>
5:09 pm - Friday March 2, 8029

የህውሃት 10  በደሎች በተለይ በአማራ ህዝብ ላይ...!!!  (ዘላለም ጥላሁን)

የህውሃት 10  በደሎች በተለይ በአማራ ህዝብ ላይ…!!!

 ዘላለም ጥላሁን


➲”ህውሃት”…(ትግራይ/ተጋሩ አላልሁም) የተሸነፈው በ1967 ነው። ማንም ቡድን ወይም ርዕዮተ አለም ህዝብን ጠላት አድርጎ ማሸነፍ አይችልም። ግለሰቦች፣ የፊውዳሉ ስርዓት ጠላት ሊሆን ይችላል። ሁሉም አማራ ግን ጠላት ሊሆን አይችልም። ህውሃት እንጂ የትግራይ ህዝብ ጠላት እንዳልሆነው ሁሉ።

➲የህውሃት መሠረታዊ ትርክት (ድርሰት) በገሃድ የተተወነው ባለፈው ዓመት ነው። ህውሃት በተለይ በአማራ ህዝብ 10 አበይት በደሎች ፈፅሟል። በእኔ ሚዛንና ምልከታ።

1ኛ) መልክዓምድራዊ_ለውጥ (Demographic Change):-

ድህረ 1983 ማንነትን ባላገናዘበ መልኩ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ዋግና ራያ ላይ መሬቱን በመውረር ሰዎችን አፈናቅሎል፣ ጅምላ ግድያ ፈፅሟል። ሴቶችን በመድፈርና አስገድዶ በማግባት የዲሞግራፊ ለውጥ እንዲመጣ አድርጓል (ይሄን ከ10 ዓመት በፊት ወልቃይት ላይ ያናገርኋቸውን ሴቶች ዋቢ አደርጋለሁ)

2) የሞራል_ስብራት:-

አማራ የተባለ ዘር ሁሉ በሄደበት ሁሉ እንደ ጠላት፣ እንደ ክፉ፣ እንደ ትምክህተኛና ጨቋኝ እንዲታይ በማድረግ እንዲገለል፣ እንዲሳደድ ማድረግ። በዚያው ሰርቶ እንዳይበላ፣ በሀገሩ እንዳይኮራ በማድረግ የሞራል ስብራት እንዲርስበት ማድረግ። ከዚህ ባለፈም “አማራ አድግ-አሜራ አህያ” የሚሉ ክብረ ነክ ስድቦችን ከትግሉ ጀምሮ ይጠቀማል። ባለፈው አመትም አጣዬ ቴ/ሙያ ተቋም ስገባ ያገኘሂት ይሄን ስድብ ነው። “አማራ ሰው ሆነህ ከምትፈጠር፣ ትግራይ እቃ ሆነህ ብትፈጠር ይሻላል” የሚለውም ኮምቦልቻ ቴ/ተቋም ያገኘነው ነው።

3) የህዝብ_እድገቱን መቀነስ: እዚህ በማልጠቅሳቸው መጠነ ሰፊና ድብቅ በሆኑ መንገዶች የህዝብ ምጣኔውን መቀነስ ዋነኛ መንገድ ነበር። ተሳክቶላቸዋል።

4) #ጅምላ_ግድያ (Genocide):

ለ27 ዓመታት በወልቃይትና በሌሎች ቦታዎች ባለፈው አመት ደግሞ በገቡበት የአማራ ክልል ሁሉ ጅምላ ግድያ ፈፅመዋል። ቤተሰቡ በሙሉ ወደ አመድነት የተቀየረባቸውን የሐይቅና የዋድላ የተወሰኑ ቤቶችን አይቻለሁ። አመድ የሆነ የሰው አፅም በእጆቼ ዳብሻለሁ። የእንስሳትንም እንዲሁ። የገረመኝ ግን የጋይንት ህዝብ አመድ ለሆኑ እንስሳት እንኳን ቀብር ፈፅሟል

5) #ሳይንሳዊ_ጦርነት (Bioterrorism):’

ህውሃት ባለፈው ዓመት በየሆስፒታሎችና በደሴ መድሃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ የሚገኘውን የፖሊዮ ክትባት በባለሙያ በታገዘ መልኩ ወደ አፈርና የእርሻ ቦታዎች ደፍተውታል። ይሄን እኔው ራሴ በወሎ ሆስፒታልችና በአቅራቢ ኤጀንሲው በአካል አረጋግጫለሁ።

በእነዚህ አካባቢዎች በቀጣይ 5-10 ዓመታት የፖሊዮ ወረርሽኝ ስጋት ሊኖር ይችላል።  ከአሁኑ ማሰብ ያስፈልጋል። ህውሃት አመታትን አስቦ የሚሰራ ክፉ ድርጅት ነው።

6) ረሃብ: ህውሃት የአማራ ህዝብ በድህነት እንዲማቅቅ ብዙ ስራ ሰርቷል።

በማዳበሪያ ሰቨቭ መሬቱ ላይ ያደረሱትን “Natural Fertility Genocide” ባለሙያዎች ብዙ ያሉት ስለሆነ ልተወው። ባለፈው አመት በአማራ ክልል ለገበሬ ዘር የሚያቀርበውን የደሴ ቲሹ ካልቸር ማዕከል ያደረጉትን አይቻለሁ። 500,000 የዘር ማሳደጊያ ባልዲዎችን እንዴት እንዳደረጉ ምስሉን ተመልከቱ። ፅናታቸው። ትጋታቸው ይገርማል። የቆቦ ጊራና  የገበሬው ፕሮጀክት ላይ የከርሰ ምድር ማውጫ የኤሌክትሪክ ስቴሽኖችን በመድፍ መተዋቸዋል። የንብ ማራቢያ ጣቢያዎችን በሳት አቃጥለዋቸዋል። ሲሪኒንቃ ለወሬ ነጋሪ አልቀረም። ለራሴ እንዴት ሰው በዚህ መጠን ይከፋል? እያለሁ እተክዝ ነበር። ጉዳዩ ግን የአማራን ህዝብ በረሃብ የመጨረስ አንዱ መንገድ ነው። ምቀኝነት።

7) ትውልዱን_ማምከን: – በኢህአዴግ/ህውሃት ዘመን በአማራ ያሉ ት/ቤቶች፣ የህክምና ተቋማት ጉዳይ የሚታወቅ ነው። ምንም እንኳ አሁንም ከዚያው ፈቀቅ ባይልም። ባለፈው አመት ህውሃት በትምህርት ቤቶችና በጤና ተቋማት የጨከነው ጭካኔ፣ አንድም በበሽታ ሌላም ትውልዱን በትምህርት ተስፋ መቁረጥ የማምከን አንዱ መንገድ ነው።

8) #ማህበራዊ/ሃይማኖታዊ እሴትን መስበር!

ወሎ አንድ ከተማ ውስጥ አባትን ከልጅህ ጋር ካልተኛህ ብለው በቤተሰብ መሃል ጥይት ደቅነውበት ነበር። ዝርዝሩ ያማል። በባል ፊት ነፍሰጡር ሚስቱን ለመድፈር ሲታገሉ፣ እባካችሁ ልጄ አለችላችሁ ብሎ የለመነውን አባት እንዴት እረሳዋለሁ? ጋይንት በተደፈሩ ማግስት ልጅ ወልደው ታቅፈው ያገኘኋቸውን እናቶች፣ ተዟዙሬ ያናገርኋቸውን 16 እንስቶች የአንገት ስብራት በምን እገልፀዋለሁ? የጋይንቱን የ8 ዓመት የአእምሮ ዘገምተኛ ልጅ (አንድ ጥይት በጭኑ አንድ ጥይት በጫንቃው ተመቶ) የተረፈውን እንዴት እረሳዋለሁ?

“እባካችሁ ልጄን ተውልኝ፣ ሌላ ሰው የለኝም” በማለቱ የገደሉትን የዋድላውን አይነስውር፣ ጫካ ወስደው ደፍረው ከሳምንት በኋላ የመለሷትን መሪውን ልጁን እንዴት መርሳት ይቻላል። ግብረሰዶም የተፈፀመበት የ9 ዓመቱ ልጅስ? የመነኮሳቱ ጉዳይስ? የቱን አንስቼ የቱን ልተወው። ህውሃት ያላፈረሰው የሀይማኖት ህግ፣ ያላቆሸሸው ማህበራዊ ወግ የለም።

9) #አለም_አቀፍ_ህግጋትን_መጣስ!፡ አይነኬ የሆኑ ሃይማኖታዊና የህዝብ ተቋማትን አውድሟል፣ ደፍሯል። አለምአቀፋዊ ግብረሰናይ ድርጅቶችን ለጦርነት ተጠቅሟል። ለአብነት የአለም ምግብ ፕሮግራም አልሚ ምግቦችንና ዱቄት ለጦርነት ተጠቅሟል። መኪኖችን ለውጊያ ተጠቅሟል።

10) #ማህበረሰባዊ_መተማመንን (Social Capital)  መሸርሸር:

የአማራ ህዝብ አብሮ ተዛምዶ፣ ተዋልዶና ተጎራብቶ ከኖራቸው የትግሬኛ ተናጋሪ ወገኖቹ ጋር በጥርጣሬና በጥላቻ እንዲተያይ አድርጓል። አስርጎ እያስገባም ብዙ ማህበረሰባዊ መናጋቶች ፈጥሯል።

በአጠቃላይ ህውሃት ፈጣሪ ኢትዮጵያን ሊቀጣ አስቦ ወደ ጥልቁ ከተጣሉት ከሳጥናኤል ነገዶች መካከል መርጦ ያመጣው የጉግማንጉግ ስብስብ ነው።  ህውሃትን ለማጥፋት የሚደረግ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ነው። ችግሩ ግን ከኑግ ጋር ያለች ሰሊጥ መሆኑ ነው። የትግራይን ወጣት በርዕዮተ አለምና በዕፅ በማደንዘዝ በእሳት አስጨረሰው። ደጋግ የትግራይ አዛውንቶችን የመከራ ማሳ አደረጋቸው።

ያም ሆነ ይህ ህውሃት ከምድረገፅ ካልተሰረዘ፣ በቀዳሚነት የአማራ ቀጥሎ የኢትዮጵያ ጉዳይ አደጋ ላይ ነው። የትግራይ ህዝብ መከራም በባሰ መንገድ ይቀጥላል።

Filed in: Amharic