቸዉ ፈረሰ ማለት ነዉ፡፡
እንዲህ ዓይነት እንቅስቃሴዎች ማለትም የአማራዉ ወጣት ወደ አፋር፣ ትግራይ ፣ ኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ፣ የአፋር
ወጣት ወደ አማራ፣ ትግራይ ፣ ኦሮሚያ እና ሱማሌ ፣ የሱማሌዉ ወጣት ወደ አፋር፣ ኦሮሚያ እና ድሬዳዋ ፣ የደቡቡ
ወጣት ወደ ሲዳማ፤ ኦሮሚያ እና ጋምቤላ… ወዘተ የሚፈጥሩት ህብረት እና መተጋገዝ በመጨረሻም በኦሮሚያ
ዉስጥ ለሚኖሩ አንገታቸውን ደፍተው በባርነት ለሚማቅቁ ኢትዮጵያን ለሚሉ በአሥር ሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ
ኦሮሞዎች እና ሌሎች ወገኖቻቸዉ ሀይል እና ጉልበት ስለሚሆኑ ሁሉም አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ኦሮሚያ ከኦሮሚያም
ወደ ሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች እየተዘዋወሩ እንደ 5ቱ ዓመት የአርበኝነት ጊዜ ህብረት ወይም እንደ 4ቱ ዓመት የወያኔ
ዘመን የህብረት ትግል ስለሚፈጥሩ ይህም ለፌድራሉ ፋሺስታዊ አገዛዝ፣ አስቸጋሪ ስለሚሆን እና እድሚያቸዉን
ስለሚያሳጥረዉ ተግተዉ ይቃወሙታል፡፡ ከፋሺስታዊ የፌድራሉ መንግስት አገዛዝ በተጨማሪም ፋኖአዊ ህብረትን
ወያኔዎች፣ ምዕራባዊያን ነጮች እና አረቦች ተግተዉ ይቃወሙታል፡፡ ምክንያቱም ይህ ፋኖአዊ የህብረት አስተሳሰብ
ጠንካራዋን ኢትዮጵያን ይመሠርታታል ብለዉ ስለሚሰጉ ብቻ ነዉ፡፡
በዚህም ምክንያት ከላይ በተወሰኑ ማስረጃዎች ለማሳየት እንደተሞከረዉ የፌድራሉ መንግስት ትናንትና ለአማራ ክልል
ሲታገሉ እና አንፀባራቂ ጀብዱ ፈፅመዉ ለነበሩት ፋኖዎች ባመሰገነበት አንደበቱ የአፋር ወገኖቹን እናግዝ ሲሉ ግን
የፈራበት ምክንያቱ ነገ የሚፈጠርን የህዝቦች የአንድነትና የህብረብሔራዊ ወንድማማችነትን ከመፍራት ብቻ ነው፡፡

መዉጫ
 ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል የሚፈልግ ሁሉ ፋኖ ያነሳዉን ህብረብሔራዊ መተሳሰብን እና መተጋገዝን
ሊደግፍ ይገባል፡፡
 በኦሮሚያ ዉስጥ ያሉ ጃገማ ኬሏዊ ኢትዮጵያዊ ኦሮሞነታቸዉን ተገፈዉ የባንዳዊ የዋቆ ጉቱ ባንዳዊ የኦሮሞነት
ቀንበር ተጭኗቸው ለሚማቅቁት በአሥር ሚሊዮኖች ለሚቆጠሩት የኦሮሞ ወንድምና እህቶቻችን
በተጨማሪም በዚያ ለሚኖሩ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሌሎች ወገኖች እንዲሁም በትግራይ ዉስጥ ያሉ አፄ
ዮሐንሳዊ ኢትዮጵያዊ ትግሬነታቸዉን ተገፈዉ የባንዳዊ የኃይለስላሴ ጉግሳ እና የባንዳዊ ዜናዊ አስረስ/ የመለስ
ዜናዊ አባት/ ባንዳዊ ትግሬነት ቀንበር ተጭኗቸው ለሚማቅቁት በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩት የትግሬ ወንድምና
እህቶቻችን ሁሉ ድምፃችንን እናሰማላቸዉ፡፡ የእነርሱ ነፃ መዉጣት የመላዉ ኢትዮጵያ ነፃ መዉጣት ይሆናል፤
ከዚህም አለፍ ብሎም በነጮች ምዕራባዊያን ፣ በአረቦች እና በባንዳ ውላጆች የተጎነጎነዉን ኢትዮጵያን
የማፍረስ ሴራ ይታደጋል፡፡
በመጨረሻም
አምናለሁ ህብረብሔራዊ ኢትዮጵያዊነት በአሁኑ ጊዜም ሆነ በቀደሙት ጊዜያት በሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጎች ልብ ዉስጥ
ተዳፍኖ ኖሯል ይኖራልም፡፡ ጊዜም ሲያገኝም ከዚህ በፊት ሲገለጥ እንደኖረው አሁንም ይገለጣል፡፡ አሁን ደግሞ ፋኖ ገለጥ

ገለጥ አድርጎ እፍ….እፍ ብሎ አቀጣጥሎታል፡፡ እመኑኝ ብዙም ሳይቆይ ከትግራይ፣ ከአፋር፣ ከደቡብ፣ ከቤንሻንጉል፣
ከሲዳማ፣ ከሱማሌ፣ ከአዲስ አበባ፣ ከጋምቤላ፣ ከሁሉም ክልሎች እኔም ፋኖ ነኝ የሚሉ ድምፆች መሰማት
ይጀምራሉ፡፡ ይህንን ስታዩ ልብ ያለዉ ልብ ይበል የባንዳዎቹ እና የፋሺስታዊ መንግስት የቁልቁለት መንገድ መገባደዱን እና
የሥርዐቱ መሞቻዉ መድረሱን ትገነዘባላችሁ፡፡
በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከእነዚህ አካላት ጋር እየተባበራችሁ ያላችሁ ወገኖች እባካችሁ ነገ ብትፀፀቱ የማትቀየሩት
የጠቆረ ታሪክ ለራሳችሁም ይሁን ለልጆቻችሁ አታስቀምጡ፤ በቻላችሁት መጠን እራሳችሁን ኢትዮጵያን እየጎዱ ካሉት
የባንዳ ልጆች አግልሉ፡፡ ከኢትዮጵያዊ ወንድም እህቶቻችሁ ጋር ተባበሩ ምክንያቱም የሀገራችሁን ትንሳኤ ተደብቃችሁ
ሳይሆን ደረታችሁን ነፍታችሁ በአደባባይ እንድታከብሩ፡፡
ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም የኑሩ!!!!!!

ማጣቀሻ፦
[1] የታሪክ ቅርስ እና ውርስ ገጽ 25
[2] ዝኒ ከማሁ፤ ገጽ 84
[3] ዝኒ ከማሁ፤ ገጽ 86
[4] ዝኒ ከማሁ፤ ገጽ 66-70
[5] http:// am.sewasew.com/Belay Zeleke
[6] የበረሃዉ መብረቅ /ጀነራል ጃገማ ኬሎ/
[7] www.ethiodemographyandhealth.org
[8] Ethio360 ልዩ ዘገባ

Filed in: Amharic