>

ስዊድን ለኢትዮጵያ መንግሥት የምታደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ልታቋርጥ መሆኑን አሳወቀች...!!! ባልደራስ

ስዊድን ለኢትዮጵያ መንግሥት የምታደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ልታቋርጥ መሆኑን አሳወቀች…!!!

ባልደራስ

 

በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን የዘር ፍጅት በመቃዎም የስዊድን መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት እያደረገ ያለውን የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያቋርጥ አስታውቋል። የሰብዓዊ ድጋፉን ብቻ እንደሚቀጥል የገለፀው የሀገሪቱ መንግሥት ይህንን ድጋፍም የሚያደርገው በአብይ አሕመድ መንግሥት በኩል ሳይሆን በዓለም የተራድዖ ድርጅቶች በኩል መሆኑን አስታውቋል። በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለው የዘር ማጥፋት ወንጀል በአውሮፓ ሕብረት እንዲታይ ስዊድን ጥረት እንደምታደርግም የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትርና ከፍተኛ ባለስልጣናት ገልጸው ይኸው ጥረት በሂደት ላይ መሆኑ ታውቋል።

ስዊድን ይህንን ርምጃ እንደምትወስድ የተገለፀው በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያውን፤ በኢትዮጵያ በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጅምላ ጭፍጨፋ በሰነዶች አስደግፈው አቅርበው ሲያበቁ ሁኔታው ከተጣራ በኋላ ነው።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾቹ ኢትዮጵያውያን ወንድማገኝ እጅጉ፣ አሕመድ አሊ፣ ናኩራ ኤፍሬም፣  ትዕግሥት መልሳቸው (ዶ/ር)፣ ኤልያስ አባይነህ፣ ይልማ ሺኩር ለስዊደን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰነዱን እና ማብራሪያውን ባቀረቡ በጥቂት ቀናት ልዩነት ነው ከላይ የተገለፀውን ውሳኔ የሀገሪቱ መንግሥት የወሰነው።

ኢትዮጵያውያኑ ከዚህ ቀደምም በኢትዮጵያ እየተፈፀመ ስላለው ብሔር ተኮር የመብቶች ረገጣ እና ግድያ ለስዊድን የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ማሳወቃቸው ይታወሳል።

Filed in: Amharic