>

አዲስ አበባን ባሰብናት ጊዜ...! (አሳዬ ደርቤ)

አዲስ አበባን ባሰብናት ጊዜ…!

አሳዬ ደርቤ

 

አዲስ አበባ ትናንት

ማንነትን ሳትጠይቅ ዜጎችን በዜግነታቸው የምታኖር፤

➔ጉልበት ያለውን በጉልበቱ፣ የተሻለ የትምህርት ዝግጅት ያለውን በወረቀቱ፣ ብቃት ያለውን በብቃቱ የምትቀጥር

➔ከሌሎች ክልሎች የሚመጡ ዜጎችን ‹‹የክፍለ ሐገር ልጆች›› በሚል መጠሪያ ተቀብላ እርድናን የምታስተምር፤

➔ድሃውንም ሆነ ሐብታሙን በአቅሙ ልክ አብልታ የምታሳድር

➔‹‹በ97ቱ ምርጫ ድምጽ የነፈግኩት መንግሥት ምንም ቢሠራ አይጥመኝም›› እያለች የምትጎርር

➔‹‹ሰፈሬን እና ቤቴን ሰጥቼ ኮንዶሚንየም አልቀበልም›› በሚል አቋም ከመንግሥት ጋር የምትከራከር

➔ከኢትዮጵያም አልፋ የአፍሪካና የዓለም ከተማ ለመሆን የምትሞክር

➔በቻርተር የሚያስተዳድራትን ሥርዓት በዘረኛነት ፈርጃ ከግንቦት ሰባቶች ጋር የምታሤር

አዲስ አበባ ዛሬ

➔በክልል ሕገ መንግሥት የምትተዳደር

➔ለወለደቻቸው ልጆቿ ባዕድነትን የምታስተምር

➔መቶ ፐርሰንት ድምጿን በሠጠችው ዘረኛ መንግሥት አንገቷን ታንቃ የምታጣጥር

➔በዜግነት ማሰብን ተነፍጋ ማንነቷን ፍለጋ ዘር የምትቆጥር

➔ከእለት ጉርሷ ቀንሳ የሠራችው የጋራ መኖሪያ ቤት በቤተሰብ ሲከፋፈል እያየች ቁጭ ብላ የምታማርር

➔‹‹አገራዊ ለውጥ ያመጣል›› የሚል እምነት ካሳደረችበት መንግሥት የዲሞግራፊ ለውጥ ተቀብላ ልጆቿን የምታባርር፤

➔መኖሪያ ቤቷን ለቅቃ ወደ ኪራይ ቤት ካመራች በኋላ ‹‹ለማይረባ እቃ ይሄን ያህል ብር አልከፍልም›› እያለች ጫኚና አውራጅ ጋር የምትከራከር

➔አራዳ ልጆቿ ‹‹የሴተኛ አዳሪ ልጆች›› እና ‹‹ወራሪዎች›› ሲባሉ አፏን ከፍታ የምታዳምጥ

➔ከክልሎች በላቀ መልኩ በዘር ፖለቲካ የምትናጥ

➔ፍቅር በሠጠቻቸው መሪዎች ‹‹ጥላቻ አለብሽ›› እየተባለች የምትንጓጠጥ

➔‹‹ጥጋቤን እና ርሐብሺን ብቻ ሳይሆን ቋንቋየን መቻል አለብሽ›› በሚል አሀዳዊ ሥርዓት እንደ ሻሜት የምትናጥ

እናም እልኻለሁ…

ከዘረኝነት የጸዳችና የሁሉም የነበረች ከተማን በተረኝነት አስተሳሰብ ለማንም የማትሆን ከተማ በማድረግ ላይ የሚገኝ መንግሥት… ዜጎችን በዜግነታቸው የምታኖርና የሁሉም የሆነች አገር እውን ያደርጋል ብሎ ለማሰብ እንደነ ሲሳይ አጌና ሦስት ዓይና መሆን ይጠይቃል፡፡😆

Filed in: Amharic