>
5:33 pm - Saturday December 5, 0342

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የገዥው ፓርቲ ክንፍ ሆኗል...!!! (ጌጥዬ ያለው)

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የገዥው ፓርቲ ክንፍ ሆኗል…!!!

ጌጥዬ ያለው


*… አገዛዙ ባወጣለት የፕሮፖጋንዳ መርሃ ግብር መሰረት ምዕመናኑ እና የሃይማኖት አባቶች ፈጣሪያቸውን መቼ ማመስገን እንዳለባቸው በዝርዝር ሰዓት መድቦ አዝዟል። ሲጀመር እኛ ፈጣሪችንን የምናመሰግነው ሁልጊዜ፣ ሁልቦታ ነው። በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆነን ነው። ዓለማዊ ድፍርስርሶች አይቃኙንም። አሁን እየተሄደበት ያለው መንገድ ግን ከፈጣሪያችን ጋር የምንገናኝበት ጊዜም በወራሪው ኦሕዴድ-ብልፅግና ተወስኗ እየተሰጠን ይመስላል። በዚህ ከቀጠለ ‘ጧት የጸለየ ከሰዓት መጸለይ አይችልም’  ተብሎ እንደ ውሃ ቅጅ ወረፋ ሊወጣለት ነው።

አገዛዙ የሃይማኖት ተቋማትን መቼ መቀደስ፣ ማመስገን፣ መወረብ፣ መጸለይ ብሎም መቼ መጾም እና መግደፍ እንዳለባቸው የማዘዝ ሥልጣን የለውም። ሃይማኖትና መንግሥት የተለያዩ ናቸው የሚባለውም እዚህ ላይ ነው። ይህ የቀኖና እና ዶግማ ጉዳይ እንጂ የስተዳድር እንቶፈንቶ አይደለም። የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የጠቅላይ ሚንስትር ተብየውን ርኩስ ጥሪ መቀበሉ ቅዱሳንን ማርከስ ነው። አገዛዙ በሃይማኖት ቀኖና እና ዶግማ ጣልቃ እንዲገባ መፍቀድ ነው። ሥልጣኑም አይደለም።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሃይማኖቶች በአንድ ሀገር ውስጥ ሃይማኖቶች እንዴት በጋራ መኖር እንዳለባቸው አስተዳደራዊ ጉዳዮችን የሚመክር እንጂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መቼ መጸለይ እንዳለባት፣ መስጊዶች መቼ መከፈት እንዳለባቸው የማዘዝ ሥልጣን የለውም። ማመስገንም ሆነ ማዘን የየሃይማኖቶች የግል ጉዳይ ነው። በጉባኤ የሚወሰን አስተዳድራዊ አጀንዳ አይደለም።

በመሆኑም ተቋሙ ባወጣው የጊዜ ሰኔዳ ምዕመናን እና የሃይማኖት አባቶች አገዛዙ በደም የተጨማለቀ እጁን ከሃይማኖት ላይ እንዲያነሳ የተቃውሞ ሰልፍ መውጣት ነው ያለብን። መላዕክት ያነሱትን ሰይዝ ነው ማንሳት ያለብን። ይህ ካልሆነ ነገ ከዛሬ የከፋ ይሆናል!

https://www.facebook.com/541629952535552/posts/pfbid041PuxzzqYZbKvUuUAnw2XrMuX2SGQAcFhdWo9xVGRGjzHYZRqAVNBbBsS9RQBqe7l/

Filed in: Amharic