>

አማራ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ጭፈጨፋ በመቃወም  በለንደን የረሃብ አድማ ተደረገ...!!! (ባልደራስ)

አማራ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ጭፈጨፋ በመቃወም  በለንደን የረሃብ አድማ ተደረገ…!!!

ባልደራስ

*… አምኒስቲ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ጠየቀ!!

በወለጋ ለተጨፈጨፍት አማራዎች በለንደን የረሃብ አድማ ተካሄደ። በምትመራው ስቶፕ-አማራ ጄኖሳይድ( Stop Amhara Genocide) ለሚጨፈጨፉት አማራዎች ድምፅ የሆነችውና የአማራ ግድያ በተባበሩት መንግሥታት በኩል በገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ እዲጣራ ግፊት እያደረግፕች ያለችው ዮዲት ጌድዮን በዚህ አዳማ ተሳታፊ ሆናለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣በኦሮሚያ በአማራ ተወላጆች ላይ በተፈጸመው ጭፍጨፋ  የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ገለልተኛ የሆነ ምርመራ እንዲያከናውኑ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠይቋል።

የመብት ተቆርቋሪው ድርጅት  ሐምሌ 14/2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ በምዕራብ ወለጋ፣ ጊምቢ ወረዳ፣ ቶሌ ቀበሌ ሰኔ 11/2014 ዓ.ም. በተፈጸመው ጭፍጨፋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን፣ እንዲሁም፣ በርካቶች መቁሰላቸውን ገልጿል።

“በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ተፈፅሟል የተባለው ግድያ፣ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ለሰው ሕይወት ያላቸውን ግድ የለሽነት ያሳየ ነው። ሴቶች እና ህጻናት ሕይወታቸውን ያጡበት ይህ አሰቃቂ ግድያ፣ ገለልተኛ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ መመርመር አለበት” ሲሉ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ዳይሬክተር ዴፕሮስ ሙቼና ተናግረዋል።

አክለውም፣ “የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እነዚህን ግድያዎች የፈጸሙ ግለሰቦች ለፍርድ እንዲቀርቡ እስከ መጨረሻው ድረስ ሊሄዱ ይገባል” ብለዋል።

በዚህም ጥቃት የጅምላ ግድያ፣ ቤቶች ማቃጠልና ዘረፋ ተፈፅሟል ብለዋል። በተጨማሪም፣ የአምነስቲ የምርመራ ቡድንም የሳተላይት ምስሎችን የመረመረ ሲሆን፣ ሰኔ 11/2014 ዓ.ም. በቶሌ ቀበሌ በሚገኙ መንደሮች ውስጥ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱንም አረጋግጧል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽንም በጥቃቱ ዙሪያ ምርመራ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

Filed in: Amharic