>

" ቶሎ አገራችንን ልቀቁ አለበለዚያ እርምጃ እንወስዳለን" እየተባልን ነው ለወገን አድርሱልን...!!! (ሮሐ ኒውስ)

” ቶሎ አገራችንን ልቀቁ አለበለዚያ እርምጃ እንወስዳለን” እየተባልን ነው ለወገን አድርሱልን…!!!

 -በቄለም ወለጋ ዞን በሰዮ ወረዳ  በደቢዶሎ ያሉ አማሮች

ሮሐ ኒውስ

በቄለም ወለጋ ዞን በሰዮ ወረዳ  #በደቢዶሎ   ከተማ 04ቀበሌ ውስጥ የሚኖሩትን አማራወች  በ4/11/2014 ከምሺቱ 3ሰአት  ጀምረው ኦነ*ግ  ሼ*ኔወች በየቤታቸው በመዞር የባንክ አካውታችሑን አምጡ : በተቀረ ትገ*ደላላችሁ : ምን እየሰራችሁ ነው ወደአገራችሁ ግቡ : ሐገሩ የኛንጅ የእናንተ አይደለም : ንብረት  መሸጥ  መለወጥም አትችሉም : ስለዚህ እርምጃ  ከምንወስ*ድባችሑ በፊት ልቀቁ በማለት  ሲያሰ*ቃዩዋቸው ማደራቸውን ምንጫችን ከስፍራው አድርሶናል::

በአለም ላይ ያላችሑ ሁ አማራወች ድምጽ ሑኑን : ወደሐገራችን  መግባትም አልቻልንም : ሕይወታችንን ታደጉልን ብለዋል::

#ሌላው

በደቢዶሎ ዙሪያ ያሉ ቀበሌወች : በሰዮ ወረዳ ውስጥ #በቀልቀልቻ_ቡቡካ_ቀበሌ  ገላኖ : ሜጢ : ወልገይ : ጉዲና : እሪጳ : አየር ማረፊያ : ጉቴ ሰዮማ   በሚባሉ  ቀበሌዎች  ውስጥ ያሉ አማራወች  ዘንድ  እየገቡ   በግ*ዴታ  ምግብ  ይመገባሉ  : ከተመገቡ  በኃላ ወደሐገራችሑ ለምን  አትመለሱም : ይሔ  የእናንተ ሐገር  አይደለም  አንድቀን እርምጃ እንወስድ*ባችሑለን : መንግስት እሚለውን አትስሙ በማለት እያ*ሰቃዩአቸው እንደሖነ መረጃ አድርሰውናል::

የመንግስት የጸጥታ አካልም በአካባቢው የሉም  : ከተማ ውስጥ  ቢኖሩም ምንም አይነት እር*ምጃ  እየወሰዱ እንዳልሆነና ብናመለከትም እሚሰማን  የለም : አርፋችሁ ተቀመጡ የሚል ምላሺ ነው  የተሰጠን ብለዋል::

Filed in: Amharic