>

"ቅዱስነታቸው ቤተክርስቲያንን ታድገዋታል"  (ብፁዕ አቡነ አብርሃም)

“ቅዱስነታቸው ቤተክርስቲያንን ታድገዋታል”++

❖❖❖

            ( ብፁዕ አቡነ አብርሃም )

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከአንድ ወር በላይ ለህክምና ከሄዱበት ሀገረ አሜሪካ ዛሬ ንጋት ላይ ወደሀገራቸው እና መንበረ ክብራቸው ተመለስዋል።

በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በተካሔደው የአቀባበል መርሐ ግብር ላይ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል ፦

* የቅዱስነታቸው ለህክምና ወደ አሜሪካን ሀገር  መሔዳቸውን ተከትሎ  በስፋት መነጋገሪያ የነበሩ ጉዳዮች  ሁሉ በቅዱስነታቸው ወደ መንበረ ክብራቸው መመለስ አክትመዋል። ይህም እጅጉን አስደሳች ከመሆኑም በላይ የቤተክርስቲያንን አንድነት በማስጠበቅ  ረገድ  ያለው ሚና ጉልህ ነው።

*ለህክምና በሄዱ ጊዜ ከወቅቱ የአየር ፀባይ አንጻር ብዙ ተፈትነን ነበር፤ ነገር ግን ቅዱስነትዎ ያን ሁሉ ወጀብ ወደጎን ብለው ወደ መንበረ ክብርዎ በመመለስዎ ቤተክርስቲያንን ለሁለተኛ ጊዜ ታድገዋታል ።

*የህክምና ጉዞዎን ተከትሎ ከውጭ ሳቢ ከውስጥ ገፊ  የነበረብዎ  ቅዱስነትዎ  ፈተናውን ተቋቁመው በተቀመጠው ጊዜ ህክምናዎን አጠናቀው ወደ አገርዎና መንበረ ክብርዎ በመመለስዎ ደስታችን ወደር የለውም ።በማለት በድጋሚ እንኳን ደህና መጡ ብለዋል።

በእውነት የብፁዕ አባታችን አቡነ አብርሃምን ታላቅነት ዳግም የተመለከትንበት መልእክትን ነው፡፡

       የአበው በረከት አይለየን አሜን !

ምንጭ ማህበረ ቅዱሳን

Filed in: Amharic