>

የአዲስ አበባ ካቢኔ አባላት ለ1 ቤት እስከ 1ሚሊዮን ብር ጉቦ እንደተቀበሉ  መረጃዎች እየወጡ ነው....!!! (ባልደራስ)

የአዲስ አበባ ካቢኔ አባላት ለ1 ቤት እስከ 1ሚሊዮን ብር ጉቦ እንደተቀበሉ  መረጃዎች እየወጡ ነው….!!!

ባልደራስ


ሐምሌ 1/2014 ዓ.ም የወጣው የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ወድቅ ለመሆን ያበቃውን ምክንያት ሸፍጥ ያቀነባበሩት በዋናነት የኦህዴድ/ብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች እንደሆኑ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለፁ፡፡ አብዛኞቹ ግን እስከ አሁን ድረስ በቁጥጥር ስር አልዋሉም፤ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የሚችሉበት መንገድም የለም ብለዋል ምንጮቻችን፡፡ እንደሚታወቀው፣ በየትኛውም ደረጃ ያሉት የፍትህ አካላት በገዥ ፓርቲ ሙሉ ቁጥጥር ያሉና የህግ የበላይነትን በነፃነት ማስከበር የማይችሉ ናቸው፡፡

 

እጣው ውድቅ የሆነው ከባንክ የተላከው የተመዝጋቢዎች ዝርዝር እና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፕውተር የተጫነው ዝርዝር ልዩነት እንዳለው በመረጋገጡ ነበር፡፡

ወደ ኮምፕውተሩ በገባው ዝርዝር ውስጥ ለመካተት እና በእርግጠኝነት የእጣው እድለኛ ለመሆን እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ጉቦ እንደተከፈለ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ የካቢኔ አባላት ቀዳሚ ተጠርጣሪዎች እንደሆኑም ለማወቅ ተችሏል።

ስለጉዳዩ አስቀድሞ ጥቆማ ደርሶት የመጀመሪያውን ተቃውሞ ያሰማው ባልደራስ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ በአንፃሩ፣ ከንቲባዋን ጨምሮ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች ሂደቱን ግልፅና ፍትሃዊ  ለማስመሰል ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል፡፡ ሸፍጡ ከተጋለጠ በኋላ፣ ምንም እንደማያውቁ መስለው መታየታቸው በብዙዎቹን እንዳላሳመነ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ከንቲባዋ በጉዳዩ ዙሪያ በህግ መጠየቅ ከሚገባቸው ባለስልጣናት መካከል አንዷ ናቸው የሚል አቋም በህግ ባለሙያዎች ዘንድ ጎልቶ እየተሰማ ይገኛል፡፡

እስካሁን ድረስ ባለው ሂደት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው በምርመራ ላይ የሚገኙት፡-

አብርሃም ሰርሞሎ  ——የዘርፍ  ምክትል ቢሮ ኃላፊ

መብራቱ ወልደኪዳን———— ዳይሬክተር

ሀብታሙ ከበደ  ————— ሶፍትዌር ባለሙያ

ዮሴፍ ሙላቱ  —————– ሶፍትዌር ባለሙያ

ጌታቸው በሪሁን ————— ሶፍትዌር ባለሙያ

ቃሲም ከድር    ————— ሶፍትዌር ባለሙያ

ስጦታው ግዛቸው  —————ሶፍፍትዌሩን ያለማ

ባየልኝ ረታ   ————— ሶፍፍትዌር ተቆጣጣሪ

ሚኪያስ ቶሌራ ————— የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ባለሙያ

ዱምሳ ቶላ    ————— የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር  ይገኙበታል።

በተያያዘ;-

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት የዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱን ያለመከሰስ መብት አነሳ!!!

የቀድሞ የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት ዶ/ር ሙሉቀን የመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የተደረገው በሰሞኑ ከጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ማውጣት ጋር ተያይዞ የተፈጠረው በቴክኖሎጂ የተደገፈ የዳታ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በወንጀል በመጠርጠራቸው ነው

/

Filed in: Amharic