>

በአማላጅ ጋጋታ ለድርድር የመጣን ሰው "ወንጀለኛ ያዝን" ማለት የክህደት ጥግ ነው...! (ጌጥዬ ያለው)

በአማላጅ ጋጋታ ለድርድር የመጣን ሰው “ወንጀለኛ ያዝን” ማለት የክህደት ጥግ ነው…!

ጌጥዬ ያለው

ራሱን መንግሥት እያለ ያለግብሩ የሚጠራው የወራሪዎች እና አሽከሮቻቸው ቡድን የ60+ ሚሊዮን አማሮችን መሪ በምናምነው ክቡር መስቀል አታሎ ክንዱን ጨብጦታል። ክቡድ ቆብ በደፉ፣ ክቡር ካባ በደረቡ፣ ወርቃማ መስቀል በጨበጡ አባታችን እና “ከእኔ በላይ አማራነት ለአሳር” በሚሉ፥ ወጣት ፖለቲከኛ ወንድማችን አማላጅት ከቀረባቸው በኋላ በክህደት አስረውታል።

ወራሪዎችስ መቼም ግብራቸው ነው፤ አማላጆች ግን ሳይረፍድ ራሳችሁን ነፃ ልታወጡ ይገባል። ሌላው ቀርቶ ጉዳዩን የያዘው የፖሊስ ክፍል እንኳን ራሱን “የታክቲክ ዘርፍ” ብሎ በስሙ ጠርቷል። ታክቲክ በጥሬ ፍቺው አታሎ ማጥቃት ነው። ሺህ መዝገበ ቃላት ብታገላብጥ አልሸሹም ዞር አሉ ይሆን እንደሁ እንጂ ከዚህ የተለየ ትርጉም አታገኝለትም።

አማላጆች ሆይ በአስቸኳይ ከአማራ ህዝብ ጎን በመቆም መሪያችንን ልትመልሱልን ይገባል። ካልሆነ ከዛሬ ጀምሮ ፅኑ የሚሆን የደም መዝገብ በጥምር ስማችሁ ይከፈታል!

Filed in: Amharic