>
5:13 pm - Monday April 20, 6691

*† ቅዱስ ፓትርያርኩ ለቤተክርስቲያንና ለሕዝብ ታምነዋል....!!! (መ/ር ታሪኩ አበራ/ አባይ ነህ ካሴ)

*† ቅዱስ ፓትርያርኩ ለቤተክርስቲያንና ለሕዝብ ታምነዋል….!!!

መ/ር ታሪኩ አበራ/ አባይ ነህ ካሴ

*….  መቅረት እንኳን ባይችሉ ጳጳሳትን ሹመውልን ይሄዱ?” ቢሏቸውም በእኔ ዘመን እና በዚህ ዕድሜዬ ቤተክርስቲያንን ለሁለት አልከፍልም!!! ብለው አሳፍረው መልሰዋቸዋል!

* … ቅዱስነታቸው ወደ ሀገር ቤት ይመለሳሉ ሲባል የተጨነቀው አካል ቤተ ክህነቱን ይረብሸው ይዟል። አቀባበል ለማድረግ ኃላፊነት የተሰጣቸውን እነ ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬን አስረዋቸዋል!

ለ4ኛ ጊዜ የተላከው ሽምግልና አልሠራም ቅዱስነታቸው ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ “እሺ መቅረት እንኳን ባይችሉ ጳጳሳትን ሹመውልን ይሄዱ”? ብለው ሊያታልሏቸው ሞከሩ እሳቸው ግን አይ በእኔ ዘመን እና በዚህ ዕድሜዬ ቤተክርስቲያንን ለሁለት አልከፍልም ። እናንተም ቤተክርስቲያንን አክብሩ ለሚያልፍ ችግር የማያልፍ መከራ ቤተክርስቲያን ላይ አንትከል አሁን ወደ መጣችሁበት ተመለሱ አሏቸው።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ቤተክርስቲያንን ለሁለት እንዲከፍሉ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ሞቴን ያስቀድመው እንጂ ቤተክርስቲያን ድጋሚ አትከፈልም ብለው በአቋማቸው ጸንተው ቤተክርስቲያንን አስከብረዋል።ሁላችን ልናከብራቸው ይገባል።ኢትዮጵያ ሲገቡም በክብር እንቀበላቸው።

ቅዱስ ፓትርያርኩ በዚህ የአቋም ጽናታቸው ከውስጥ የሚገፏቸውን የብልጽግና ተላላኪ ቅጥረኛ ባንዳዎች አንገት አስደፍተዋል፤ ከውጪም ሆነው እያባበሉ የሚጎትቷቸውን የቤተክርስቲያንና የሃገር ገነጣጣዮችን አንገት አስደፍተው ተስፋ አስቆርጠዋል።ለቤተክርስቲያን ክብር በጽናት መታገል ማለት ይሄ ነው።

*በተያያዘ ዜና*

ቅዱስነታቸው ወደ ሀገር ቤት ይመለሳሉ ሲባል የተጨነቀው አካል ቤተ ክህነቱን ይረብሸው ይዟል። አቀባበል ለማድረግ ኃላፊነት የተሰጣቸውን እነ ሊቀ ማዕምራን ፋንታሁን ሙጬን አስረዋቸዋል።

የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው እስክንድር ገ/ክርስቶስ ከታሰሩት መኻል ተፈትቷል። የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት አገልጋዮችን ደኅንነቶች ሊያስራቸው ወደ ቤተ ክህነት ቢመላለሱም አልተሳካላቸውም።

ምክንያቱም የእስር ማዘዣ ያላመጣ አካል ወደ ግቢ እንዳይገባ ቆፍጣናው ሥራ አስኪያጅ ስላዘዙ። የእስር ማዘዣ የያዘም በቅድሚያ ኃላፊዎችን ሳያነጋግር በቀጥታ ወደ ታሳሪዎች እንዳይሔድ አዝዘዋል።

ሊታሰሩ የተፈለጉት:-

፩. መልአከ ሕይወት አባ ኃይለ ገብርኤል  ነጋሽ የልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ፣

፪. መልአገነት አባ ኪዳነ ማርያም ደስታ አቡነ ቀሲስ፣

፫. መምህር ሙሴ ኃይሉ የፓትርያርኩ ልዩ ተጠሪ ፕሮቶኮል፣

፬. መምህር ልሣነ ወርቅ ደስታ ገብረሕይወት  የልዩ ጽ/ቤት ጉዳይ አስፈጻሚ፣

፭. መልአከ ሰላም አባ ኪሮስ ወልደ አብ ካሜራ ማን፣

፮. አባ ተስፋ ሥላሴ ዘርአይ ናቸው።

አቡነ አብርሃም እና አቡነ ጴጥሮስ የታሰሩትን እነ ፋንታሁን ሙጬን እና ኤልያስ ተጫነን ጣቢያ ድረስ ወርደው ጠይቀዋቸዋል። አቡነ አብርሃም ከባሕር ዳር እንደገቡ በቀጥታ ነበር ወደ ጣቢያው ያቀኑት። እንዲህ እንጅ አባትነት። እግዚአብሔር ያሰንብትልን!

የታሰሩት በአስቸኳይ ይፈቱ ዘንድ እናሳስባለን።

ሲወጡ ጭንቅ ሲመለሱ ጭንቅ።

Filed in: Amharic