“ከዚህ ‘ሰው’ ተማሩ”
ጌታቸው አበራ
እንደ መግቢያ
ይህ …፣ ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚድያ ላይ የሚዘዋወረውን የቴዎድሮስ አድኅኖምን ‘የወያኔ ቀለም ገዋን’ ፖለቲካ ካየሁ በኋላ የመጣልኝ ሃሳብ ነው። ሰውየው በየወቅቱ የሚያምንበትን ወያኔያዊ ተግባር በይፋ ለመፈጸም፣ በዓለም ጤና ድርጅት የያዘው ስራና ስልጣን አግዶት አያውቅም፤ እናም ‘ለኛ ሰዎች’ ይህቺን ማለት ወደድኩ…)
ዩ፣ ኤን፣ በመስራቱ – ምንም ሳያግደው ያለም ጤና አለቃ፣
ዘሬን ይዘርዝረኝ – ብሎ መንደር ወርዶ ሃኬቱን ሲያቦካ፣
ምንም ካልተባለ – ከልካይ ህግ ከሌለ…፤
ታዲያ! የኛዎቹ- የትልቋ አገር፣የኢትዮጵያ ልጆች እማትተነፍሱ፣
ምን ገዷችሁ ይሆን? ለአገር እማትጮሁ፣ ለህዝብ እማትደርሱ?!
..የኢትዮጵያ ምሁራን ባለም ላይ ያላችሁ፣
ለአገር ‘ላትጥሙ’-እንደ ጨው ዘር ብናኝ የተበተናችሁ፤
ለሰብአዊነት ለአገር ህልውና ተነሱ ታገሉ!
የእናቴ መቀነት ጠልፎኝ ነው ሳትሉ፤
ዩ ኤን… እምትሰሩ..፣
ዓለም ባንክ፣ አይ ኤም ኤፍ፣ ናሳ.. እምትሰሩ፣
ባለም ዩኒቨርሲቲ እምታስተምሩ..፣
ሰብሰብ በሉና መላ እስኪ ፍጠሩ፣
ሳትፈሩ፣ … “ሳታፍሩ”..!!
(የመንግስቱ ለማን “መርፌ” እስኪ ስሩ!)
ሐምሌ 2014 ዓ/ም
(ጁላይ 2022)