>

እሬቻ ከገዳ የወረራ ሥርዓት ጋር ምን ያገናኘዋል? እሬቻስ የማን በዓል/ባሕል ነው?  (አቻምየለህ ታምሩ)

እሬቻ ከገዳ የወረራ ሥርዓት ጋር ምን ያገናኘዋል? እሬቻስ የማን በዓል/ባሕል ነው? 

አቻምየለህ ታምሩ

ኢትዮጵያ ውስጥ የተዘረጋው የኦሮሙማ አፓርታይዳዊ አገዛዝ ዋና ስራ አስፈጻሚ የኾነው ዐቢይ አሕመድ ከሁለት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ እሬቻን የኦሮሞ ገዳ ሥርዓት አካል ነው ብሎናል። እሱና በስሩ የኮለኮላቸው  የአፓርታይድ አገዛዙ ፊታውራሪዎች ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ጥንታዊቱን በራራን፤ ዘመናዊቱን አዲስ አበባን አፍርሰው በኦነጋውያን የደነዘዘ አእምሮ ውስጥ በተፈጠረችው ፊንፊኔ ለመተካት ያላፈረሱት የቆየ አሻራና የከተማይቱን ጥንታዊነት የሚመሰክር ምልክት የለም።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የፖሊስ ሠራዊት ኦሮሚያ ከሚባለው ክልል በመለመሏቸው ለከተማው ከባሕር የወጣ አሳ በሆኑ የፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ ቀሮዎች ተክተውታል። ደብረ ዘይት በሚገኘው ሆራ ሐይቅ ከመስቀል በኋላ ይከበር የነበረውን እሬቻን “ሸገርን ለማስዋብ” በሚል ዐቢይ አሕመድ ግለሰቦችን [አብዛኛዎቹ አማሮች ናቸው] አምስት  ሚሊዮን ብር እንዲያወጡ አድርጎ ያስቋረውን ሰው ሰራሽ ሐይቅ “ሆራ ፊንፊኔ” የሚል ስያሜ በማውጣት እሬቻን አዲስ አበባ ውስጥ እንዲከበር አድርገዋል።

ሽመለስ አብዲሳ በሸራተን አዲስ እሬቻን አስመልክቶ በኦሮሚፋ ባደረገው ዲስኩር “እሬቻ ወደ አዲስ አበባ ወደ ጥንቱ እሴት ተመልሶ እንዲከበር ውሳኔ የተላለፈው በጠቅላይ ሚኒስትራችን በዶክተር ዐቢይ አሕመድ ነው” ሲል ነግሮናል። ይህን የሽመልስ አብዲሳ ምስክርነት ይዘን የዐቢይ አሕመድን “ሸገርን ማስዋብ” ፕሮጀክት ስንመረምር በዚህ ፕሮጀክት ስም በተሰበሰበው የሕዝብ ገንዘብ አዲስ አበባ መሀል የተቋረውና ሆራ ፊንፊኔ ብለው የሰየሙት ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለምን አላማ እንደታሰበ ግልጽ ይሆንልናል።

በመሰረቱ እሬቻ የኦሮሞ ገዢ መደብ በየስምንት አመቱ ሲያደርግ የኖረውን ወረራ ገና ሳያካሂድ፤  ኦሮሞ የእርሻ ስራና ሰብል ማምረት ሳይጀምርና ኦሮሞ ዛሬ ኦሮምያ የሚባለውን ምድር ሳይረግጥ መስከረም በገባና መስቀል በተከበረ በሳምንቱ ሲከበር የኖረ የአራሾች ክብረ በዓል ነው። እሬቻ በሸዋ ውስጥ በብዛት ይከበረ የነበረው ደብረ ዘይት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ  የጸበል ሥፍራ በነበረው ዛሬ ሆራ  ሐይቅ እየተባለ በሚጠራው ቦታ ነበር።

እሬቻ የኦሮሞ በዓል አለመሆኑን በተጨማሪ ለማወቅ የቃሉን ፍቺ ማየትም ይቻላል። እሬቻ የሚለው ቃል የአማርኛ ቃል እንጂ የኦሮምኛ ቃል አይደለም። እሬቻ ኦሮምኛ ነው የሚል ቢኖር የቃሉን የኦሮምኛ ግንድና ቃሉ በኦሮምኛ እንዴት አንደሚረባ ማስረዳት ይጠበቅበታል።

የግዕዙ ሊቅ አለቃ ደስታ ተክለ ወልድ “ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት” በሚል ባሰናዱት መዝገበ ቃላት ውስጥ እንደጻፉት እሬቻ ዋናው ሰብል ደርቆ ከመታጨዱና በአውድማ ተወቅቶ ወደ ጎተራ ከመግባቱ በፊት ቀድሞ የደረሰው ተቆርጦ በበትር በመወቃት ወይም በእጅ ታሽቶ የሚቀመሰው እህል ይሉታል። ሌላው የግዕዝ ሊቅ ከሣቴ ብርሃን ተሰማም በ1951 ዓ.ም ባሳተሙት “የአማርኛ መዝገበ ቃላት” መጽሐፋቸው የአማርኛ ቃል ስለሆነው እሬቻ የሚነግሩን ትርጉም ተመሳሳይ ነው።

በመሆኑም የእሬቻ በዓልንም የሚያከበረው አራሹ ገበሬ ክረምቱን በሰላም እንዲያልፍ፤ ያዘመረው እህል ለፍሬ እንዲበቃና እሸት እንዲቀምስ ያስቻለውን ፈጣሪውን ለማክበር ነው። በመሆኑም የእሬቻ በዓል እህል የሚያበቅል አራሽ ገበሬ የሚያከብረው አመታዊ ዝክር ነው።

እዚህ ላይ የቦረና ኦሮሞው ወዳጄ ጎዳና ያዕቆብ እሬቻን የኦሮሞ ባሕል ለሚያደርጉት ኦነጋውያን የሰጠውን አስተያየት መጥቀስ አስፈላጊ ነው። ጎዳና እሬቻን አብረንህ እናክብር ለሚሉት ሰዎች የሰጠው አስተያየት እንዲህ የሚል ነበር፤

“እሬቻን አብረንህ ሳናከብር ላሉኝ ወዳጆቼ ከብቶቻቸውን ለማጠጣት የእግዜር ዝናብ ከሚፈልጉ ከዘላን ማኅበረሰብ የተገኘሁት ቦረና በሚን ሁሳብ ነው ዝናብ ቆመ ብዬ ምስጋና የሚያቀርበው? በሹፌርነት ቤተሰቡን የሚያስተዳድር ሰው ነዳጅ ጠፋ ብሎ ምስጋና ሲያቀርብ ሰምታችኹ ታውቃላችኹ? አርብቶ አደሩ ቦረናስ አራሽ በበሬ ሆኖ ስለ ሰብል እና አዝመራው ተጨንቆ እንኳን ዝናብ ጠፋ አሁን ሰብሌን መሰብሰብ እችላለኹ የሚለው በምን መዋቅር ነው?”

ጎዳና እንዳለው ኑሮውን የከብት ጭራ እየተከተለ ውኃና ግጦሽ ፍለጋ የሚንከራረት ዘላን የማይመለከተውን በእርሻ የሚተዳደሩ አርሷደሮችን በዓል ያከብራል ካልተባለ በስተቀር የከብት ጭራ እየተከተለና ውኃና ግጦሽ ፍለጋ የሚንከራተት ዘላን ዝናብ ቆመ ብሎ ምስጋና ማቅረብ በሹፌርነት ልጆቹን የሚያስተዳድር የቤት ባለቤት ነዳጅ ጠፋ ብሎ ለፈጣሪው ምንጋና እንደማቅረብ አይነት ጤና የጎደለው ተግባር ነው።

የኦሮሞ ብሔርተኞቹ እነ ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን፣ ዶክተር ነገሶ ጊዳዳ፤ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፤ አቶ ይልማ ደረሳ፤ ፕሮፈሰር ተሰማ ታዓ፤ ወዘተ እንደነገሩን ደግሞ ኦሮሞ ከብት በማርባት የሚተዳደር የነበረ ሲሆን የእርሻ ስራ የጀመረው ደግሞ ዛሬ በሰፈረበት አካባቢ ካገኛቸው የኢትዮጵያ ነገዶች ተምሮ መሆኑን ነግረውናል። ዘመኑም ከ17ኛውና ከ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ ነው። ይህ ማለት የተሰማራበት የስራ መስክ ከብት ማርባት፤ እምነቱ ደግሞ ዋቄ ፈና ነው የተባለው ኦሮሞ የማያበቅለው እህል የሚሽትበትን ወቅት ጠብቆ ሃይማኖቱ አይደለም የተባለውን መስቀልን አሳልፎ መስቀል በሆነ በሳምንቱ እህል እንዲያበቅል፤ እሸት እንዲቀምስ ለሚያስችል ፈጣሪ ምስጋና ሊያቀርብ ይችላል ካልተባለ በስቀር ከብት አርቢ የነበረው ኦሮሞ እሬቻን ማክበር የጀመረው ሸዋን ሲወር ያገኛቸው አራሽና እህል አብቃይ የአማራ ገበሬዎች ያመረቱት ሰብል ለፍሬ እንዲበቃና እሬቻ [እሼት] እንዲቀምሱ ላስቻላቸው ፈጣሪያቸው ያቀርቡት የነበረውን የምስጋና ባሕል በመውረስ ነው።

ስለዚህ እሬቻ ከብት አርቢ የነበረው ኦሮሞ ከነ ቃሉ ከሰብል አምራች የአማራ አርሶ አደሮች የወረሰው የምስጋና በዓል፣ ቃሉም አማርኛ  ሲሆን ኦሮሞ አካባቢውን ከመውረሩ በፊት ጀምሮ ይከበር የነበረው ደብረ ዘይት በሚገኘው ሆራ ሐይቅ እየተባለ በሚጠራው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የጸበል ቦታ እንጂ አዲስ አበባ ውስጥ አልነበረም።

ይህ እውነት ቢሆንም ቅሉ የኦነጋውያን ኦሮሙማ ማዕከሉ ዘረፋ፣ ወረራና ቅሚያ ስለሆነ አዲስ አበባን ዳግማዊ ምኒልክ የጥንቱን በራራ ፍራሽ አድሰው እንደገና ከማቆማቸው በፊት የነበሩት ኦሮሞዎች፤ እሬቻም ከነ ቃሉ የኦሮሞ አይደለም፤ አዲስ አበባ ውስጥም ተከብሮ አያውቅም የሚለው የታሪክ እውነት ደንታ አይሰጣቸውም። ኦነጋውያን እንኳን በአዲስ አበባ ዙሪያና በመላው አገሪቱ የሚገኘው ኦሮምኛ ተናጋሪ ቀርቶ ከቦረና ውጭ ያለው ኦሮምኛ ተናጋሪ በወራሪ አባገዳዎች መሬቱን የተቀማ፣ ማንነቱን በኃይል የቀየረና ኦሮምኛ ቋንቋ በግዳጅ እንዲናገር የተደረገ እንጂ  ኦሮሞ አለመሆኑን ኦሮሞዎ ብሔርተኞቹ እነ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ፕሮፈሰር መሕመድ ሐሰን፣ ወዘተ እንኳ ያጠኑትን ታሪክ ለመቀበል ዝግጁ ያልሆኑ ሕመምተኞች ናቸው። በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ትክክለኛ ኦሮሞዎቹ ወራሪዎቹ አባገዳዎቹና የነሱ ዘመዶች ብቻ ናቸው። ከነሱ ውጭ ያለው ነባሩ ሕዝብ  ተገዶ ኦሮምኛ እንዲናገር ተደረገ እንጂ  ኦሮምኛ ስለተናገረ ኦሮሞ አይደለም።

ኦሮምኛ የሚናገረው ሁሉ ኦሮምኛ እንዳልሆነ እውነተኞቹ ኦሮሞዎቹ ራሳቸው ምስክር ናቸው። በእውነተኞቹ ኦሮሞዎች ትውፊት ውስጥ «Saglan Borana, sagaltamman garba» የሚል አባባል አለ። ይህ ወደ አማርኛ ሲተረጎም «ዘጠኙ ኦሮሞ ነው፤ ዘጠናው ገርበ ነው» ማለት ነው። ገርበ ኦሮሞ ሲስፋፋ ያስገበራቸውንና ባርያ ያደረጋቸውን ነገዶች የሚጠራበት ስያሜ ነው። በኦሮሞ በራሱ ትውፊት መሰረት ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልል ውስጥ ከሚኖረው ኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝበ መካከል ትክክለኛው ኦሮሞ ከአስሩ አንዱ ብቻ ነው ማለት ነው። ከአስሩ ዘጠኙ ገርበ ወይም በአባገዳዎች በወረራ የተያዘና በኃይል ኦሮሞ የተደረገ ሕዝብ ነው።

ይህንን እውነት ከኦሮሞዎች ትውፊት በተጨማሪ ዛሬ በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል። የሰላሌና አምቦ ሕዝብ የDNA ውጤት እንደሚያሳየው ዝምድናው ከምንጃርና ወይም ጅሩ ሕዝብ ጋር እንጂ ከቦረና (እወነተኛው ኦሮሞዎች) ጋር አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ ፖል ሶሊሌት የተባለው የፈረንሳይ ጎብኝ እ.ኤ.አ. በ1884 ዓ.ም. ሸዋን ጎብኝቶ በጻፈው የጉዞ ማስታወሻው በሰላሌና ጃርሶ ውስጥ ኦሮሞ ገርበ ያደረጋቸው የአካባቢው ቀደምት ባለይዞታዎች አማሮች እንደሆኑ ጽፏል።

የአርሲ ሕዝብ ዝምድናው ከሐዲያ ጋር እንጂ ከቦረና ጋር አይደለም። ጀርመናዊው የታሪክ ምሁር በርካምበር እንዳጠናው ከአርሲ ሕዝብ ሁለት ሶስተኛው ሐድያ ነው። የጅማ ሕዝብ ከየምና ከከፋ ሕዝብ እንጂ ከኦሮሞ ጋር ምንም ዝምድና የለውም። አባጅፋር ራሱ አረብ እንጂ ኦሮሞ አይደለም። ወለጋ እውነተኛ ኦሮሞዎች ከመቶ አስርም አይሞሉም። እውነተኛ ኦሮሞዎቹ ለባሪያ ፍንገላና ውሀና ሳር ፍለጋ መጥተው ሌላውን ገርበ አድርገው የቀሩት አባገዳዎችና ልጆቻቸው ብቻ ናቸው።

የትኛውም ብሔርተኛ ቢሆን አገር ማፍረስ እንጂ አገር ማስተዳደር አይቻለውም። በየትኛውም አለም ብሔርተኛ ሆኖ በመንግሥትነት ተሰይሞ አገር ሲያፈርስን እንጂ አገር ሲያረጋጋና ሲያስተዳድር ታይቶ ተሰምቶ አይታወቅም። በኢትዮጵያም ሆነ በአለም ታሪክ በብሔርተኛነት እሳቤ በመንግሥትነት ተሰይሞ አገር የማስተዳደር እርሾና የሥነ መንግሥት እሳቤ ያለው አገዛዝ የለም። የኦሮሞ ብሔረተኞም ዓላማቸው ወንድምን በወንድም ላይ እኅትን በእኅት ላይ በማስነሳት የኦርሞ ኤምፓየር ቅዠታቸውን ማሳካት እንጂ ኢትዮጵያ የምትባልን አገር የማስተዳደር ፍላጎት፣ እርሾና የሥነ መንግሥት እሳቤ የላቸውም።

ከነገዳቸው ውጭ ያለውን የተቀረውን ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ይዞ ለመቆየት የሚያስችል ባሕላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ እሴት እንዲሁም የሥነ መንግሥት አስተሳሰብ የሌላውን ዘረፋን፣ ወረራንና መውረስን ፖለቲካቸው ያደረጉ ያበዱ ብሔርተኞች መንግሥት ይሆኑናል ብሎ ማሰብ ውሻ ነከሰኝ ብሎ ለጅብ አቤት እንደማለት አይነት የዋህነት ነው። ብሔርተኛ ሁሉ አገር ማፍረስ እንጂ አገር ማስተዳደር እንደማይችል ያለፉት አርባ አራት አመታት የኢትዮጵያ የቁልቁለት መንገድ ምስክር ነው። ልክ በቅሎ እንደማትወልድ ሁሉ የነገዱ ሳይሆን የኢትዮጵያ ስነ መንግሥት እሳቤ የሌለው፣ ከነገዱ ውጭ ያለውን የተቀረውን ኢትዮጵያን አንድ አድርጎ ይዞ ለመቆየት የሚያስችል ባሕላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ እሴት ያልያዘ ማናቸውም አይነት የሁሉም መንግሥት የመሆን ችሎታ የለውም። ያለው ችሎታ ቢኖር እንደ ወያኔና ኦነግ የሌላውን መዝረፍ፣ መቀማት፣ መቀራመት፣ መውረስና የተሰራ አገር ማፍረስ ብቻ ነው።

ባጭሩ እሬቻ ኦሮምኛም የኦሮሞም አይደለም። እሬቻ ኦሮሞ ከንቱ ወርሶ ኢትዮጵያን ከወረረበት የገዳ ሥርዓት ጋር የሚያገናኘው አንዳች ነገር የለም። እሬቻ የኦሮሞ በዓል/ባሕል  ቢሆን ኖሮ የሚከበረው አንጋፋው ኦሮሞ በሰፈረበት በከብት አርቢው ቦረና እንጂ ከቦረና 600 ኪሎ ሜትሮች በላይ ርቆ  በእርሻ ሥራ የሚተዳደሩ ገበሬዎች በሚኖሩበት ደብረ ዘይት አይደለም።

እሬቻ የሚባልም የአማርኛ እንጂ የኦሮምኛ ቃል የለም። እሬቻ የሚል ስር ያለው የኦሮምኛ ቃል የለም። ባለፈው ዓመት እሬቻ ቃሉም ሆነ ባሕሉ የኦሮሞ አለመሆኑን በጻፍሑት ጽሑፍ ላይ አንዱ የኦሮሞ ብሔርተኛ ፕሮፈሰር ባቀረበው ትችት እሬቻ አሮምኛ ነው፤ “ህርሱ” የሚል ቃል በኦሮምኛ ውስጥ አለ፤ ትርጉሙም መስጠት ማለት ነው፤ ስለዚህ እሬቻ የተወሰደው ከህርሱ ነው የሚል መልስ ቢጤ ጽፎ ነበር። ይህ የኦሮሞ ብሔርተኛ ፕሮፈሰር ግን የበዓሉ ትርጉም ህርሱ የሚል የኦሮምኛ ቃል ከሆነ  በዓሉ ኦሮምኛ ወዳልሆነው ወደ እሬቻ ለምን እንደተቀየረ አልነገረንም። በዓሉ የኦሮሞ ከሆነ፣ ቃሉም ኦሮምኛ ከሆነ በዓሉ ህርሱ ተብሎ ለምን እንደማይከበር፤ በእርሻ የሚተዳደሩ ገበሬዎች የሚያከብሩትን ይህን በዓል ቀዳሚው ኦሮሞና ከብት አርቢው ቦረና ሳያከብረው ገርባው ብቻ ለምን እንደሚያከብረው መልስ የሰጠ ሰው እስካሁን አላየንም።

በእውነቱ እሬቻ የኦሮሞ ባሕል ቢሆን ኖሮ ቃሉ ኦሮምኛ፤ በዓሉንም ከሁሉ በፊት እሬቻን ሊያከብሩት የሚገባቸው ገርባዎች ሳይሆኑ ትክክለኞቹ ኦሮሞዎች ቦረናዎች ነበር። ያልተበረዘው ቀዳሚው ኦሮሞ የሆነው ቦረና የማያከብረው በዓል የኦሮሞ በዓል አይደለም። ቦረና ራሱ እሬቻን የገርባ በዓል ነው የሚለው።

እሬቻ የኦሮሞ ባሕል አለመሆኑን ለማወቅ ቃሉ አማርኛ እንጂ ኦሮምኛ አለመሆኑን፤ በዓሉም በእርሻ የሚተዳደሩ እንጂ የከብት አርቢዎች በዓል አለመሆኑን፤ በዓሉ ኦሮሞ የእርሻ ስራን ከመልመዱ ዘመና በፊት ዛሬ በሚከበርበት በደብረ ዘይት የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የጸበል ቦታ በአማሮች ሲከበር የኖረ በዓል መሆኑን፤ ገርባው እንጂ ያልተበረዘውና ትክክለኛ ኦሮሞ  የሆነው ቦረና ቃሉንም ሆነ በዓሉን የማያውቀው መሆኑን፤ ይልቁንም እሬቻ ሲከበር የኖረው ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነው ቦረና ከሚኖርበት 600 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ላይ መሆኑን ማስታወስ በቂ ነው።

ቦረና የማያከብረውን በዓል ገርባው የኦሮሞ ነው ብሎ ማክበሩ የሚያሳየን ነገር ቢኖር ገርባው ኦሮሞ አለመሆኑን ብቻ ነው።  እሬቻ የኦሮሞ ቢሆን ኖሮ ቃሉ ኦሮምኛ ይሆን ነበር፤ በዓሉም በገርባው ምድር ሳይሆን ትክክለኛ ኦሮሞ የሆነ ቦረና በሚኖርበት በቦረና ምድር እንጂ ቦረና ከሚኖርበት አካባቢ 600 ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ ገርባ እንጂ ቦረና በማይኖርበት ምድር በሸዋ ውስጥ አይከበርም ነበር። ይኼው ነው።

Filed in: Amharic