>

ዝክረ ~ ፍቅሩ ኪዳኔ - ከአዲስ አበባ እስከ ፓሪስ...! (በአንተነህ ሲሳይ)

ዝክረ ~ ፍቅሩ ኪዳኔ – ከአዲስ አበባ እስከ ፓሪስ…!

በአንተነህ ሲሳይ


በሀገራችን ብሎም በአህጉራዊ እና ዓለምአቀፍ የስፖርት ተቋማት ውስጥ ጉልህ ሚና ከተጫወቱ ሰዎች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱትን አንጋፋ የስፖርት ጋዜጠኛ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔን ለመዘከር በወዳጆቻቸው ትብብር የተዘጋጀው ልዩ የመታሰቢያ ፕሮግራም ወዳጆቻቸው ሁሉ በተገኙበት  ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም በደማቅ ሥነ-ስርዓት በኢትዮጵያ ኤምባሲ ተካሂዷል፡፡

via- Ethiopian Embassy, Paris, France

* * *

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ታላቁን የስፖርት ሰው ፍቅሩ ኪዳኔን የሚዘክር  ፕሮግራም አካሄደ

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ታላቁን የስፖርት ሰው ፍቅሩ ኪዳኔን የሚዘክር  ፕሮግራም በቦሌ ካሶፒያ ሆቴል አካሂዷል።

በመታሰቢያ ፕሮግራሙ የባህልና ስፖርት ሚንስቴር ዴዕታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት: ሺ አለቃ አትሌት ሀይለ ገብረ ስላሴ: የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አብነት ገብረ መስቀልን ጨምሮ የስፖርት ጋዜጠኞች ተገኝተዋል።

አምባሳደር መስፍን ቸርነት: ፍቅሩ ኪዳኔ በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኝነት ፈር ቀዳጅ የነበረና ለሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎች አርአያ መሆን የቻለ መሆኑን አንስተዋል።  አምባሳደሩ ጨምረውም ፍቅሩ ኪዳኔ የኢትዮጵያ የስፖርት ዲፕሎማት ነበር ብለዋል።

ሺ አለቃ አትሌት ኃይለ ገብረ ሥላሴ ፍቅሩ ኪዳኔ ኢትዮጵያን ለአለም በሚገባ ያስተዋወቀ ሰው ነበር ብሏል።

ፍቅሩ ኪዳኔ ለኢትዮጵያ ስፖርት ጥብቅና የቆመ ሰው ነበር ያሉት አቶ አብነት ገብረ መስቀል በበኩላቸው የስፖርት ጋዜጠኞች የዕርሱን አርአያ መከተል እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ንዋይ ይመር ለስፖርቱ ተቆርቋሪ የነበረና  የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር  እንዲጠናከር የለፋ ታላቅ ሰው አጥተናል ብሏል።

የኢትዮጵያ  የመጀመሪያው ስፖርት ጋዜጠኛ  ፍቅሩ ኪዳኔ በሀገር ውስጥ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ   እና በኢትዮጵያ ብስክሌት ፌደሬሽን በዋና ጸሀፊነት እንዲሁም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ሆነው ተሰርተዋል።

በተለያዩ የአለም ሀገራት በመዘዋወር  የሀገራቸውን ስም ያስጠሩት ፍቅሩ ኪዳኔ

ከሀገር ውስጥ ተቋማት በተጨማሪ አለም አቀፍ  የስፖርት ተቋማትን በሀላፊነት መርተዋል።

በአለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በሚታተመው መጽሄት ዋና አዘጋጅ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በስፖርት ጋዜጠኝነትም በፈረንሳዩ ሊኪፕ ጋዜጣም ተሰርተዋል።

በመርሀ ግብሩ ታላቁ የስፖርት ሰው በህይወት ዘመናቸው የሰሯቸውን ስራዎች የተመለከተ ዘጋቢ ፊልምም ቀርቧል።

በአዲስ አበባ የተወለዱት ፍቅሩ ኪዳኔ ባሳለፍነው ሳምንት በ87 አመታቸው ህይወታቸው ማለፉ  የሚታወስ ሲሆን የቀብር ስነ ስርአታቸውም በዛሬው ዕለት በፈረንሳይ ሀገር ተፈጽሟል።

Filed in: Amharic