ለአማራ አዲስ-አበባ ከመግባት መንግስተ ሰማያት መግባት እየቀለለ መጥቷል ….!!!
አባግርሻ ራያ
አማራ ሆነህ ወደ አዲስ አበባ መጓዝ እጅግ ከባድ ሁኗል፤ የአዲስ አበባ መታወቂያ የሌለው እንዲሁም ኦሮሞኛ የማይናገር ሰው በግልፅ ወደ አዲስ አበባ መግባት አይችልም ተብሏል!! ይህ አሰራር ህጋዊ እስኪመስል ድረስ በግልፅ እየተፈፀመ ነው፤ ላለመጉላላት ጉቦ እየሰጡ የሚያልፉ ሰዎችም እንዳሉ ታውቋል!!!
አንድ ተጓዥ በግሉ የደረሰበትን ሲገልጽ:-
ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ላይ ነኝ” እኔ የነበርኩበትን አውቶቡስ ጨምሮ ሁለት የዋሊያ እና የኢትዮ ባሶች ከሰንዳፋ ወደ ደብረ ብርሃን እንዲመለሱ ተደርገዋል።
አንድ የአፋን ኦሮሞ ተናጋሪ የከሚሴ ሰው ከኦሮሞ ልዩ ሃይል ጋር ሲነጋገር ሰምቼው እጅግ ተለሳልሼ ኦሮሞ መስዬ ምን እያለህ ነው ስለው “እቃህን ያዝና ለብቻህ ቁም እሸኝሃለሁ ብሎኛል” ሲለኝ እሱ ጋር እንደ ልጅ ተያይዤ ጉዞዬን ቀጥያለሁ።
የአፋን ኦሮሞ ተናጋሪ የሆኑ የአማራ ክልል መታወቂያ የያዙ ሰዎች እንዲያልፉ በትህትና ይፈቀድላቸዋል።
መሪ አልባ ህዝብ!