የታምራት ላይኔ ነገር፡ የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ…!!!
አቻምየለህ ታምሩ
ታምራት ላይኔ የሚባለው የአማራ ሕዝብ ቀንደኛ ጠላት የፋሽስት ወያኔ ሎሌ ሆኖ አዲስ አበባ እንደገባ ወደ ሐረር በማቅናት «ሽርጥ ለባሽ ይሏችሁኋል…በሏቸው» አማራውን ያስፈጀው፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያን በፋሽስት ወያኔ ቅኝ ግዛት ስር እንዲወድቁ ያደረገውና በአማራ ሕዝብ ላይ ለ49 ዓመታት ያላቋረጠ እልቆ መሳፍርት ግፍ እንዲፈጸምበት ያደረገው ወንጀሉ አልበቃው ብሎ ፋሽስት ወያኔ ችግር ውስጥ የገባ በመሰለው ቁጥር ከተደበቀበት እየወጣ በአማራ ሕዝብ ላይ ተጨባሪ የጭቃ ጅራፉን እየመዘዘ ይገኛል።
ታምራት ላይኔ የአማራ ሕዝብ አገርና መንግሥት ስለሌለው ብቻ በወንጀል አለመጠየቁን አማሮችን በግፍ ማስጨፍጨፉ፣ በአገራቸው ውስጥ ስደተኛ እንዲሆኑና በአማራነታቸው ብቻ ተወንጅለው እስካሁን ድረስ መድረሻቸው ሳይታወቅ ጠፍተው በቀሩት የአማራ ተወላጅ ምሁራንና አባቶቻችን ሕይወት ተጠያቂ መሆኑ የተረሳለት መስሎታል። በፍጹም! የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም!
ታምራት ዛሬ ላይ ፓስተር ሆኛለኹ ብሎ የሃይማኖት ካባ ቢያጠልቅም በአማራ ሕዝብ ላይ ያለው ጥላቻ ግን ከጌቶቹ ከፋሽስት ወያኔዎች የሚያንስ አይደለም። ከሰሞኑ ፋሽስት ወያኔን ለመከላከል ባሰራጨው የአማራን ሕዝብ ባወገዘበት ቅርሻቱ ግፉአኑን የአማራ ሕዝብ ትግራይን እንደወረረና በትግራይ ላይ ጦርነት እንደከፈተ አድርጎ ከስሶታል።
ግፈኛው ታምራት ላይኔ የአማራን ሕዝብ ትግራይን እንደወረረና በትግራይ ላይ ጦርነት እንደከፈተ አድርጎ በማቅረብ የሚያወግዘው የአማራ ሕዝብ በወሎ፣ በሸዋና በጎንደር ፋሽስት ወያኔ የፈጸመውን የዘር ማጥፋት፣ ውድመትና የጅምላ ፍጅት ለምን ተከላከለ ብሎ ነው።
ተከዜንና አሸንጌን ተሻግሮ የትግራይን መሬት የረገጠ አንድ አማራ የለም። አማራ የኅልውና ተጋድሎ እያደረገ ያለው ፋሽስት ወያኔ በግፍ በወረራቸውና በቅኝ በያዛቸው የወሎና የጎንደር ወረዳዎች ውስጥ ነው።
ግፈኛው ታምራት ላይኔ ግን የመንፈስ አባቱን ፋሽስት ወያኔ በአማራ ሕዝብ ላይ ባካሄደው ውድመትና የፍምላ ፍጅት ባለመርካቱ በታምራት ላይኔ ፍቃድ ፋሽስት ወያኔ በቅኝ በያዛቸው የወሎና የጎንደር ወረዳዎች ውስጥ የአማራ ሕዝብ ከወራሪው የፋሽስት ወያኔ አንበጣ ሠራዊት ጋር እያካሄደ ያለውን የኅልውና ተጋድሎ ትግራይን የወረረና በትግራይ ላይ ጦርነት የከፈተ አድርጎ እየዘመተበት ይገኛል።
ዛሬ አማራው አገርና መንግሥት ስለሌለው ብቻ ታምራት ላይኔ ነጻ ሰው የሆነ ቢመስለውም አማራው አገርና መንግሥት ሲኖረው ግን ዛሬ ፋሽስት ወያኔ በወሎና በጎንደር እያካሄደ የሚገኘውን የጽልመት ወረራ የአማራ ሕዝብ ለምን ተከላከለ ብሎ በከፈተበት የጭካኔ ዘመቻ ብቻ ሳይሆን በመንግሥትነት ተሰይሞ የፋሽስት ወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚ በነበረበት ዘመን በግፍ ስላስጨፈጨፋቸው የአማራ ገበረዎች፣ በአገራቸው ውስጥ ስደተኛ እንዲሆኑ ስላደረጋቸው ሚሊዮን የአማራ ተወላጆችና በአማራነታቸው ብቻ ተወንጅለው እስካሁን ድረስ መድረሻቸው ሳይታወቅ ጠፍተው ስለቀሩት ምሁራንና አባቶቻች ተጠያቂ ይሆን እጁ የኋሊት በመጫኛ ታስሮ እውነተኛ ችሎት ፊት የአማራ ሕዝብ ከሚያቀርባቸው ደመኞቹ መካከል ታምራት ግንባር ቀደሙ ነው። ታምራት ላይኔ በአማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመውንና እየፈጸመ የሚገኘውን ግፍ ግፉአኑ የአማራ ሕዝብ ቢረሳው እንኳን መዝግቦ የያዘው የኢትዮጵያ አፈርና ቅጠል ያስታውሰዋል።