>

አለም የዘነጋት ሀገር፣ አለም የዘነጋው ህዝብ  (አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም)

አለም የዘነጋት ሀገር፣ አለም የዘነጋው ህዝብ 

አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ

እንደ መግቢያ 

2014 በዐረቡ ዓለም በወገኖቻችን ላይ በደረሰው ግፍና በደል ብሔራዊ ውርደት ነው ብለን ነበር ዛሬስ በወለጋና በሌሎች የአገር ክፍሎች ውስጥ ለሚፈፀመው አረመኔያዊ ተግባር ምን ስያሜ እንስጠው ?

#ከወለጋው ቶሌ’ ቀበሌ ዙርያ ግድያ በፊት፣ በዐማራው ህዝብ ላይ ተመሳሳይ ጨካኝ ግድያዎች ተፈጽመውበታል። በስካቫተር እየተዘገነ’ በአንድ ጉርጓድ ከሰማንያ ሰው በላይ ሲቀበር ተመልክተናል። ግን’ ሞትን አለማመዱን።

~#የአንድ_ሰሞን‘ የፌስቡክ ጩኽት ከመሆን የዘለለ ትግል አላደረግንም። ወዳጄ ልቤ’ ! በምናብህ’ የነበረችው #ኢትዮጵያ ዛሬ የለችም። ለዐማራው ህዝብ ሞት’ ራሱ ዐማራው ብቻ ነው ዛሬ’ የሚያለቅሰው። 

~#አትሞኝ! ብሄር’ ብሄረሰብ የሚለው አድማቂ’ ሰፈሩ ድርስ ሞት እስካልመጣበት ድረስ፣ ስላንተ ሞት ሌላው ብሄር ደንታ እንደሌለው እየተረዳህ አይመስለኝም።

~#ስለዚህ‘ … በራስህ ላይ ብቻ ቆመህ ተከላከል። የሰው ልጅ አንዴ ይሳሳታል! ሁለተኛውን ከደገመ ግን’ ራሱ ዕልቂቱን በፈቃዱ መርጡኣል ማለት ነው። የፈረንጅ ጥቅስን ማስቀደም እንወዳለንና’ እንካ የፈረንጅ ጥቅስ።

የወለጋ ዘር የማጥፋት ወንጀል ስርአታዊ ቅንብር  ወይንስ ክስተት ?

የ ሀገር ሰላም ለመጠበቅ የታጠቀን ፋኖ ለማስፈታት በአስር ሽሆች እየአሰረ እና እያፈነ ያለው የኦሮሞ ብልጽግና መራሽ መንግስት በወለጋ በሁለት ቀናት 300 የሚጠጉ አማሮች ከቤት ለቤት አሰሳ ሲጨፈጨፉ የእግዚያብሔር ያጥናችሁም ሆነ ነፍስ ይማር ከማለት ይልቅ አሁንም ሰላማዊውን ፋኖ ትጥቅ ለማስፈታት ላይ ነው። በአለፉት ሁለት ወራት ከታዋቂ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ መስከረም አበራ እና እስከ ስለሰበአዊ መብት ተሟጋች ሰላማዊ ወገኖቻችንን በማሰር እና በማፈን ተጠምዷል።

የስርአቱ አካል የነበረው አቶ ዮሐንስ ቧ ያለው በፌስቡክ ገጹ እንዳስነበበን በወለጋ እየተካሄደ ያለው ጄኖሳይድ ክስተት ሳይሆን በእቅድ እና በስርአት እየተካሄደ ያለ መዋቅራዊ መሰረት ያለው ወንጀል ነው። በተመሳሳይ የኦሮሞ ጽንፈኞች እየተካሄደ ያለውን ዘር የማጥፋት ፍጅት እኔ አይደለሁም መንግስት ነው በሚል እርስ በእርስ የጣት ጥቆማ ተጠምደዋል። የሽመልስ አብዲሳ እጅ ይሁን የሌላው ከህግ ውጭ ነው የተባለ ታጣቂ ስልቻ ቀልቀሎ ከሚለው አባባል ያላለፈ የኦሮሞ መንግስት ይሁን አማጺ ነን ባዮች ሁሉም በመርህ አንድ እና ልዩነት የሌላቸው ጠባብ ፋሽስት መሆናቸውን ያለፉት 40 አመታት አሳይቶናል። 

አማጺ ነኝ ባዩ የኦሮሞ ጽንፈኛም ሆነ መንግስት ነኝ ባዩ ስልጣን የጨበጠው ጠባብ ብሔርተኛ ቡድን ለ 30 አመታት ኢትዮጵያን በመንፈስ አፍርሶ የተለያዩ የደቡብ አፍሪካ በአፓርታይድ ስርአት የነበሩ ባንቱስታን የተባለ ስራትን ያለምንም ማስተካከል በስርአትነት የተቀበለው እና በህገመንግስት ያጸደቀው መንግስት ዛሬም የከፋ የከረፋ ዘረኛ ስርአትን ያስቀጠለ እንጅ የሐገራዊ አንድነትን ያመጣ፣ ገዳይ እና ሀገር አፍራሽ የሆነውን ህገመንግስት መርህ አርጎ የቀጠለ እንጅ አይን ለመመለስ እንኳን ለማስተካከል ያልሞከረ መሆኑን ሊሰመርበት እና እየተሰራ ያለው የጅምላ ጭፍጨፋም የስርአቱ አካል መሆኑን ለታሪክም ለአለማቀፍ ፍርድቤትም ሊዘገብ ይገባዋል።

ከትቂት ቀናት በፊት በፓርላማ ተጠይቀው ሰላማዊ ህጋዊ ታጣቂ አማሮችን የኩነኑት ጠቅላይ ሚኒስቴር የወለጋ ገዳዮችን ከህግ አክባሪ የሀገር ተስፋወች ጋር ሲያነጣጥሩ አይተናል። ይህ የሚያሳየን ሸኔ ከመንግስት ኦሮሞ መራሽ መንግስት ከሸኔ ያልተለያዩ አካላት መሆናቸውን እንጅ አንዱ የዘረኛ ስርአትን ተጻራሪ ሌላው የስርአት ደጋፊ መሆናቸውን አይደለም።

ለዚህ የዘረኞች መተጋገዝ እና የጸረ ኢትዮጵያ እና ጸለ አማራ ሴራንም ሆነ ቀጣይ ግድያን ማቆም የሚቻለው ገዳይህ አዛኝ እስኪሆን መጠበቅ ሳይሆን አሁንም በመደራጀት፣ እራስን በማስታጠቅ እና አይቀሬውን የስርአት ለውጥ ተጋድሎን ማድረግ ነው!

ትዝብት—- በጎንደር በአማራ እና በኢትዮጵያ ጠላቶች የተቃጣውን ዜጋን እስር በእርስ የማጋጨት አስከፊ ሙከራ እንደ የህዝብ እና የሀይማኖቶች ግጭት አድርገው ሲያጎሩ ያየናቸው በስም ተቃዋሚ በተግባር የዚህ ዘረኛ ስርአት ደጋፊወች ዛሬ አትተንፍሱ፣ አትናገሩ፡ አብይ ምን ያድርግ ሲሉ ማየት እጅግ የሚያሳፍር ተግባር ነው። 

ዘረኝነትን በአፍ ማስቀጠል አይቻልም የሚገድሉትና ገዳዮቹ “እየመረጠ ያለቅሳል” የሚሉት የአማራ ምስኪን ሕዝብ!

የጎሣ ፌደራሊዝምና የጎሣ ፖለቲካ እስካልተወገደ ድረስ የአማራው መሞት ይቀጥላል!

ጠቅላይ ሚ/ር አቢይ አህመድ በJune 20/2018 የወልቂጤ ውሏቸው “ከቤኒሻንጉል ክልል የአማራ ብሄር ተወላጆችን ያፈናቀሉ የክልሉ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው ይነሳሉ ፣ ለፍርድም ይቀርባሉ። ተፈናቃዮችም ወደነበሩበት እንደመለሱ መንግስት ይሠራል። ካሣም ይከፈላቸዋል” ብለው ነበር። ይህ ንግግራቸውና ግድያና መፈናቀሉ “የሉዐላዊ ሃግራቸውንና ብሄራዊ መዝሙሯን ለምን ትከለክላላችሁ” በሚሉን የርሳቸውና የኦህዴድ “ኦሮምያ ሪፑብሊክ” አይመለከተውም:: ይልቅ አማራውን የደም ካሣ እያስከፈሉት ነው:: ጭፍጨፋውም መፈናቀሉም ቀጥሏል:: ያሰሩትም ይሁን ለፍርድ ያቀረቡት የለም:: ቀልድ ነበርና:: እርሳቸው ፋኖን ትጥቅ ሲያስፈቱ “የስጋት ምንጭ አይደለም” ያሉን ሸኔ ጭፍጨፋውን ቀጥሏል:: ይህ ግልፅ ነው:: ፖለቲካዊና ተቋማዊ ቁማርም ነው:: የሸኔ ጭፍጨፋ “በህግ ማስከበር” ስም የተከፈተው አማራን የማዳከም ዘመቻ ወታደራዊ ቅጥያ (extension) ነው::

አሁን ለይቶለታል:: የብልፅግናቸው የስልጣን ችግኝን የሚያጠጡት የአማራን ደም ነው:: አማራ ኢትዮጵያን ማዳን የሚችለው እራሱን በመጀመሪያ ማዳን ሲችል ነው:: ፍትህን በትግልህ እንጂ ወንጀለኞችን ተማፅነህ አታገኝም:: ፍትህን የምትጠይቃቸው የግድያ ምላሽ የሚሰጡህንና የመኖር ሕልውናህ ላይ ጦርነትን ያወጁ ጠላቶችህን ነው:: የአዞ እምባቸውን የሚያፈሱ የቀበሮ ባህታውያንን ነው:: 

ይልቅ እንደ እንድ ሠው ቆመህ ሚሊዮን ሕዝብ ሆነህ እራስህን ለማዳን በዚህ የጎሣ ፌደራሊዝም ሥርዐትና በአስተናጋጆቹ ላይ ሳይመሽ ዝመት:: መብትና ነፃነት በልመና አይገኝም:: እምቢ ለነፃነቴ ብለህ በሕብረት ተነሳ:: ሞት በርህን እያንኳኳ ነው:: ሁለት ሕይወትም ይሁን ሞት የለም:: 

የቤት ሥራህን ዛሬውኑ መሬት ላይ ጀምር! 

ይብቃህ!

የሰላም በሮች ሲጠረቀሙ የአመፅ በሮች ይከፈታሉ! በፈርጣማ ክንድህ በርግደው!

We Do Not Beg For Freedom; We Fight For It!

ይሄው ነው፡፡

አሳዛኙ ሁነት

በጥላቻ መንፈስ ተገፋፍተው ኦሮሚያ ተብሎ በሚጠራው ክልል ውስጥ በሚኖሩ የአማራ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ወንድሞቻችን፣ልጆቻችን፣እህቶቻችንና አባቶቻችን ላይ የተፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት ግድያ መሰረታዊ ምክንያት አዲስ ሀገር ከመመስረት የመነጨ እኩይ ተግባር ነው፡፡ እንዲህ አይነት ተመሳሳይ የገሳ ማጽዳት ተግባር ዳግም እንዳይከሰት ከተፈለገ በወያኔ እና ኦነግ ፊትአውራሪነት የጸደቀው ህገመንግስት ተራማጅ በሆነ ህገመንግስት በሰለጠነ መንገድ መቀየር እንዳለበት ብዙዎች ኢትዮጵያዊ ምሁራን በየጊዜው ሳይሰለቹ ምክረ ሃሳባቸውን አቅርበዋል፡፡ በእኔ በኩል ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች መፈጸም ይኖርባቸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ እነኝህም፡-

  1. በኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎች መሰረታቸው ጎሳ ላይ መሆን የለበትም
  2. በኢትዮጵያ የዘር ማጽዳት ወንጀል የሚቆመው ሀገሪቱ በጎሳ ክልሎች እንድትከፋፈል የሚፈቅደው የጆሴፍ ስታሊን መሰል የሆነው ህገመንግስት በሰለጠነ መንገድ፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ይሁንታ መቀየር አለበት የሚለው የግል አስተያየቴ ነው፡፡

በአሁኑ ግዜ የአማራ ህዝብ ተስፋ መቆረጥ ያለበት አይመስለኝም፡፡ በከፍተኛ ደረጃ እየተጠቃ ያለው ይሄ ህዝብ በመሆኑ አንድነቱን በማጠናከር ራሱን ከጥቃት መከላከል ይገባዋል ባይ ነኝ፡፡ ማናቸውም ነገሮች በእጁ ላይ ያሉ ይመስለኛል፡፡ ታሪክ የህብረት ችቦ እንድንለኮስ ግድ ብሎናል፡፡ ግፉ ይበቃል፡፡  በቃ፣በቃ፣በቃ….›› ENOUGH ENOUGH ENOUGH ….( ENOUGH) (power of infinity). ኢትዮጵያዊ የአማራ ወንድሞቻችን ደም በሰማይ ላይ እየጮሀ ይገኛል፡፡ The blood of Amharas is crying higher and higher to the heaven, ስለሆነም የወንድሞቻችን ደም እንዳይፈስ  ውስጣዊ መፍትሔ መሰጠቱ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ ራስን ከጥቃት አለመከላከልን የመሰለ ውድቀት የለም፡፡ ራስን ከጥቃት መከላከል ተፈጥሯዊ ነው፡፡ እንኳን የሰው ልጅ አራዊቶች ራሳቸውን ከጥቃት እየተከላከሉ ነው ዝርያቸውን ያቆዩት፡፡

 

 በነገራችን ላይ በወለጋና አካባቢው እየፈሰሰ ያለው የንፁሃን ደም ከሰማይ ሰማያት ይጣራል፣ የጭካኔና የግፍ ቁና ሞልታለች:: ለአለቁት እንባችን አፍሰን፣ በአካል ለተጎዱና ለተሰቃዩ ሁሉ መሪር ሃዘናችንና መፅናናትን ገልፀን ይህ የወገንን ደም እንደዥረት የሚያፈስ እጅግ አፀያፊና አሰቃቂ ድርጊት እንዲገታና እንዲወገድ ምን ማድረግ ይገባል የሚለው ጥያቄ ግን አንገብጋቢና አጣዳፊ መልስ ይሻል:: በእኔ አስተያየት የሚከተሉትን አነሳለሁ- 

1) ኃላፊነቱ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነው የሚል እምነት ቢኖረኝም፣ በኦሮሞ ሕዝብ ስም ለሚነግደው አሸባሪ ቡድን የኦሮሞ ኅብተሰብ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ሆ ብሎ በተቃውሞ ሊነሳ ይገባዋል፣

ሀ) የኦሮሞ ፋኖዎች በአፋጣኝ በድርጅትና ትጥቅ ተዘጋጅተው ጫካውን ከዚህ አረመኔ ቡድን ጋር ፊት ለፊት መጋራትና መመንጠር ይኖርባቸዋል:: ከዚህ አኳያም በውጊያው አውድማ ላይ የአማራና የልዩ ልዩ አስተዳደር ፋኖዎች እንዲቀላቀሏቸው እቅፋቸውን ከፍተው መቀበል አለባቸው የየሚል ሃሳብ አለኝ:: 

ለ) በዚህ አረመኔ ቡድን ላይ መለስተኛ የክተት ጥሪ ሊታወጅ ይገባዋል:: ከዚህ አንፃር እልቂቱ እየደረሰበት ባሉት አካባቢዎች ሕዝቡ ለክተት እንዲዘጋጅና ከሰፈሩ እስከ ጫካው ያለውን ጉዱን እንዲከላ በቆራጥነት መነሳትና መሰለፍ ይኖርበታል፣ 

3) በመንግሥትና አስተዳደሩ ውስጥ በየእርከኑ ባሉ የአሸባሪው ቡድን አባላትና ደጋፊዎች በመብራት እየተፈለጉ አስቸኳይ ህጋዊ ውሳኔ ሊወሰድባቸው ይገባል፣ አውቆ ለሚገድልና ለሚያስገድል ስለሚፈረድበት ህጋዊ ፍርድ ነፍሴ አትራራለትም፣ ያውም በኃላፊነት ቦታ ላይ ተቀምጦ?

4) በተቻለ መጠን ከጎረቤት መንግሥታት ጋር በመተባበር አሸባሪውን ቡድን አጣብቂኝ ውስጥ በማስገባት ከሚካሄደው የመመንጠር ዘመቻ ጋር የእለት ጉርስና የትጥቅ ፍሰት እንዲነጥፍበት መሥራት፣ 

ማሳሰቢያ:- 

1) ምንም እንኳ የኦሮሞን ሕዝብ የማይመጥኑ መወገድ የሚገባቸው “እግዴዎች” ፊውታራሪነትና በፖለቲካ መሸቀጫነት ሽብርን እንደ መሳሪያ በመጠቀም ሥልጣን የሚናፍቁ ስንክልክል ያሉ የፖለቲካ ዱክማኖች አጃቢነት የለበትም ባይባልም፣ “የኦነግ ሸኔ” እንቅስቃሴ ከሕወሓት ዓላማና የተግባር እንቅስቃሴ ጋር የተቆራኘና የተናበበ መሆኑን ያለምንም መጠራጠር መረዳት ያስፈልጋል:: ልብ ብለን ለምንከታተልና ለምንገነዘብ ሁሉ ይህ መሰሉ ከዱር እንሣትነት ያነሰ እልቂት በየጊዜው ወቅት እየጠበቀ የሚከሰተው ሕወሓት አንድም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሲገባ ከገባበት ማጥ ለመውጣትና ሁኔታዎችን ለመለወጥ ሲጥር፣ አሌያም የስልት ለውጥ ሲያደርግ እንደ መሸጋገሪያነት ለመጠቀም ሲንደረደር ነው በአማራና ኦሮሞ ኅብረተሰቦች መካከል ግብግብ ለማስፈጠር የሚገለገልበትን ቀይ ካርድ በመምዘዝ አሸባሪ ቡድኑን እንደ ውሻ ያዝ እሽው የሚለው:: 

2) የሚደረጉ ፀረ “ኦነግ ሸኔ” እንቅስቃሴዎች ሁሉ ሥነ ሥርዓት የያዙና በየእርከኑ ካሉ ኃላፊዎች ሥምሪት የተሰጠውና ለቁጥጥር የተመቸ መሆን ይኖርበታል:: የሰሜኑ ጫፍ ሀገራችን ጉዳይ እንዳረገዘ ነውና ሰሜኑ ሳይላላ ደቡቡን የማጥበቁ ሚዛናዊ ስልት የግድ መታሰብ ያለበት ነው:: 

3) የሚያዋጣን ሃሳብና ተመክሮ እየተለዋወጥን በአሸባሪዎች ላይ በአንድነት መዝመት እንጅ የትም የማያደርስና ምንም የማይፈይድ የእርስ በርስ አንቲካራና ብሽሽቆሽ መሆን የለበትም:: በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው የግፍ ጭፍጨፋ ንፁህ ህሊና ያለውን ሁሉ ያማል ይዘገንናልና በጋራ ምን እንድርግ ላይ እንረባረብ:: 

እየተገደሉ ያሉት ሰዎቸ ናቸው፡፡

እውነቱ ሊነገር የሚገባበት ትክክለኛው ሰዓት ችግሩ አፍጥጦ የመጣበት ሰዓት ነው። ነገር ግን ሰዉ ስሜታዊ የሚሆንበት፣ የተከፋበት እና ያዘነበት ሰዓት ስለሆነ መናገር አትችልም። ብትናገር ብዙ ውግዘት ይጠብቅሀል። ኦሮሞው ሲገደል ከተናገርክ – ገዳዩን ወገን ልታሰየጥን ነው ይልሀል። አማራው ሲገደል ከተናገርክ – ጀስቲፋይ ልታደርገው ነው ይልሀል፣ and the vice versa! ለትግሬውም፣ ለሲዳማውም፣ ለአፋሩም ያው ነው! አዙሪት!

ሀሳቡን ብቻ ለመረዳት ብሎም በደጉ፣ በሰላሙ ጊዜ ቆም ብሎ ለማሰብና ሰቆቃውን አስቀድሞ ለማስቀረት የቀነጨረው ጭንቅላትህ አይፈቅድልህም! ችግር ነው! ያንተ አስተሳሰብ እስኪለወጥ ወይም/እና ሥርዓቱ ሕግ አክባሪና አስከባሪ እስኪሆን የሚለወጥ ነገር ስለሌለ በየቦታው ግፍ ሲፈፀም ኡኡ ላለማለት ወስኜ ትቼዋለሁ። ብያለሁ ለማለት ካልሆነ ለውጥ የለውም።

አላውቅም፣ ከዚህ በፊት ያላልኩት – አሁን የምለው አዲስ ነገር የለኝም። ለመድገም ያህል . . . በሰው ልጆች እኩልነት፣ በሰብዓዊ መብት መከበር፣ በመከባበር፣ በሕግ የበላይነት፣ በልዩነት ተፈጥሯዊነት፣ ወዘተ እስክናምን ገና እናልቃለን! እንተላለቃለን!

በየቦታው የሚገደሉትና ተሸማቅቀው የሚኖሩት ንፁሀን የአንድ ብሔር፣ የአንድ ሀይማኖት፣ የአንድ የፖለቲካ አመለካከት፣ የአንድ ፆታዊ ምርጫ አራማጆች ስለሆኑ አይደለም። በመንግሥት መዝገበ ቃላት እንደተጠቀሰው “አናሳ” ስለሆኑ ብቻ ነው! 

የሀይማኖት አናሳ – መናፍቅ/የማርያም ጠላት፣ 

የብሔር አናሳ መጤ- ነፍ ጠኛ፣ ወራሪ፣ ሸ ኔ፣ 

የሴክሹዋል ኦሪየንቴሽን አናሳ – ቡሽ’ቲ

የፖለቲካ አመለካከት አናሳ – አጎብዳጅ፣ ተላላኪ፣ ባንዳ፣ ገንጣይ፣ አስገንጣይ . . .

ወዘተ እየተባሉ፣ አናሳዎች መብታቸው ተሸራርፎ፣ ከሰው በታች ተደርገው፣ አንገታቸውን ደፍተው የጥቃት ሰለባ የሚሆኑበትን ቀን ይጠብቃሉ!

በየቦታው የሚገደሉት ንፁሀን ሰዎች አይደሉም። ሰውነታቸውን አስቀድመው በትርክት የተገፈፉ ነፍ ጠኞች፣ ኦነጎች/ሸኔዎች፣ ቡሽ’ቲዎች፣ ባለጊዜዎች፣ መጤዎች፣ መናፍቃን ወዘተ ናቸው። ለእርድ ሲዘጋጁ የኖሩና አሁንም የሚዘጋጁ! በብሔርተኞች እና በበከቱ አክቲቪስቶች ቁማር የሚቆመርባቸው፣ ደራሽ፣ አዳኝ፣ ታዳጊ የሌላቸው አናሳዎች ናቸው። ከኑሯቸው ይልቅ ሞታቸው ለቁጥር፣ ለማታገያነት፣ ለሽቀላ የተመቹ tokens ናቸው! 

ሰዎች አይደሉም!

ዛሬ፣ ትናንት እና ከትናንት ወዲያ አንድን ቡድን በጅምላ dehumanize ስታደርግ፣ ስትሰድብ፣ ስታጥረገርግ ከርመሀል። ላንተ ከኪቦርድ እና ከላይክ ያላለፈ የፌስቡክ ውሎ ሊሆን ይችላል። ኪሎ-ባይታም ጭንቅላትህ ከዚህ ያለፈ አያስብም። ያንተ ቢጤ ሰላሳ ሺህ በክቶች ግን አሉ! ያግዙሀል። ይሄ ሁሉ ተደምሮ የሚያመጣው ውጤት ያው ነው። መሳሪያ ባለመያዝህ ብቻ ነው ከነሱ የለየህ፣ ከነሱ ብትብስ እንጂ አትሻልም። ገዳዮቹ ሰምተው፣ ተከትበው ነው። አንተ ግን ከታቢው፣ ነጋሪው ነህ! 

ሬሳ ባየህ ቁጥር ኡኡ አውግዙ ማለትህ ነፃ አያወጣህም። ስላወገዝክም የሚለወጥ ነገር የለም። መነሻው፣ ምንጩ፣ መፈልፈያው አንተው ነህ። ቃላትህ ይገድላሉ፣ ያድናሉ። ያፀድቃሉ፣ ያሰየጥናሉ! ያሰየጠንከውን አድማጮችህ፣ አንባቢዎችህ፣ ተከታዮችህ፣ ቢጤዎችህ ለምን አይገድሉት? እንደሱማ ከንቱ ድካም ይሆንብሀል!

እንደነብዩ ኢሳይያስ ከ”ወዮላችሁ” ወደ “ወዮልኝ” ተሻገር! የራስ ፈስ አይሁንብህ፣ ራስህን እይ። ራስህን ዐቅብ! ለሆነው ሁሉ ያንተ እጅ አለበት! ወደራስህ ተመልከት!

ምናልባት ያኔ ተስፋ ይኖረናል!

ከክፉ ተወልጄ….

ላለፉት 27 ዓም የጎሣ ፖለቲካን በተጣቡና በፈበረኩዋቸው ምስያዎቻቸው በሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን ግፍ፥ መከራ፥ እንግልት ፥ በደል ፥ እሮሮ ፥ ፍትህ ፥ እኩልነትና ነፃነት እጦት አልታይ ብሏቸው ስለ መንገድና ሕንፃ ግንባታ ተጨንቀው ለምተናል በልፅገናል ከዓለም ተወዳዳሪ የሆነ ምጣኔ ሃብት ልማት ደርሰናል እያሉ ሲደስኩሩ የነበሩ ፣ ምሁራን ሳይሆኑ የምሁራነ ቋንቋ ሳይገባቸው በሚያነበንቡና ድዊያን ጉርባ ካድሬዎቻቸው ዛሬ ኢትዮጵያ የሰው ልጆች መብት የተደፈጠጠባትና የተረገጠባት የአምባገነን  ፋሺስቶች የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ መኖራችንን በሌላኛው ዓይናቸው በገሃድ ሲያዩት ኅሊናቸው ምን ይነግራቸውና ይወቅሳቸው ይሆን ?

ከዚህ ቀደምም በተለያየ መጣጥፌ ውስጥ እንዳኖርኩት የአንድ መንግሥት ፍሬያማነት ወይም ውጤታማነት በዋናነት የሚለካው የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች በመጠበቅና በመከላከል በሚያደርጋቸው ተቋማዊ ሥራዎቹ እንጂ ባነጠፈው የተንጣለለ መንገድ ወይም ገዢዎቹ ከሕዝብ ካዝና በዘረፋ ገንዘብ በገዟቸውና በየአውራ መንገዱ በሚሽከረከሩት ውብ ካዲላስ መኪናዎች ዓይነት አይደለም ። 

ሰብዓዊ መብቶች ከተከበሩና በሕግ አግባብነት ከተጠበቁ የምንመኘው ልማቱ በተከታታይነትና በቋሚነት ተከትሏቸው ይመጣል ።

ሰብዓዊ መብቶች እንዳይደፈጠጡ፥ እንዲከበሩና ወደፊትም እንዲጠበቁ ዋስትና የሚኖረው ይህንን ሁኔታ በሕግና በተጠያቂነት ማስከበር የሚችሉ የፍትህና ለሰው ልጆች መብት ፈጥነው ዘብ የሚቆሙ ተቋሞችን በማቆም ነው ። 

ከዚያ ውጭ ዳግም ላለመፈፀማቸውና ላለመመለሳቸው ዋስትና የለም ። 

ለውጡ ተቋማዊ መሆን አለበት ። 

አሮጌው ተቋም ፈርሶም በአዲስ መተካት ይሻል ። 

ይሄ ደግሞ ዕውን ሊሆን የሚችለው የሕዝብ መንግሥት ሲመሠረት ብቻ ነው ።

መናደድ ሲበዛ…………..

እሳቱ ተሰማ የሚባል የቀድሞው ዝነኛው የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራ ዘፋኝ አንድ የታወቀባትና በዘፈን ምርጫ የራዲዮ ፕሮግራምም ተደጋግማ በሕዝብ የምትመረጥ ” መናደድ ሲበዛ ያስቀኛል ” የምትል ታዋቂ ዘፈን ነበረችው ። ከስንኙ በጥቂቱ እንሆ መናደድ ሲበዛ ያስቀኛል፣ እንደው መናደዴ ይቆጨኛል፡፡ በነገራችን ላይ ጋሼ እሳቱ ነብሱ በሰላም ትረፍ፡፡ ይፋጃል እሳቱ የሚባል ልጅም አለው፡፡ አንድ ግሮሰሪም የቀድሞው እቴጌ መነን ት/ቤት አካባቢም እንደነበረው አስታውሳለሁ፡፡ አጼ ቴዎድሮስን አለጊዜው የተነሳ ንጉሥ ብለው ነጮች እንደሚጠሩአቸው ሁሉ እኔም የእሳቱ ተሰማ ” መናደድ ሲበዛ ያስቀኛል ” የምትለዋ ዘፈኑ አለጊዜዋ ቀድማ የተዘፈነች ትመስለኛለች ።

የአዲስ አበባ ሰዉም ተናዶ በሽቆ ጨርሶ ራሱን በአርምሞ ቆልፎ የተቀመጠና የሚያስቅ ነገር ብቻ ቢገኝ ብሎ በአይኑ የሚባጅ ምስኪን ይመስለኛል ።በቀድሞው ግዜ የስዩም ባሩዳን፣ አልቤ ሾው፣ ደረጄ ( የሶስቱም ነፍስ በሰላም ትረፍ) ፣ ዛሬ ተመልካች አጥቶ በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች የሚንከራተተው ልመንህ ታደሰ ቀልዶችና ቁምነገሮቻቸው የሰው ልጆች መንፈስን የሚያድሱ ነበሩ፡፡ ዛሬ ደግሞ የበእውቀቱ ካሣን ፣ የተስፋሁንን ፍራሽ አዳሽና የእሸቱን ኮሜዲ አለ በተባለበት ሁሉ ተጋፍቶ ቲኬት ገዝቶ ለአንድ ሰአት ስቆ የወር ብሽቀቱን አራግፎ እቤቱ የሚገባውም የትዬሌሌ ነው ። የምፈራው አንድ ቀን እነዚህ የሳቁ ባለቤቶች አንዱን የመንግሥት ወይም የሚሊታሪ ወፍራም ባለሥልጣን አሸማቀቁ ተብሎ የተከረቸሙ እንደሆን ይብላኝ ለአዱ ገነት ልጆች ። አዱ ገነት ድሮ ቀረ አትሉኝም፡፡ ዛሬ አዲስ አበባ የጎሰኞች መፈንጫ ከሆነች አመታት ተቆጠሩ፡፡ የአዲስ አበባ ልጆች ባይተዋር ሆነዋል፡፡

እንደኔ አይነቱ ከአዘቦቱ የብሽቀት ክልል ርቆ የሚኖር ባተሌ በዩቲዩብ መርጦ የሚያይ ብቻ ስለሆነ መሳቅም ማዘንም ምርጫው ነው ። ያም ሆኖ ግን ያገርና የወገን ጉዳይ ሆኖ የሚያስለቅሰውም ሆነ የሚያበሽቀው የዜና ናዳ አይስተውም ።

ሰሞኑን የምሰማው የእልቂት ዜና ግን ቢያንስ ለአንድ ሳምንት በአርምሞ ዘጋግቼ እንድቀመጥ አስገድዶኝ ነበር ። ግን ምን ያደርጋል በተለያዩ የሀገሬ ክፍሎችና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ጓደኞቼ በስልክ የሸሸሁትን እያወጉኝ ይባስ አንጀቴን አሳረሩኝ ። አንዳንዱ ደግሞ አጣርቶ ሰምቶ አጣርቶ አያወራ በነሱ ንዴት አርምሞየን አስፈረሰኝ ። 

ያሁኑ ገቢረ ዜና ደግሞ እንደ ዱሮው መናደዴ በዝቶ ወደ ሳቅ የሚለወጠው አልሆነም ። እርር ኩምትር የሚያደርግ እንጂ ። እና መናደድ ሲበዛ ማሳቁን ትቶ ማሳቀቁን በዛሬው ጊዜ በሰፊው ተያይዞታል። እና የቀረው በራስህ ቤት ራስህን መደበቅ ብቻ ሆኗል ። አልሰማም፣አላይም፣አልናገርም በማለት

ብቻ ። በራስ ቤት የመደበቅን ያህል ደግሞ አሰቃቂ ነገር የለም ። ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ በጣሊያን ጊዜ ቤታቸውን ለአንድ ጣሊያን አከራይተው ሆቴል ሲነግድበት ቆይቶ አንድ ቀን ነጋድራስ ኪራይም ለመቀበል ከሆቴሉም ለመቅመስ ብለው ወደ አከራዩት ቤታቻው ሊገቡ ሲሉ ጣልያኑ ሮጦ መጥቶ በዋናው በር ሳይሆን በጓሮ በር በኩል ሲያስገባቸው የዘር ልዩነት ጉዳይ መሆኑ ነጋድራስ ገባቸውና

ታሪኬ ብዙ ተሰማ እሸቴ

ተደብቄአለሁ በገዛ ቤቴ !

አሉ ይባላል ። እና ይኼ በገዛ ቤታችን መደበቅና መደባበቅ የዘር ውርስ አልሆነብንም ትላላችሁ ?

የኮሎኔል መንግሰቱ መንግስት  አገዛዝ ዘመን ኢትዮጵያዊ የወሎ ሰፋሪዎች ትዝታዬ

በ1981 አመተ ምህርት በአሶሳ ሆስፒታል ስሰራ በአሶሳ አካባቢና በደምቢ ዶሎ፣ጊምቢ፣ አሶሳ  ክልል ሰፋሪዎች በጠና ሲታመሙ አዲስ አበባ እና አሶሳ በመኪና ተጭነው በብዛት ይመጡ ነበር። አብዛኞቹ የወሎ ደገኞች በመሆናቸውና ምንም የጤና እቅድ በሌለበት ሁኔታ ቆላ ውስጥ ሲዘረግፏቸው በወባና በሌሎች የቆላ ወረርሺኞች በተለይ በአንጎል ወባ ፣ ተስቦና በመሳሰሉት በየቀኑ ይረግፉ ነበር። በተጨማሪም በመጀመሪያ ወደ ተጠቀሱት አካባቢዎችና እንደ ጊቤ ወንዝ አካባቢና ሌሎች ስፍራዎች እንደሰፈሩ የሚሰጣቸው ቀለብ ከሩሲያ በእርዳታ የሚመጣ ደረቅ ብስኩት ብቻ እንደነበር አንዳንድ ጥናቶች ያሳያሉ። ብስኩቱን ቀምሼው ነበር። ጣሙ ጥሩ አልነበረም፡፡ ከአንዳንድ ምሁራን የጥናት ወረቀቶች ላይ እንዳነበብኩት ከሆነ ለሁለተኛው የአለም ጦርነት ዝግጅት በብዛት ተፈብርኮ ሳይቤሪያ የበረዶ በርሀ ውስጥ ታምቆ የኖረና ለጤና አደገኛ ነበር ። ሰፋሪዎች ሲቸግራቸው ወቅጠው አቡክተው ለመብላት ቢሞክሩም ችግር ሆኖባቸው እንደነበር ሲነገር ሰምቻለሁ። 

በግዜው ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰፋሪዎች በበሽታ ምክንያት ህይወታቸው አልፎ ነበር። ነገር ግን ደርግ አጸፋውን በመመለስና ሰፋሪዎችን በማሰልጠንና በማስታጠቅ ሁኔታውን ተቆጣጥሮት ነበር። ደርግን በጭካኔውና በገዳይነቱ እንጂ በኢትዮጵያዊነትና በዘር አድላዊነት ልንከሰው አንችልም። ( በገራችን ላይ በደርግ ስርዓት ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያዊ ባለስልጣናት ሁሉ ወንጀለኞች አልነበሩም ለሀገራቸው እድገት ቅን የነበሩ፣ለኢትዮጵያ አንድነት ሲሉ ውድ ህይወታቸውን የሰዉ፣ የሚወዷትን ሀገራቸውን ጥለው ወደ ውጭ ሀገር የተሰደዱ ቁጥራቸው ቀላል አልነበረም፡፡ ከእነኚህ ውስጥ ኮሎኔል በላይ አስጨናቂ፣ኮሎኔል ታሪኩ አይኔ፣ኮሎኔል ካሳ ፣ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ፣ኮሎኔል ሀዲስ ተድላ፣አቶ ፋሲካ ሲደልል፣ አቶ ገብረጻዲቅ ፣ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ወዘተ ወዘተ  በመልካም ተግባራቸው ከሚጠቀሱት መሃከል ይገኛሉ) እነኚሁ የውሎ አማራ ኢትዮጵያዊ ወንድሞቻችን፣ እህቶቻችን፣ልጆቻችንና አባቶቻችን ያንን ሁሉ መከራ ችለውና ተርፈው የቀሩትን ምስኪኖች ነው አሁን በደም መሬት ወለጋ ጊምቢ፣ ደምቢዶሎ አካባቢ ከ40 አመት በኋላ የሚጨፈጭፏቸው። ኧረ እንተዛዘን!! ኧረ የመንግሥት ያለህ! አረ የሰው ያለህ / በነገራችን ላይ እነኚህ ኢትዮጵያዊ ወንድሞቻችን የሰፈሩት በኢትዮጵያ ምድር ወለጋ ላይ ነው፡፡ ወደ ሌላ ባእድ ሀገር አልነበረም፡፡ በሌሎች የአለም ሀገራት እንደሚሰራው ሁሉ በኢትዮጵያም የተደረገው ተመሳሳይ ነው፡፡ ድርቅና ጠኔ ከሚያጠቃው ከአንዱ የሀገሪቱ ክፍል  ወደ ሌላው ለም መሬት ያለበት የሀገር ክፍል ህዝብን ማስፈር የተለመደ ነው፡፡ ዛሬ በጎሳ ፖለቲካ ያበዱ የክንቱ ከንቱዎች እንደሚደሰኩሩት እነኚህ ወንድሞቻችን መጤዎች አይደሉም፡፡ የጎሳ አጥርን ያለፉት ስፓኞች ከደቡባዊ ስፔን ውሃ በመሳብ ደረቅ መሬት ላለው ደቡባዊ ስፓኝን አልምተው ህዝባቸውን ከመመገባቸው ባሻግር ወደ ውጭ ሀገር በመላክ ወደ እድገት ጎዳና ገስግሰዋል፡፡ ባልታደለችው ኢትዮጵያ የበቀሉ እንክርዳዶች ግን የገዛ ወንድሞቻቸውን መግደላቸው ሲታሰብ ልብን ያደማል፡፡ በአጭሩ እነኚህ በግፍ የተገደሉት የአማራ ተወላጆች መጤ ሳይሆኑ በኢትዮጵያ ምድር የሰፈሩ ኢትዮጵያዊ ወንድሞቻችን ናቸው፡፡

ህዝብን ማደራጀትና ማስተባበር ከብዙ ሰቆቃ ያድናል.

“ግለሰብም ይሁን ኢ-መደበኛ ኃይሎች በምንም መልክ ይሁን በምን ንጹሃን ዜጎችን ማረድ መግደል መጨፍጨፍ የጨፍጫፊዎች ስብእና የወረደ የዘቀጠ መሆኑንና አላማ ቢስ መሆናቸውን የሚያሳይ ድርጊት ነው። መንግስትን እና የመንግሥትን ሰርአት መቃወም ይቻላል ነገር ግን አይጥን ፈርቶ ዳዋውን” እንዲሉ ንፁሃን ዜጎችን ማረድ መግደል ለማንኛውም ቅሬታ መፍትሄ ሊያመጣ አይችልም።

በቤኒሻንጉል ክልልም ሆነ በኦሮሚያ ክልል በሚኖሩ በአማራ ተወለጆችም ይሁን በሌሎች ወገኖች ላይ በማንነታቸው በየጊዜው እየደረሰባቸው ያለው ኢሰብአዊ ድርጊት አሳዛኝ ቅስም ሰባሪ መሆኑ አያጠራጥርም። ይሁንና ለዚህ ችግር መፍትሔ የሚሆነው ባስቸኳይ በጥምር ወይም የጋራ አሰሳ በሶስቱ አጎራባች አሥተዳደሮች ማለትም #አማራ #ቤኒሻንጉልንና #ኦሮሚያ ክልልን አጠቃሎ በቅንጅት አሰሳ ቢካሄድ ሰው አራጆችን ለመመንጠርና ለመጠራረግ ይረዳል። 

ከዚያ ባሻገር ደግሞ የቀበሌ የሰላምና የህዝብ የደህንነት ጥበቃ ማደራጀት እና ህዝብ የራሱንና አካባቢውን ደህንነት በመጠበቅ ለችግሩ መፍትሔ ሊያመጣ ይችላል። የፀጥታ ኃይሎች ሰርጎ ገቦችን በየቦታው መቆጣጠር አይችሉም ዋናው የፀጥታው ባለቤት የአከባቢው ህዝብ ስለሆነ ህዝብን ማደራጀትና ማስተባበር ከብዙ ሰቆቃ ያድናል፡፡

እንደ መደምደሚያ

ተው ስማኝ አገሬ !
ወለጋ የኢትዮጵያ ግዛት እንጂ ጠፈር ውስጥ አይደለም የጭፍጨፋው ሚስጥር ካልገባህ ነገ ዕሩቅ አይደለምና የትም ክልል ብትገኝ ዕጣው ይደርስሃል 

 

Ethiopia Shall Prevail!!!

Filed in: Amharic