>

ዜና ትንግርት:- መከላከያ. ጋዜጠኛ ተመስገንን ከለቀቃችሁ “እርምጃ እወስድበታለሁ” አለ!!! (መስከረም አበራ)

ዜና ትንግርት:-

መከላከያ. ጋዜጠኛ ተመስገንን ከለቀቃችሁ “እርምጃ እወስድበታለሁ” አለ!!!

መስከረም አበራ

*… ጋዜጠኛ ተመስገን በዋስትና የሚለቀቅ ከሆነ መከላከያ ሠራዊት “እርምጃ እወስድበታለሁ” ማለቱን ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤት እንዳሳወቀ የጋዜጠኛው ጠበቃ ገለፁ!

ዜናውን ያወራው “VOA” ባይሆን ኖሮ ለማመን እቸገር ነበር! “ተመስገን ደሳለኝን ፍርድቤት በዋስ ለቆት ፅሁፍ መፃፉን እንዲቀጥል ከተደረገ የሃገራችን መከላከያ እኔ እርምጃ እወስድበታለሁ ብሏልና በዋስ እንዳትለቁት” ብሏል  የኢትዮጵያ አቃቤ ህግ ፤ ይህን የዘገበው ደግሞ “VOA” ነው፡፡ የሃገራችን መከላከያ በፍርድቤት ወንበር ተቀምጦ በምኒሽር ፍርድ ሊሰጥ መሆኑን የህግ አካል የሆነው አቃቤ ህግ ኮራ ብሎ በፍርድቤት ፊት ተናግሯል፡፡እዚህ ደርሰናል ጎበዝ!

በተያያዘ ዜና:- “ልጄን ሳላየው እንዳልሞት አደራ”

ተመስገን ደሳለኝ እናት

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ዛሬ ያሉበት ሁኔታ ይሄንን ይመስላል!!

“ልጄን ሳላየው እንዳልሞት አደራ” እያሉ ይገኛሉ!!

ሃያሉ እግዚያብሔር ምህረቱን ይላክሎት እናቴ።

Filed in: Amharic