>

"የደስታችን ምንጭ ሜዳሊያው ብቻ ሳይሆን አትሌቶቻችን ኢትዮጵያን አሸናፊ ለማድረግ ያሳዩት ትብብርና ህብረት ነው"  ( ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ)

“የደስታችን ምንጭ ሜዳሊያው ብቻ ሳይሆን አትሌቶቻችን ኢትዮጵያን አሸናፊ ለማድረግ ያሳዩት ትብብርና ህብረት ነው”

 ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ

*… የትግራይ መንገድ እንዲከፈት … አትሌቶቻችን ከቤተሰቦቻቸው እንዲገናኙ …

*… አይክፋችሁ በበለጠ ድል እንክሳችኃለን…!!! ‘

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በብሔራዊ ቤተመንግስት የተናግረችው ፦

ኢትዮጵያ በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሜዳሊያ ብዛት ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በድል እንድታጠናቅቅ ያደረገው የአትሌቲክስ ቡድን ወደ ሀገሩ ገብቷል።

የአትሌቲክስ ቡድኑ ዛሬም በአዲስ አበባ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ እየተዘዋወረ ደማቅ አቀባበል እየተደረገለት ይገኛል።

ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ታሪክ በዓለም አደባባይ ስሟ በጉልህ እንዲነሳ፣ ሰንደቅ ዓላማዋ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ካደረጉ አንጋፋ አትሌቶች አንዱ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ነው።

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ለአትሌቶቹ እየተደረገ ባለው አቀባበል ተገኝቶ ለጋዜጠኞች በሰጠው አስተያየት፤ የአትሌቶቹ ድል ትልቅ ትርጉም እንዳለውና በተገኘው ውጤት ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ተናግሯል።

በተለይ ኢትዮጵያ ስሟ በጦርነትና በተለያዩ ችግሮች እየተነሳ ባለበት በዚህ ወቅት የአትሌቲክስ ቡድኑ የተቀዳጀው ድል፤ ኢትዮጵያ በአንድነትና በፅናት ፈተናዎቿን እንደምታሸንፍ ያሳየ ነው ብሏል።

በጥቅሉ ለተገኘው ድል የድሉ ባለቤቶችንም ፈጣሪንም ማመስገን እንደሚገባም አትሌት ኃይሌ ተናግሯል።

አትሌት ኃይሌ መላው ኢትዮጵያዊ በድሉ የተደሰተው ባገኘነው ወርቅ፣ ብርና ነሐስ ብቻ ሳይሆን፤ የአትሌቲክስ ቡድኑ አባላት በዓለም አደባባይ ባሳዩት ኢትዮጵያዊ አንድነትና ሕብረት ነው ይላል።

አትሌቶቹ ያሳዩትን አንድነት፣ ሕብረትና ትብብር በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመድገም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለእናት ሀገሩ ሰላምና ልማት በአንድነት ሊነሳ እንደሚገባም አስገንዝቧል።

”ይህን ትብብር ወደ ፖለቲካው፣ወደ ኢኮኖሚውና ለሌሎች በጎ ነገሮች በማዋል ኢትዮጵያ ፍቅርና አንድነት የሰፈነባት ሀገር ማድረግ ይገባል” ብሏል።

ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው አራት የወርቅ፣ አራት የብርና ሁለት የነሐስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ታሪካዊ ድል አስመዝግባለች።

‘ አይክፋችሁ እንክሳችኃለን ‘

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በብሔራዊ ቤተመንግስት የተናግረችው ፦

የትግራይ መንገድ እንዲከፈት …

| “ይሄ ደስታችን ሙሉ እንዲሆን፣ የትግራይ መንገድ እንዲከፈት እና መሰረተ ልማቶቹ ተለቀዉ እነዚህ የትግራይ አትሌቶቻችን ከቤተሰቦቻቸዉ ጋር እንዲገናኙ፣ እንዲሁም በትግራይ የሚገኙ አትሌቶቻችንን አግኝተን በ ቡዳፔስት (Budapest) ለሚደረገዉ ዉድድር እንድንዘጋጅ መንግስት እጠይቃለሁ!”

….

” … ቶክዮ እኔ ውጭ ሀገር መኖር ሆነ መጥፋት አስቤው አላውቅም፤ ከመጀመሪያው ጀምሮ። የዛሬ ዓመት ግን መጥፋትም አስቤ ነበር፤ በጣምም ከፍቶኝ ነበር።

አንገታችንን ቀና አድርገን እንድንመጣ እነ ሰለሞን ባረጋ እና ሌሎችም ናችው ጥሩ ድጋፍ ያደረጋችሁልን።

ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በሚወደው 5 ሺ እና 10 ሺህ ውድድር ውጤት አላገኘንም። በእርግጠኝነት የዛሬ ዓመት እና የዛሬ ሁለት እንክሳችኋለን አይክፋችሁ።

እነ ሰለሞንም ሞራላችሁ አይነካ እንወዳችኃለን፤ ወርቆቻችን ናችሁ።

በስፖርቱ ቤተሰብ ፊት ቆሜ ቃል ገባላችኋለሁ። የምንወደው እና የምንፈልገው ዘንድሮ ያጣነው ውጤት ይመጣል። ተስፋ አደርጋለሁ እንሰራለን ከሰራን እናመጣዋለን”

አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ

Filed in: Amharic