>
5:13 pm - Saturday April 19, 1462

የሰዎች በህይወትና በሰላም የመኖር መብት ይከበር! (ኢሰመጉ)

የሰዎች በህይወትና በሰላም የመኖር መብት ይከበር!

ኢሰመጉ

 

 

ኦሮምያ ክልል

በኦሮምያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አሞሩ ወረዳ አጋምሳ ከተማ በ23/12/2014 ዓ.ም የሸኔ ታጣቂ ቡድን በአካባቢው

በመግባት ማንነት ላይ መሰረት በማድረግ በርካታ የአካባቢውን ንጹሃን ሰዎች መግደሉን እና በርካታ ሰዎችን ማፈኑን

ይህ ድርጊት የተፈጸመውም አካባቢው ላይ የነበረው የጸጥታ ኃይል በ22/12/2014 ዓ.ም አካባቢውን ለቆ ወደ ሌላ ግዳጅ ከሄደ በኋላ መሆኑን፤ በዚህም ምክንያት በአጠቃላይ ከ23 እስከ 25/12/2014 ዓ.ም ድረስ በርካታ ንጹሃን የአካባቢው ተወላጆች መገደላቸውን፣ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው እንዲሁም በአጋምሳ ከተማ የነበሩ በርካታ ሰዎች

አካባቢውን ለቀው በመሄድ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ኢሰመጉ አካባቢው ላይ ከነበሩ ሰዎች ካሰባሰበው

መረጃዎች ለማወቅ ችሏል፡፡

ይህንን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ኢሰመጉ ወደፊት ጥልቅ ምርመራ በማድረግ ዝርዝር ሪፖርት እንደሚያቀርብ ይገልጻል፡፡

ተያያዠ የህግ ድንጋጌዎች፡

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ አንቀጽ 3 “እያንዳንዱ ሰው በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነቱ የመጠበቅ

መብት” እንዳለው ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለችው የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ

ቃል-ኪዳንም በአንቀጽ 6 (1) እና 9 (1) ላይ ይህንኑ መብት በማረጋገጥ፣ መንግሥታት በቃል-ኪዳኑ የተረጋገጡትን

መብቶች በግዛታቸው የማክበር፣ የማስከበርና የማሟላት ግዴታ እንዳለባቸውም በአንቀጽ 2 (1) እና 2(2) ይደነግጋል።

የአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር አንቀጽ 4 ማንኛውም ግለሰብ በሕይወት የመኖር መብቱና የአካሉ

ደህንነት ሊከበርለትና ሊጠበቅለት እንደሚገባና እነዚህን መብቶቹን በዘፈቀደ ሊነፈግ እንደማይችል ተመላክቷል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 14 “ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት

የመኖር፣ የአካል ደህንነትና የነጻነት መብት አለው” ሲል ይደነግጋል። በተመሳሳይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 15

ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት እንዳለውና በሕግ ከተደነገገው ውጪ ሕይወቱን ሊያጣ እንደማይችል

በግልፅ ደንግጓል። ከዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች እንደምንረዳው

መንግስት የሰዎችን ሰብዓዊ መብቶች ማክበር፣ ማስከበር እና የማሟላት ሀላፊነት አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ሲቀር እና

በመንግስት ቸልተኝነት የዜጎች ሰብዓዊ መብቶች ሳይከበሩ ሲቀሩ ዋነኛ ተጠያቂ ሊሆን የሚገባው መንግስት ነው፡፡

የኢሰመጉ ጥሪ፡

✔ መንግስት ማንነት ላይ መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችና የደህንነት ስጋት አለባቸው የሚባሉ አካባቢዎችን በመለየት

የጸጥታ ሁኔታዎችን በትኩረት በመከታተል የሰዎች በህይወትና በሰላም የመኖር፣ ንብረት የማፍራት

መብቶች እንዲጠበቁ ኃላፊነቱን እንዲወጣ፣

✔ በደረሰባቸው ጥቃት ምክንያት ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አሞሩ ወረዳ አጋምሳ ከተማ የተፈናቀሉ ሰዎች

እንዲቋቋሙ፣ ሰብዓዊ እርዳታና ፍትህ እንዲያገኙ እንዲደረግ እንዲሁም ደህንነታቸው ተጠብቆ፣ ንብረት

አፍርተው በነጻነት እንዲኖሩ ዋስትና እንዲሰጥ እና የሚሰጡ ድጋፎችም ለሚያስፈልጋቸውና ለጥቃት

ተጋላጭ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ትኩረት በሰጠ መልኩ እንዲሆን፣

✔ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የሃገር ሽማግሌዎች፣ሃይማኖት አባቶች እና የማህበረሰብ አንቂዎች

ችግሮችን በውይይት የሚፈቱበት ሁኔታ እንዲፈጠርና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ

እንዲያበረክቱ ኢሰመጉ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Filed in: Amharic