>

አገር ከሀዲው አገዛዝ ሱዳን በወረራ የያዘችውን መሬት እንደ ድንበር አስምሮ ለመስጠት ከስምምነት ላይ ደርሷል ...!?!? ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

አገር ከሀዲው አገዛዝ ሱዳን በወረራ የያዘችውን መሬት እንደ ድንበር አስምሮ ለመስጠት ከስምምነት ላይ ደርሷል …!?!?

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

አሸባሪው አገዛዝ በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ወሬ እና በእስልምና መጅሊስ መፈንቅለ ሥልጣን ግርግር አጀንዳዎች ተከልሎ የሠራንን ጉድ ሰማቹህ ወይ???

ታስታውሳላቹህ??? ሱዳን ድንበራችንን ጥሳ በመግባት ወረራ በፈጸመችብን ጊዜ ሱዳን ድንበራችንን አልፋ እንድትገባ እና መሬታችንን እንድትወር ያደረጋት እራሱ አገዛዙ መሆኑንና አገዛዙ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሱዳን ወረራ እንደተፈጸመብን ያላመለከተውም ለዚህ እንደሆነ ነግሬያቹህ ነበረ!!!

ሀገራችንን ያስወረረው ይሄው ከሀዲውና አሸባሪው አገዛዝ ያስወረረን እሱ እራሱ ነውና ወራሪውን የሱዳን ኃይል ምንም ሳይል እስከአሁን ቆይቶ ነበር፡፡ ከዛሬ ምሽት ዜና እንደሰማቹህት አገዛዙ ከሱዳን ጋር ሁለት ስምምነቶችን ማለትም 1ኛ. በመተማ ገላባት በኩል ያለው ድንበር እንዲከፈትና መንገዱ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን የሚለውንና 2ኛ. ሁለቱን ሀገራት የሚያዋስነውን ዓለም አቀፍ ድንበር በጋራ ለመጠበቅ መስማማታቸውን የሱዳን ከፍተኛ የጦር መኮንን በሀገሩ ቴሌቪዥን ላይ የሰጠውን መግለጫ በዋቢነት በማቅረብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አስከፊውን የክህደት መርዶ አርድቶናል!!!

ለመሆኑ በሱዳንና በሀገራችን መሀከል የተሰመረ ምን የዓለም አቀፍ የድንበር መስመር አለና ነው አገዛዙ ከሱዳን ጋር ይሄንን የድንበር መስመር በጋራ ለመጠበቅ የሚስማማው???

የሱዳኑ የጦር መኮንን “ሁለቱን ሀገራት የሚያገናኘው ዓለም አቀፍ ድንበር!” ሲል የገለጸው የቱን የድንበር መስመር እንደሆነ ገብቷቹሃል ወይ??? የሱዳኑ ከፍተኛ የጦር መኮንን “ሁለቱን ሀገራት የሚያገናኘው ዓለም አቀፍ የድንበር መስመር!” ሲል የገለጸው የድንበር መስመር ሱዳን “የሻለቃ ጎየን መስመር!” እያለች የምትጠቅሰውን የተጭበረበረ የድንበር መስመርን ማለትም አሁን ወርራ የያዘችብንን በስፋቱ አንዳንድ የአውሮፓ ሀገራትን የሚበልጠውን ሰፊ የሀገራችንን መሬት ወደ ሱዳን የሚያደርገውን መስመር ነው!!!

አሁንስ አገዛዙ ይሄንን ስምምነት መስማማቱን ያውም የሱዳንን ከፍተኛ የጦር መኮንን መግለጫ በማቅረብ ከመግለጡና ሱዳን “የሻለቃ ጎየን መስመር!” እያለች የምትገልጠውንና ብዙ የሀገራችንን መሬት ለሱዳን የሚሰጠውን የተጭበረበረና ሀገራችን በሰዓቱ ያልተስማማችበትን መስመር መቀበሉን ከማረጋገጡ የሀገራችንን መሬት ያስወረረው እሱ እራሱ መሆኑን ተረዳቹህ ወይ???

ብልጡ ወያኔ ይሄንን ያደረገው እሱ መሆኑ እንዳይታወቅና ከታሪክ ተወቃሽነት ለመሸሽ ለውጥና ሕግ የማስከበር ጦርነት የሚል ድራማ አምጥቶ የሸሸ በመምሰል ባለ አደራ ኩሊዎቹን እነ አቶ አቢይን ከጀርባ ሆኖ እየጋለበ እንዲህ እንዲያደርጉ በማድረግ በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ሱዳን ለዋለችለት የማይተካ ውለታ ቃል የገባላትን የሀገራችንን ሰፊ መሬት በኩሊዎቹ በእነ አቶ አቢይ በኩል ለሱዳን አስረክቧታል፡፡ አቶ ጌታቸው ረዳ ሰሞኑን “መሬቱ የሱዳን ነው፡፡ መንግሥት አስቀድሞ የወሰነበት ጉዳይ ነው!” እያለ ሲናገር ሰምታቹህታል አይደል???

የሚያፍር ሕሊና ካላቹህ ይሄንን የሀገር ክህደት የፈጸመብንን ወንበዴና አሸባሪ የወያኔ ኩሊ አገዛዝ “መንግሥቴ!” የምትሉ ደናቁርትና ዘገምተኞች እፈሩ!!!

አየ ሀገሬ! እነኝህ የእፉኝት ልጆች ብለው ብለው ለዚህ ውርደትና የክህደት ኪሳራ ዳርገውሽ አረፉት??? እጅግ በጣም ያሳዝናል!!!

Filed in: Amharic