ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ዛሬ ማለዳ በፌደራል ፖሊስ የደህንነት ሰዎች ተወስዶ ታርስሯል።
አዲስ ስታንደርድ
*… ለአንድ ሰዓት የቆየ ብርበራ በቤቱ ውስጥ የፈጸሙ ሲሆን በዚህም የእጅ ስልኩንና የባንክ ደብተሮችን ጨምሮ የተለያዩ የግል መገልገያ ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን ወስደዋል”
የአማራ ድምጽ የብይነ መረብ ሚዲያ ባለቤትና ምስራች ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ዛሬ ማለዳ 2 ሰዓት ላይ የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱና ሲቪል በለበሱ የደህንነት ሰዎች መያዙን ወንድሙ አቶ ከድር ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።
እንደ አቶ ከድር ገለፃ “የጸጥታ አካላቱ
ለአንድ ሰዓት የቆየ ብርበራ በቤቱ ውስጥ የፈጸሙ ሲሆን በዚህም የእጅ ስልኩንና የባንክ ደብተሮችን ጨምሮ የተለያዩ የግል መገልገያ ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን ወስደዋል” ብለዋል።
ጋዜጠኛ ጎበዜ የተያዘው የፍርድ ቤት ማዘዣ ባልያዙ የደንብ ልብስ የለበሱ እና ያልለበሱ የጸጥታ ሃይሎች መሆኑን ገልጸው በትክክል ወዴት ጋዜጠኛውን እንደወሰዱት ባያውቁም የጸጥታ አካላቱ “አዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ ወደሚገኘው ጣቢያ እየወሰድነው ነው” ብለውኛል ሲሉ ለዜና ክፍላችን ተናግረዋል፡፡