>

አቶ ስንታየሁ ወዳላወቁት ስፍራ ተወሰዱ - ዛሬ ፖሊስ ፍ/ቤት አላቀረባቸውም....!

አቶ ስንታየሁ ወዳላወቁት ስፍራ ተወሰዱ – ዛሬ ፖሊስ ፍ/ቤት አላቀረባቸውም….!

የባልደራስ ለእውነተኛ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ እና የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ስንታየሁ ዛሬ በቀጠሯቸው መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት (ሳርቤት)  መቅረብ የነበረባቸው ቢሆንም ፖሊስ ሳያቀርባቸው ቀርቷል። ሌሎች ዛሬ ቀጠሮ የነበራቸውን እስረኞች ወደ ፍ/ቤቱ የወሰደው ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ አቶ ስንታየሁን ግን ከልክሏቸዋል።

ችሎት የተሰየሙት ዳኞች “አቶ ስንታየሁ የታሉ?” ብለው ሲጠይቁ፤ “ክሱን ስላቋረጥን አላቀረብነውም” የሚል ምላሽ ከፖሊስ ቀርቦላቸዋል። ዳኞቹም በመቀጠል ክሱ መቋረጡን የሚያሳይ ወረቀት ቢጠይቁም ፓሊስ ግን ምንም አይነት ደብዳቤ ሊያቀርብ አልቻለም።

አቶ ስንታየሁ አሁን ከጥቂት ግዜያት በፊት በፖሊሶች ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል። የአቶ ስንታየሁ ቤተሰቦች እና ወዳጆቻቸው በአሁኑ ሰአት በጭንቀት ላይ ይገኛሉ።

ፍትህ ለግፍ እስረኛው አቶ ስንታየሁ ቸኮል!

Filed in: Amharic