>

ስንታየሁ ቸኮል ቤተሰቦቹ እንዳይጠይቁት መከልከሉን ለፍርድ ቤቱ ተናገረ...!!!

ስንታየሁ ቸኮል ቤተሰቦቹ እንዳይጠይቁት መከልከሉን ለፍርድ ቤቱ ተናገረ…!!!

በእስር ላይ በሚገኝበት የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ውስጥ ቤተሰቦቹ፣ የትግል አጋሮቹ እና ሌሎች ወዳጆቹ እንዳይጠይቁት በተደጋጋሚ እየተከለከሉ መሆኑን አቶ ስንታየሁ ዛሬ ሀሙስ ሀምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ለተሰየመው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ተናግሯል። ፖሊስ በጉዳዩ ላይ መልስ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ለሀምሌ 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ቀጥሯል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በስንታየሁ ላይ በሀሰት የተከፈተው የምርመራ መዝገብ ለነሐሴ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ተቀጥሯል። ምስክሮችን እያፈላለገ እንደሆነ የገለፀው መርማሪ ፖሊስ በእስካሁኑ ምርመራው አመርቂ ማስረጃ አለማግኘቱን ገልጿል።

ችሎቱ ስንታየሁ በአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲከራከር ቆይቶ በዋስትና የተሰናበተበትን መዝገብ ከአዲሱ መዝገብ ጋር ያለውን ተመሳስሎ እየገመገመ ይገኛል።

Filed in: Amharic