>

ሀገሪቱ እውን መከላከያ ሀይል አላትን....??? (ቬሮኒካ መላኩ)

ሀገሪቱ እውን መከላከያ ሀይል አላትን….???

ቬሮኒካ መላኩ


ከሰሜን አማራ ፈርጥጦ ደቡብ አማራ ጫፍ ላይ ሒዶ የቆመውን ሰራዊት እንዴት ብለህ መከታ ነው ትለዋለህ፤ ወያኔ እየተቀናጣ የወሎ ከተሞችን ሲዘርፍ እርሱ በሀሴት ሲያለምጥ የነበረን ሀይል እንዴት ልመካበት እችላለሁ!

በአራቱ የወለጋ ዞኖች አማራዎች እንደ ጎመን ቅጠል ሲቀረደዱ ያልደረሰን መከላከያ ከወያኔ ዘመኑ መከላከያ እንዴት ለይቼ ላየው እችላለሁ፤

መሀል ሸዋ ደራ ዙሪያ የኦነግ መፈንጫ ሲሆን ዝም ብሎ የሚመለከትን ሀይል እንዴት ተከላካየ ብየ ልጥረው!! የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሸኔ እንደ አሸን የሚፈላበት መሆኑ እየታወቀ መከላከያ በአርምሞ ሲያየው እኔ ምን ልበል!?

የሀገር ዳር ድንበር እየጠበቀ ነው እንዳልል

1) ከሱማሊያ የተነሳ ታጣቂ 105 ኪሎሜትር ዘልቆ ገብቶ ወረራ ይፈፅማል!

2)ከደቡብ ሱዳን የተነሳ ታጣቂ 200 ኪሎሜትር ዘልቆ በመግባት የወርቅ ማዕድን ማምረቻን ይቆጣጠራል።

3)ሱዳን 50 ኪሎሜትር ድንበር ገፍታ ሀገራችን ከወረረች እነሆ ሁለት አመት ሊሆናት ነው!  ታዲያ ዬህ ሁሉ ዝም ተብሎ እየታየ ባለበት ሁኔታ መከላከያን እንዴት ልትተማመንበት ትችላለህ!

በርግጥ ስለመከላከያ ያቀረብኳቸው መረጃዎች ከአውድ ውጭ የምትረዱ ወዳጆቼ እንዳላችሁ ለመገንዘብ ችያለሁ፤ ስለመከላከያ ያቀረብኳቸው ክሪቲክሶች በሙሉ ተቋሙን እንዴት አድርገው እንዳፈረሱት ለማስረዳት እንጂ በቀና ልቦናው ለሀገር ህይወቱን የሚገብረውን ወታደር ክብር ዝቅ ለማድረግ ፈልጌ አይደለም፤

ግን ግን ማወቅ ያለብን ነገር መከላከያ ተቋሙ እንደተቋም አይቆጠርም፤ የኢህአዴግ ወታደር በስንት ጣሙ(ከእነድከመቶቹ)። ኢትዮጵያ ውስጥ በአለፉት  3 &4 አመታት ውስጥ ያልፈረሰ ተቋም የለም። ት/ሚ ፈርሷል የለም።  ተቋሙ ሆን ብሎ አንድ ትውልድ አማራ አጥፍቷል፤ አጥንቶ መፈተን ነውር ነው፤ መኮራረጅ ጌጥ ሁኗል!!

የፍትህ ተቋማቱ እንደምታያቸው ነው፤ አቃቢዎቻችንም ተጠርጣሪን ግለሰብ መከላከያ ስለሚገድለው አይፈታ ይታሰር የሚሉበት ጊዜ ላይ ደርሰናል!!

አልደከም የባስ ምን አደከማችሁ ያልፈረሰ ተቋም የለም፤ ይህ ሀቅ እወቁ!!!

NB፦የአማራ ፋኖ ላይ ሲዘምት ግን ይጠነክራል!

Filed in: Amharic