>

የግፍ እስረኛው አቶ ስንታየሁ ወደ ወረዳ 9 እስረኞች ማቆያ ተወሰዱ...!!! (ባልደራስ)

የግፍ እስረኛው አቶ ስንታየሁ ወደ ወረዳ 9 እስረኞች ማቆያ ተወሰዱ…!!!

ባልደራስ

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ትላንት ወዳልታወቀ ቦታ ፖሊሶች እየወሰዷቸው እንደነበር ለቤተሰቦቻቸው አሳውቀው ነበር፣ ዛሬ  አዲሱ ገበያ ችሎት አካባቢ ወደሚገኛው ወረዳ 9 የእስረኞች ማቆያ መወሰዳቸው ታውቋል። ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሲያስገቧቸው ፖሊስ ማተብህን በጥስ እንዳላቸውና አልበጥስም በማለት መሟገታቸውን ለቤተሰባቸው ገልጸዋል።

ፖሊስ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት  የከሰሳቸውን የመጀመሪያውን ክስ ማቋረጡንም በቃል እንደነገራቸውና  በጽሁፍ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ክስ መቋረጡን እንደሚያሳውቅ ፖሊስ ጨምሮ እንደነገራቸው አቶ ስንታየሁ ለቤተሰቦቻቸው  ገንለጸዋል።

በሌላ በኩል  አሁን እስር ቤት ለምን እንደሚያቆይዋቸው አቶ ስንታየሁ ፖሊሶቹን ሲጠይቁ፣ አዲስ ክስ ”  የባልደራስ አባል የሆኑትን አቶ  ናትናኤል ያለምዘውድን በየካቲት 29, 2014 ዓ.ም  በእስር ላይ በነበሩበት ወቅት ወደ ታሰሩበት እስር ቤት በመምጣት  ናትናኤል እዚህ ነው ወይ የታሰረው ብለህ በመጠየቅዎ ምክንያት የፖሊስ ሥራን አስተጓጉለዋል” የሚል ክስ እንደሚመሰረትባቸው   ለቤተሰባቸው ጨምረው ተናግረዋል።

ህጻናት ልጆቻቸው ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ ካሰናበታቸው ወዲህ ለዓመትባል ከወላጅ አባታቸው ጋር ለማሳለፍ በጉጉት እየጠበቁ ባሉበት ወቅት፤ ፖሊስ ባልተገባ ክስና ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጪ  በኩላሊት ህመም የሚሰቃዩትን የግፍ እስረኛውን አቶ ስንታየሁ ቸኮልን ከጣቢያ ወደ ጣቢያ እያዟዟሩ ማንገላታቱንና ማሰቃየቱን ቀጥሏል።

ፍትህ ለግፍ እስረኞች!

ፍትህ በግፍ በእስር ላይ ለሚገኙት ለአቶ ስንታየሁ ቸኮል!

Filed in: Amharic