>

በጦር ግንባር ላይ ባሉት የምስራቅ አማራ ፋኖዎቻችን ላይ ተፈጽሞ የከሸፈ መንግስታዊ ጥቃት...!!! ( ወንድወሰን ተክሉ)

በጦር ግንባር ላይ ባሉት የምስራቅ አማራ ፋኖዎቻችን ላይ ተፈጽሞ የከሸፈ መንግስታዊ ጥቃት…!!!

* ወንድወሰን ተክሉ*

♦️ ፋሺስታዊው የኦህዴድ/ብዓዴን ጸረ አማራ ብልጽግና ቡድን  በምስራቅ አማራ ፋኖ ላይ ድንገተኛ የማጥቃት እርምጃ መውሰዱን የኢትዮ 360 ሚዲያ ሀብታሙ አያሌው ገለጸ!!

♦️  እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም….!!!

በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወልዲያ ግንባር ከወራሪው ጠላት ትህነግ ጋር በመፋለም ላይ ባለው የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራር ላይ  በተከፈተ መንግስታዊ ድንገተኛ ጥቃት የፋኖ ምሬ ወዳጆና ፋኖ እስራኤል ህይወት ለጥቂት ከሞት እንዳመለጡና አንድ አመራር ተመትቶ መቁሰሉን የኢትዮ360 ሚዲያው ጋዜጠኛ ሀብታሙ አያሌው Habtamu Ayalew Teshome  በእለተ ቅዳሜው በዛሬ ምን አለ ፕሮግራም ላይ ገለጸ።

በምስራቅ አማራ ፋኖ ውስጥ የምሬ ወዳጆ ቀኝ እጅ በሆነው ፋኖ እስራኤል ላይ ዓርብ መስከረም 6/ ቀን 2015( 16-09-22) አምባሰል ማሪዬ ላይ መንግስታዊው አሸባሪ ቡድን ከበባ በማድረግ አፍኖ ለመውሰድ ያደረገው ሙከራ በፋኖ እስራኤል፣ በባልደረቦቹ፣ በቤተሰብና በአካባቢው ነዋሪ ሕዝብ ጣልቃ ገብነት ሁላችንም እንተላለቃታለን እንጂ ፋኖ እስራኤልን አትነኩም በማለት ከከበባው ሊያመልጥ እንደቻለ ገልጿል።

የምስራቅ አማራ ፋኖ ዋና አዛዥ ስለሆነው ፋኖ ምሬ ወዳጆ ላይ ስለተፈጸመው የግድያ ሙኩራ ሀብታሙ አያሌው ሲናገር  በወልዲያ የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት አዛዣ ፋኖ ምሬ ወዳጆን ከሚያዘው ሰራዊቱ ጋር ካለበት ግንባር ነጥለው ወደ ወልዲያ እንዲመጣ ካደረጉ በሃላ የተፈጸመበት የግድያ ሙከራ ነው ሲል ገልጾታል።

የመከላከያ አዛዦች ፋኖ ምሬ ወዳጆን «አንተ መሬ ነህ። እኛ አንተን መከተል ሰልችቶናል። አንተ ደግሞ የጠላት ቁጥር አንድ ኢላማ ነህ። ስለዚህ ወደ ሃላ ተመልሰህ እዚህ ወልዲያ በመሆን እንደ አዛዥነትህ ጦርህን ማዘዝ ይገባሃል በማለት ግንባር ላይ ካለው ሰራዊት ነጥለው ወደ ወልዲያ እንዲመጣ ካደረጉ በኋላ ምሬ ወዳጆ በወልዲያ ከተማ ወጣ ባለስፍራ ላይ በአካባቢው ካሉ ፋኖ አመራር ጋር ስብሰባ ላይ ባለበት ሁኔታ ድንገተኛ የሆነ ጥቃት ተከፍቶባቸው  ገደል ለገደል ተንከባሎ ህይወቱን ማትረፍ የቻለ ቢሆንም ከአመራሮቹ ውስጥ አንዱ ጉሮሮው ላይ ተመቶ ሆስፒታል በመታከም ላይ ነው በማለት ገልጿል።

ጸረ አማራው የኦህዴድ/ብዓዴን መራሹ አሸባሪው መንግስት በመላው የአማራ ፋኖ ላይ በከፈተው የማጥፋት ዘመቻ ከ15ሺህ በላይ የአማራ ፋኖን አፍኖ በእስር ቤት በማጎር እያሰቃየ ያለ ፋሺስታዊ ቡድን ሲሆን የአማራ ሕዝባዊ ኋይል -ፋኖ መስራቾችን እነ ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ የመ/አ ማስረሻ ሰጤንና ባልደረቦቻቸውን ደግሞ በየጫካውና በየዱር ገደሉ እንዲንከራተቱ ያደረገ ስርዓት መሆኑ ይታወቃል።

አሁን ከትህነግ ጋር እየተናነቀ ባለው የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራር ላይ – ማለትም – በፋኖ ምሬ ወዳጆና በፋኖ እስራኤል ላይ አሳቻ ጥቃት ለምን እና እንዴት ሊፈጸም እንደቻለ ክስተቱን እየገለጸ ያለው ሀብታሙ አያሌው ያልገለጸው ቢሆንም በምስራቅ አማራ ፋኖ ላይ ቀደም ሲል በኮምቦልቻ በደሴና በወልዲያ ተደጋግሞ የተፈጸመውን መንግስታዊ ጥቃትን በማስታወስ ስርዓቱ ወያኔን እዋጋለሁ ከሚለው በላይ የአማራን ፋኖ እና የፋኖን አደረጃጀትን እየተዋጋ ያለ መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ሆኖ ነው ያየነው።

ፋኖ ምሬ ወዳጆ ከተከፈተበት ድንገተኛ የግድያ ሙከራ በሃላ መከላከያው መጀመሪያ ጥቃቱን የፈጸመው ሰርጎ የገባ ጠላት ወያኔ ሃይል ነው ብሎ ለመሸፋፈን የሞከረ ሲሆን በወልዲያ ከተማ ሰርጎ ገብ የሆነ የወያኔ ሰራዊት አለ ወይ ተብሎ ሲጠየቅና አዎን በወልዲያ ውስጥ ሰርጎ ገብ የትህነግ ሰራዊት አለ ማለት እንደማይችሉ ሲያውቁ  ታሪኩን ለወጥ አድርገው በስህተት በደረሰን ጥቆም የእናንተን መሰባሰብ የጠላት ሃይል ነው በሚል የከፈትነው የስህተት ጥቃት ነው በማለት ሊያስተባብሉ እንደሞከሩ ነው የተገለጸው።

ሆኖም ይህ  የመከላከያው ማስመሰያ ምክንያት የማይሰራና በአንጻሩም ጥቃቱ ሆን ተብሎ ፋኖ ምሬ ወዳጆን ግንባር ላይ ካለውና ከሚያዘው ሰራዊት ነጥሎ ወደ ወልዲያ እንዲመጣ በማድረግ ሊደመሥሱት ብለው የወሰዱት እርምጃ መሆኑንና ከጥቃቱም ምሬ ወዳጁ ሳይፈልጉ መትረፍ መቻሉን ነው በግልጽ ቌንቌ መረዳት የተቻለው።

የምስራቅ አማራ ፋኖ ለተደጋጋሚ ጊዜ በብልጽግና መራሹ  መከላከያ ሰራዊት አንዴ በስህተት ነው – ሌላ ጊዜ ጥቀር መሳሪያና የቡድን መሳሪያን ልንቀበል ነው እያለ ጥቃት የተፈጸመበት ቢሆንም ለመከላከያ ያለውን አጋርነትና ወገናዊ ድጋፍ ግን ደጋግሞ ከመግለጽ ያላቆመ የመሆኑ ጉዳይ ጸሐፊውን አስገርሞታል።

በምስራቅ አማራ ፋኖ አመራር በሆኑት ምሬ ወዳጆና ፋኖ እስራኤል ላይ የተፈጸመውን መንግስታዊ የተጠና ድንገተኛን ጥቃት ድርጅቱ በራሱ መንገድ በይፋ ገና ያልገለጸው ሲሆን መረጃውን ለሕዝብ ያበቃው ሀብታሙ እያሌው እታች ምድር ላይ በራሱ መንገድ ባገኘው መረጃ ላይ ተመርኩዞ እንጂ ምሬም ሆነ ፋኖ እስራኤል እንዲሁም እንደ ድርጅት የምስራቅ አማራ ፋኖ በይፋ የገለጸው ነገር አለመሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

Filed in: Amharic