በአስቸኳይ ከእስር ፍቱትና ይረሸን ሀላፊነቱን እኔ እውስዳለሁ…!
ኮማንደር በቀለ አብዩ የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መመሪያ አዛዥ።
በወለጋ አማራ ተጨፈጨፈ፣ወጣቶች አርበኛ ዘመነ ካሴን ጠይቁት የሚል የሚዲያ ቅስቀሳ አድርገሃል በሚል በአዴት ከተማ ፖሊስ አዛዝ ም/ኮማር አበረ አሰፋ ትዕዛዝ በ21/01/2015 ዓ/ም በአዴት ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስሬ ከዋልሁ በኋላ ከቀኑ 11:00 ወደ ይልማና ዴንሳ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ተዛዋሬ አደርሁ።
በ22/01/2015 ዓ/ም ከቀኑ 7:30 ላይ
1ኛ ኮማንደር በቀለ አብዩ የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ አዛዥ
2ኛ ም/ኮማንደር አበረ አሰፋ የአዴት ከተማ ፓሊስ አዛዥ
3ኛ ኮማንደር ብርሃኑ አለሙ የይልማና ዴንሳ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ
4ኛ ሁለት ሲቢል የለበሱ የአዴትና አካባቢው ልዩ ሀይል አመራሮች በጋራ ሁነው ከታሰርሁበት ጣቢያ አስወጥተው ወየ ይልማና ዴንሳ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት አንድ ቢሮ አስገቡኝ።ገና እንደገባሁ ኮማንደር በቀለ አብዩ የዞን አመራሮች የምትሳደብ፣ወለጋ ላይ አማራ ተጨፈጨፈ የምትል፣ዘመነ ካሴ ይፈታ የሚል ቅስቀሳ የምትቀሰቅስ እንዴት ብትንቀን ነው የሚል የዛቻ ማዕት ያውረድ ጀመረ። ገና ከጅምሩ የተጀመረው ዛቻ ወደ ድብደባ ተቀየረ ።ከመቀመጫው ተነስቶ በጥፊ በእርግጫ በቦቅስ ድብደባውን ቀጠለ።ሶስት ጊዜ ሸጉጥ አውጥቶ ማስጠቢቂያ አስለቀቅ ወደ እኔ አነጣጠረ።ተኩስና ግደለኝ እኔም የባርነት ህይውት ሰልችቶኛል አታመንታ አልሁት። የሚችለውን ሁሉ አደረገ ግን አረካም። ሁለቱ የልዩ ሀይል አመራሮች በግረምት ሁኔታውን ይከታተላሉ።የአዴት ከተማ ፖሊሰ አዛዥም እኔን በዛ መልኩ እንድደበደብ ያመቻቸው እርሱ ነው።የይልማና ዴንሳ ወረዳ ፖሊስ አዛዥም ከመቀመጫው ሳይነሳ ይሰድበኝ ጀመር።
ኮማንደር በቀለ አብዩ ኩፍኛ ደብደባ ከፈፀመብኝ በኋላ ባደረገው ግፍ ሁሉ ባለመደቱ በአስቸኳይ ከእስር ይፈታና ከአደባባይ ላይ ይረሸን።ሀላፊነቱን እኔ እውስዳለሁ።ለሌላው መማሪያ ይሆን ዘንድ አደባባይ ላይ ይረሸን ብሎ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ ከግቢ ወጣ።ኮማንደር በቀለ በፈፀመብኝ ድብደባ የግራ ጀሮየ ላይ ከፍተኛ ችግር ፈጥሮብኛል።ጉረሮየም ጉዳት ደርሶበታል።ለይልማና ዴንሳ ወረዳ አቃቢ ህግ ባለሙያዎች፣ለአዴት ፖሊስ አባላት አስቸኳይ ህክምና ማደረግ እንዳለብኝ በተደጋጋሚ ብጠይቅም በአዴት ከተማ ፖሊስ አዛዥ ሞ/ኮ/ር አበረ አሰፋ እንቢተኝነት ህክምና ተከልክየ ከሰነበትሁ በኋላ ዛሬ ከእስር ተፈትቻለሁ።
ኮማንደር በቀለ ሆይ ሞት እረፍት ነው። ሞትን የሚፈራ ሰው ፈልገው ያስፈራሩ።ንፁሃንን መደብደብ በወያኔ ጊዜም ሲያደርጉት የነበረው አሮጌ ልምድ እንጅ አዲስ መንገድ አይደለም።በ1997 ዓ/ም ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፅመውን ግፍ በመቃውሜ 3 ጊዜ ያሰሩኝ የፈቱኝ እረስዎ ነበሩ።ተ፣ትናንትም ዛሬም በህዝባችን ላይ ለሚደረሰው ግፍና መከራ ለምን የሚሉ ንፁሃንን ማሳደድና ማሰቃየት ለእርስዎ ሹመትና ማረግ እድገት ስለሆነልዎ የእኛ ቁስል የእረስው ሹመትና እድገት የሆነ ቢሆንም በጊዚ ሂደት በህግና በታሪክ ከመጠየቅ ግን የሚያመልጡ ከመሰለዎት ተሳሰተዋል።ይመኑኝ ጊዜ ሲደርስ ወደ ፍትህ አደባባይ ከሚቀርቡት ግለሰቦች መካከል እርስዎ የመጀመሪያው መሆንውን አይጠራጠሩ።በድብደባና አፈና መኖር ቢቻል ኑሮ የትናንቱ የነፍስ አባትዎት ትህነግ ከአራት ኪሎ ቤተመንግስት ወጥቶ ደደቢት ባልተወሸቀ ነበረ።
በእስርና በወከባ የሚቆም ትግል አልጀመርንም።ትግላችን የሚጠይቀውን ሁሉ ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነኝ።ትግሉ ይቀጥላል።
ምስጋና
በያላችሁበት ሁሉ ድምፅ ለሆናችሁኝና ጣቢያ ድረስ እየመጣችሁ ለጠየቃችሁኝ ሁሉ ምስጋየ ይድረሳችሁ።
ለአዴት ከተማና የይልማና ዴንሳ ወረዳ ፖሊስ አባላት የአቃቢ ህግ ባለሙያዎች ሁሉ ላሳያችሁኝ ፍቅርና ክብር ብቻ ሳይሆን ግፍን የምትጠየፉ ከህዝብ ጎን የቆማችሁ መሆናችሁን ያሳያችሁበት አጋጣሚ ነበረ።
ነፃነት ወይም ሞት !