>

ዘመነን በማሰር የህዝብን ትግል ማስቆም አይቻልም....! (መስከረም አበራ)

ዘመነን በማሰር የህዝብን ትግል ማስቆም አይቻልም….!

መስከረም አበራ

“…. ዘመነ ትግሉ የሚጠይቀውን መስዕዋትነት ለመክፈል የተዘጋጀ አንድ ተዋናይ ነው እንጅ ትግሉ ራሱ አይደለም..,!!!

ጠዋት ስነሳ ብልፅግናው እና ተቀላቢ ባታሊዎኑ በፎቶ፣በዜና በማስደገፍ ግዳይ መጣሉን ሊያስረዳ ይሟሟታል፡፡ ሽንፈቱ ብቻ እንዲወራ የሚፈለገው ጎራ ሽንፈቱን እንዲጋት ምድረ ካድሬ እየተረባረበ የዜና መአት ያቀብለዋል፡፡ በገዛ ግዛቱ የሚኖርን አንድ ዜጋ በመያዙ መንግስት ተብየው አቅሉን በሚያስት ደስታ ውስጥ ነው- “እኔ ጎበዙ አንድ ዜጋን ተቆጣጠርኩ” አይነት ነገር! አማራ አራት አመት ሙሉ እንደ ዶሮ ታርዶ ሲጣል ልሳኑን ዘግቶ የኖረው አሚኮ “ጀግናው” መንግስት በግዛቱ የሚኖር አንድ ግለሰብን የመያዙን “ድንቅ ዜና” ማይክሮ ሰከንድ ሳታልፈው ለመዘገብ እያለከለከ ደርሷል፤ በኢቢሲ መንደር ትልቅ ፌሽታ ሆኗል፡፡

በትንሹም በትልቁም መደሰት ይቻላል! የማይቻለው የአማራን ህዝብ እንደ እንደ ዶሮ የሚታረድበት ስርዓት መምራትም በአማራ ህዝብ ተወዶ መኖርም ነው፡፡ ይህ የማይሆን ነገር ነው፡፡ ዘመነም ይህ እንደማይሆን ስለገባው ነው “ተው” ያለው! ዘመነን ለትግል ያሰለፈውን ጥቁር ገፅታችሁን እንደ ክብር ልብስ ለብሳችሁ ዘመነን ማሰሩ፣ማሳደዱመፍትሄ ከሆነ ይቅናችሁ!

በስተመጨረሻም ዘመነ ሰው ስንፈልግ ባጅተን ያገኘነው የስለት ልጃችን ነው!  ካድሬዎች እና መንግስታችሁ እንደምታስቡት የሚገርመን ዘመነ እንዴት ተያዘ ብለን ሳይሆን እንዴት በርካቶችን እንደ ዝንብ የሰበሰበውን የመንግስት መዓድ ገፍትሮ ለአማራ ህዝብ የመቆምን ሁልጊዜ የማይገኝ እድል መረጠ የሚለው ነው! ዘመነን እንወደዋለን፣እንሳሳለታለን…….! የዛሬው ከኤርትራ በረሃ ጀምሮ ያለፈበት የፈተናው አካል እንደጂ ሌላ አይደለም፡፡

ዘመነ የቆመለት ህዝብ በትግሉ ሁለንተናዊ ክብሩን ያስመልሳል፤የዘመነ እስር የዚህ የአማራ ህዝብ ትግል አንድ  አካል ነው!

ዘመነ የአማራ ህዝብ ትግል ያለወለም ዘለም የሚያዙት መሆኑ የገባው፣ትግሉ የሚጠይቀውን መስዕዋትነት ለመክፈል የተዘጋጀ አንድ ተዋናይ ነው እንጅ ትግሉ ራሱ አይደለም፡፡ ዘመነን በማሰር የህዝብን ትግል ማስቆም አይቻልም፡፡

የትግል ምክንያት ያለው ህዝብ ትግል አይቆምም! 

የማንም ልብ አይውደቅ !!!!!!

Filed in: Amharic