>
5:13 pm - Saturday April 19, 5141

ለወገን ጦር -እንቅፋት ፥ ለአሸባሪው ኃይል -ብርታት የሆኑ  የብልጽግና የጦር ሕግጋት...!!! (አሳዬ ደርቤ)

ለወገን ጦር -እንቅፋት ፥ ለአሸባሪው ኃይል -ብርታት የሆኑ  የብልጽግና የጦር ሕግጋት…!!!

አሳዬ ደርቤ

➔ጠላት ሲተኩስ አጸፋ መልስ። ክላሹን ተንተርሶ ሲተኛ ግን ልትጠብቀው እንጂ ልታጠቃው አይገባም።

➔የጠላት ጦር ጥቃት በከፈተበት ግንባር ተገኝቶ ከመመከት ውጭ በሌላ ግንባር ጥቃት መሰንዘር አይፈቀድም።

➔ሕዝብን ሊያፈናቅልና ንጹሐንን ሊገድል ድንበር አልፎ የሚመጣን ጠላት ምታው። መፈርጠጥ ሲጀምር ግን በክብር ልትሸኘው እንጂ ልትከተለው አይገባም።

➔ጠላት በየትኛውም ጊዜ ወደ አፋርና አማራ ክልል ዘልቆ ወረራ ሊፈጽም ይችላል። የወገን ጦር ግን ወራሪን ጠራርጎ ከማስወጣት ባለፈ ድንበር አልፎ መዋጋት አይችልም።

➔የወገን ጦር በጠላት የትግል ሰሌዳ ከመንቀሳቀስ ውጭ የእራሱን እቅድ አዘጋጅቶ ያልታሰበ ጥቃት መሰንዘር አይፈድለትም።

➔አሸባሪ ሃይል የወንበርና የሸገር ሥጋት መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት መሸጋገር አይቻልም።

➔አሸባሪው ቡድን ሲጠነክር የጎረቤት ክልሎችን ሊያወድም ይችላል። የጠላት ጦር ሲዳከም ግን እስኪያገግም መጠበቅ እንጂ የተከበረውን ወራሪ ወርሮ ህልውናውን ማክሰም አይፈቀድም።

➔ከአሸባሪዎች ጋር በሚደረግ ጦርነት ውስጥ በየዓመቱ ጠንክሮ መታገል እንጂ ድል ማድረግ አይፈቀድም።

Filed in: Amharic