>

"ዘመነ ካሤ በአስቸኳይ ይፈታ!!!" በሚል ሰልፍ የወጡ ነዋሪዎች ላይ ብአዴን ቅጣት ጣለ ....! (ጌጥዬ ያለው)

“ዘመነ ካሤ በአስቸኳይ ይፈታ!!!” በሚል ሰልፍ የወጡ ነዋሪዎች ላይ ብአዴን ቅጣት ጣለ ….!

ጌጥዬ ያለው


*…. የአርበኛ የዘመነ ካሤን እስር ተከትሎ የባሕር ዳር ፖሊሶች በከፊል ትጥቅ እንዲፈቱ እየተገደዱ ነው

በምዕራብ ጎጃም፤ ሽንዲ ወንበርማ ወረዳ፤ #ቡራፈር ቀበሌ፤ በልባን የሚኖሩ አማሮች ባለፈው መስከረም 18 ቀን 2015 ዓ.ም. “‘እኔም ዘመነ ካሤ ነኝ፣ ዘመነ ካሤ በአስቸኳይ ይፈታ” በማለት በቡድን ሰልፍ አድርጋችኋል” በሚል እየተደበደቡ ነው። ባለፈው መስከረም 24 ቀን የቀበሌው ሊቀ መንበር እና የቀበሌው ፖሊስ ወጣቶችን ሰብስበው ደብድበዋል። በተጨማሪም ከመቶ እስከ አንድ ሺህ ብር መቀጮ በግዳጅ መክፈላቸውን የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል። የገንዘቡ ሰብሳቢዎችም ሊቀ መንበሩ እና ፖሊሱ ናቸው።

ታዲያ በሕገ ወጥ ኬላ ገንዘብ ሰብሳቢው የአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ) መሪ አርበኛ #ዘመነ ካሤ ወይስ የወራሪው የኦሮሞ አገዛዝ ተላላኪው ብአዴን? ድርጊቱ ሀገር መስራቹን አማራ በምጣኔ ኃብት፣ በፖለቲካ እና በስነ ልቦና አድቅቆ ሀገር አልባ የማድረጉ የኦሮሙማ ፕሮጀክት ውጥን ነው። የወንበርማ ወጣቶች ሆይ ዓይናችሁን የነካውን ዓይኑን አውጡት!

እናንተ መሪያችሁን ለመደገፍ በተከለከላችሁበት አፍታ አማራን ጨፍጫፊው የኦሮሞ ሰራዊት በአገዛዙ ድጋፍ ዱላውን ጥሎ ብሬን እና ስናይፐር እየታጠቀ እንደሆነም እንዳትዘነጉ። ከፖሊስ ጣቢያ እስከ ብርሸለቆ የጦር ማሰልጠኛ ተበርግዶ እየተሰጠው እየዘረፈ መሆኑንም አስታውሱ።

ራሳችሁን ለመከላከል ቢቻል ብትደራጁና በጋራ ብትወጡ ጥሩ ነው። ይሄን ማድረግ ካልተቻለ ግን ጠቅላላ ጉባዔ ወይም የቡድን ጠርናፊ ሳትጠብቁ በየግላችሁ ራሳችሁን አስከብሩ። ከፈጣሪያችሁ ቀጥሎ በራሳችሁ ላይ ሥልጣን ያላችሁ እናንተው ናችሁ።

እሸቴ ሞገስ እና ልጁ ይታገሱ ያደረጉት ይህንኑ ነው። ኤርትራዊው ዘርአይ ደረስ በሮም አደባባይ ፋሽስት ጣልያንን አብጠልጥሎ ጀግኖች የኢትዮጵያ አርበኞችን ለመደገፍ እና እንኳንስ በሮም በአዲስ አበባ የተከለከለውን አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ አላማ በጣልያን ምድር ለማውለብለብ ጓደኛ አላስፈለገውም። ብቻውን አድርጎታል።

ብትችሉ በህብረት፤ ባትችሉ በተናጠል ማንነታችሁን አስከብሩ!

የአርበኛ የዘመነ ካሤን እስር ተከትሎ የባሕር ዳር ፖሊሶች በከፊል ትጥቅ እንዲፈቱ እየተገደዱ ነው!!!

ቀበሌ 16 በሚገኘው ፖሊስ መምሪያ ታጥቀው ወደ ቢሯቸው እንዳይገቡ ተደርገዋል። የዘመነ እስር በፖሊስ አባላቱ ውስጥ ቁጣን ቀስቅሷል።

በተያያዘ ከትናንት በስቲያ መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በውቢቷ በባሕር ዳር ወጣቶች በወራሪው የኦሮሞ አገዛዝ ለሚመራው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባልነት በግዳጅ እየታፈሱ ነው። በተለይም በቀበሌ 7 እና በቀበሌ 2 በርካታ ጎልማሶችና ወጣቶች ታፍሰዋል። አፈሳው ከምሽት ሁለት ሰዓት ጀምሮ የሰሌዳ ቁጥር በሌላቸው ተሽርካሪዎች ነው እየተፈፀመ የሚገኘው። ከባሕር ዳር በተጨማሪ በሌሎች የአማራ ከተሞችም አፈሳው እንደቀጠለ ሲሆን በቅርቡ ከሞጣ የታፈሱ ወንዶች አዴት ከሰነበቱ በኋላ ወደ ዳንግላ አቅራቢያ መዘዋወራቸውን የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል።

Filed in: Amharic