>

የማንነት ፖለቲካ (identitarian politics) የሰነፎች ቁማር ነው...!!! (ሞገስ ዘውዱ)

የማንነት ፖለቲካ( identitarian politics) የሰነፎች ቁማር ነው…!!!

ሞገስ ዘውዱ


*…. የተባነነበት ሌባ ቶሎ ይቆጣል እንደሚባለው ሁሉ ተረኝነት ይቅርና ፍትሃዊ ስርዓት ይስፈን ስትለው ነጠላ ዜማውን ይዞ፣ ነጠላውን ዘቅዝቆ ምንትስ ጠል ነህ ይልሃል። ባሻዬ ይህቺን ዜማ እኮ ላለፉት ረዥም ዓመታት እናውቃታለን። ሌላ ዘዴ ፍጠር!

እውነት ለመሸሽ፣ ሰርቆ ለመደበቅ፣ አቅም አጥሮት ውድድር ሲወድቅ፣ በስንፍናው ሽልማት ሲያጣ፣ ጎበዞች ለፍተው ሀብት አፍርተውና እሱ ሲደኸይ፣ በፍሬ ነገር ሲተች፣ ወዘተ፣ ዘሎ የሚደበቅበት የማንነት ምሽግ ነው። የሱ ችግሮች ሁሉ ተጠያቂ የሌላው ቡድን ሰዎች ናቸው( እንደ ቡድን ማንነት ተኮር የሆኑ ጥቃቶች መኖራቸው ባይካድም)።

የትግል ዘዴውም ፍትህና እኩልነት ፍለጋ ሳይሆን አድፍጦ ግዜ መጠበቅ ነው። ተረኛ ሆኖ “ጠላት” ለመበደል እና ለመበቀል! የኔ ከሚላቸው ሰዎች ተለጥፎ የሱ ሰው አገር ቢሸጥ እንኳን አብሮ ይደልላል እንጂ ተው አይልም። ምክንያቱም የሱ ሰው ያደረገው ሁሉ ፅድቅ ስለሆነ።

የማንነት ፖለቲካ ፍልስፍና፣ አካሄድና ውጤት ላይ ሌላ ግዜ በሰፊው እንመለስበታለን። ለዛሬው ግን አንድ የቀነጨረ አስተሳሳብ ላይ አስተያየት ልስጥ።

እውነታውን በማስረጃ፣ አመክንዮ እና ትንተና ከማስረዳት ይልቅ ሰው ቅሬታ ሲያቀርብ ” ኦሮሞ ፎቢያ” አለብህ እያሉ ሀሳቡን ሳይሆን ሰውዬውን በ shaming, blaming and claiming strategy ፀጥ ለማስባል ዘመቻ ይከፈታል። ሌላው ቢቀር ቢያንስ የሰውዬውን የቀድሞ ስብእና እና ማንነት እንኳን ለማጠራት ግዜ የላቸውም። ለምን ቢባል አላማው ማሸማቀቅ እንጂ እውነቱን መጋፈጥ አይደለም! አሁን የኦህ-dead ካድሬን አትንካብኝ የሚለው መንጋ ከ4 ዓመታት በፊት( ሰው እንዲህ በፍጥነት ይረሳል!?) ወያኔ ተረኛ ነው ብሎ ሰልፍ የወጣ ነበር። በዚያም አላበቃም፣ ታግሎ አባረረው። አንዳንድ ለፍትህ የታገሉት የዋሆች ለውጥ ሊመጣ ነው ብለው ፈነደቁ( እኔም መስሎኝ ነበር)። ከዚያ ጉዳዩ በፍጥነት “የቀን ጅብ” አባሮ “የጅቦች ቀን” መተካት መሆኑ 27 ወራት እንኳን ሳይሞላው ታወቀ።

እናም የተባነነበት ሌባ ቶሎ ይቆጣል እንደሚባለው ሁሉ ተረኝነት ይቅርና ፍትሃዊ ስርዓት ይስፈን ስትለው ነጠላ ዜማውን ይዞ፣ ነጠላውን ዘቅዝቆ ምንትስ ጠል ነህ ይልሃል። ባሻዬ ይህቺን ዜማ እኮ ላለፉት ረዥም ዓመታት እናውቃታለን። ሌላ ዘዴ ፍጠር!

ይሄም አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ ” ፕሮቴስታንት-ጠል” የምትል ዜማ ተለቃለች። ስማ ልንገርህ ወንድማለም፣ እንኳን ፕሮቴስታንት ቀርቶ እናቴ ከባለገች፣ የሰው ሀቅ ላይ ከደረሰች፣ ባለ ግዜ ሆኜ ጎረቤት አምሳለሁ ካለች አንቺ እናቴ አደለሽም እላለሁ ደረቴን ነፍቼ! ነጭ ነጯን፣ በሚያግባባን አማርኛ እንድነግርህ ከፈለግህ፣ አሁን ስልጣን የያዘው ስብስብ ፈ*ጣ፣ ዘ*ፊ፣ እና የሀይማኖትና ብሄር ቅብ ( ethno-religious oligarchy) ሲሆን ተራ ስልጣን ለማግኘት እና ታማኝ ለመሆን ደረጃ አንድ “ኦሮ-ጼንጤ” መሆን፣ ቀጥሎ ፕሮቴስታንት መሆን፣ ከዚያ ከተረፈ ተላላኪ ካድሬ መሆን ይጠይቃል።

ይሄ አካሄድ ለህወሃትም አልበጀም፣ ለትግራይ ህዝብም አንዲት ነገር ጠብ አላለለትም፣ መከራውን አበዛው እንጂ ። አሁንም ቢሆን ለምስኪኑ የኦሮሞ ማህበረሰብ መከራ እንጂ ሌላ ነገር አያመጣለትም። ለPolitical Protestantismም ቢሆን ጥላቻ እንጂ ምንም ዘላቂ ትርፍ አያመጣለትም።

ተረኝነትና ዘረኝነት ይውደም፣ ፍትሃዊ ስርዓት ይለምልም!

Filed in: Amharic