>

ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ እና ጎበዜ ሲሳይ “በሽብር ፈጠራ ወንጀል” መጠርጠራቸውን ፖሊስ አስታወቀ (ኢትዮ ኢንሳይደር)

ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ እና ጎበዜ ሲሳይ “በሽብር ፈጠራ ወንጀል” መጠርጠራቸውን ፖሊስ አስታወቀ

ኢትዮ ኢንሳይደር

ከትላንት በስቲያ በቁጥጥር ስር የዋሉትን ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ እና ጎበዜ ሲሳይን “በሽብር ፈጠራ ወንጀል” እንደጠረጠራቸው የፌደራል ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስታወቀ። ጋዜጠኞቹ ከፌደራል መንግስቱ ጋር ሶስተኛ ዙር ውጊያ እያደረገ የሚገኘውን ህወሓትን በመደገፍም ተወንጅለዋል።

የፌደራል ፖሊስ ውንጀላውን ያቀረበውን ዛሬ አርብ ጷጉሜ 4፤ 2014 ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ባስገባው የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ደብዳቤ ነው። ፖሊስ በዚሁ ደብዳቤው “የሽብር ቡድን” ሲል ከጠራው ህወሓት “ከፍተኛ አመራሮች ጋር”፤ ሁለቱ ጋዜጠኞች “በተለያየ መንገድ በመገናኘት እና ተልዕኮ በመቀበል” እንደጠረጠራቸው አመልክቷል።

አንደኛ ተጠርጣሪ ሆና ችሎት የቀረበችው ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ “የአማራ ህዝብ መንገድ ከፍቶ ሽብር ቡድኑን ማሳለፍ እንዳለበት እና ሽብር ቡድኑ ወደ መሀል ሀገር ገብቶ ህገ መንግስቱና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል መናድ እንዳለበት ፍላጎቷን ገልጻለች” የሚል ውንጀላ ቀርቦባታል። ሁለተኛው ተጠርጣሪ ጎበዜ ሲሳይ “ ‘ጦርነቱ ሰልችቶናል። ከፈለጉ አራት ኪሎ ሄደው ማጽዳት ይችላሉ’ የሚል ቀስቃሽ እና ሀገሪቱ ላይ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር” የሚያደርግ መልዕክት አሰራጭተሃል በሚል በፖሊስ ተወንጅሏል።

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/8033/

Filed in: Amharic