>
5:13 pm - Sunday April 19, 0240

ባልደራስ ጠቅላላ ጉባኤውን በአንድ ወር ማራዘሙን አስታወቀ...!!! (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

ባልደራስ ጠቅላላ ጉባኤውን በአንድ ወር ማራዘሙን አስታወቀ…!!!

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር


ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከ12 ቀናት በኋላ ሊያካሄደው የነበረውን ጠቅላላ ጉባኤ ወደ መስከረም ወር አራዘመ። ፓርቲው የጠቅላላ ጉባኤውን መራዘም ይፋ ያደረገው ትላንት ሰኞ ነሐሴ 9፤ 2014 በጽህፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

በመግለጫው ላይ ከተገኙት የባልደራስ አመራሮች አንዱ የሆኑት የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ “ነሐሴ 22 ብለን ይዘነው ነበር፤ ያልተሟሉ ነገሮች ስላሉ ከነሐሴ 22 ትንሽ እናራዝመዋለን” ሲሉ ተናግረዋል። ዶ/ር በቃሉ ጠቅላላ ጉባኤውን ለማካሄድ “ያልተሟሉ ነገሮች አሉ” ቢሉም ጉዳዮቹ ምን እንደሆኑ ግን አልጠቀሱም። ሆኖም ጉባኤው በመስከረም ወር እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

ባልደራስ በመጪው ጠቅላላ ጉባኤው፤ ከክልላዊ ፓርቲነት ወደ ሀገር አቀፍ ፓርቲነት የሚሳድገውን ውሳኔ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። በቅርቡ ከፓርቲው ፕሬዝዳንትነት መልቀቃቸውን ባስታወቁት አቶ እስክንድር ነጋ ምትክ ፓርቲውን የሚመራ ፕሬዝዳንት  የሚመረጠውም በዚሁ ጠቅላላ ጉባኤ ነው። የባልደራስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ “ከጠቅላላ ጉባኤው በኋላ ሰፋ ያለ ሽግሽግ ይኖራል” ሲሉ ከመስከረሙ ጉባኤ በኋላ በፓርቲው ውስጥ ጉልህ ለውጦች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/7678/

Filed in: Amharic