>

ህግ ቢኖር ለእጣ መጭበርበር ዋንኛው ተጠያቂ መሆን ያለበት አዳነች አቤቤ ወይስ ዶ/ር ሙሉቀን ....???  (አባይ ነህ ካሴ)

ህግ ቢኖር ለእጣ መጭበርበር ዋንኛው ተጠያቂ መሆን ያለበት አዳነች አቤቤ ወይስ ዶ/ር ሙሉቀን ….???

አባይ ነህ ካሴ

*… አዳነች አቤቤ የኮምፒውተር ሥራው ሁሉ ተጠናቅቆ ወደዚያ አካባቢ ማንም ድርሽ እንዳይል ከተደረገ በኋላ ያሬድ የሚባል ባለሙያ አምጥተው የተዘጋውን ኮምፒውተር ቤት አስከፍተው እንዲነካካ ማድረጋቸው ለምን ሊሸፋፈን ተፈለገ..?

ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ መተንፈስ አልቻልሁም (I can’t breath) እስኪሉ ያደረሳቸውን አፈና ዐይቶ ዝም ማለት የሚቻል አይመስለኝም ነበር። ምክር ቤቱ ያለ መከሰስ መብታቸውን በሚገርም አፈና ከገፈፈ በኋላ እንደሚደረግ እርግጠኛ የነበረው አካል ወደ ማረፊያ ቤት ወስዷቸዋል።

ሰውዬው ስርቆት ውስጥ ገብተው ከኾነም እንኳ የተሔደበት መንገድ ፍጹም ኢፍትሐዊ ነው። በተደጋጋሚ አፈ ጉባኤዋ የፈጸሙት አፈና በግላጭ ታይቷል። ዶ/ር ሙሉቀንም ለታሪክ ይቀመጥ ብለው በልዩ ርጋታ ተከራክረዋል። ተመዝግቧል። ከአፈ ጉባኤዋ በመቀጠል የመስተዳድሩ ቴሌቪዥን ሠራተኞች ያደረጉት ድምፅ አፈናም ተመዝግቧል። የስርጭቱ ማይክ ጠፍቶ ግን በአዳራሹ ግን እየተሰሙ ሰውዬው እየተናገሩ በቪድዮ ምስላቸው ታይቷል።

በዚያ ኹኔታም ውስጥ ኹለት የጥርጣሬ ነጥቦችን ማስመዝገባቸውን ተረድቻለሁ።

፩ኛ. በኋላ በየመድረኩ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል የሰማነው የዶ/ር ሹመቴ ቢሮ ለእገዛ ተጠይቆ እምቢኝ ማለቱ

፪ኛ. አዳነች አቤቤ የኮምፒውተር ሥራው ሁሉ ተጠናቅቆ ወደዚያ አካባቢ ማንም ድርሽ እንዳይል ከተደረገ በኋላ ያሬድ የሚባል ባለሙያ አምጥተው የተዘጋውን ኮምፒውተር ቤት አስከፍተው እንዲነካካ ያደረጉት ነገር።

በተለይ ኹለተኛው ብዙ ትኩረት ይሻል።

ሀ. ከንቲባዋ በፈለጉት ሠዓት የፈለጉትን ሰው ይዘው የመግባት ሥልጣን ማን ሰጣቸው?

ለ. የላይኛው የታመነበት አሠራር ነው ከተባለ እንኳ ባመጡት ባለሙያ የመጨረሻዋ አረጋጋጭ በመኾናቸው ተጠያቂነቱ ከዶ/ር ሙሉቀን ይልቅ እርሳቸው ላይ ለምን አልወደቀም? ምክንያቱም ከዕጣ ማውጣቱ በፊት የመጨረሻውን ቁልፍ የተጫኑት በያሬዳቸው በኩል እርሳቸው ናቸውና!

Filed in: Amharic