>
5:13 pm - Thursday April 19, 3145

ሕጋዊነትን እየተላበሰ የመጣው የኦሮሞ ወረራ (ጌጥዬ ያለው)

ሕጋዊነትን እየተላበሰ የመጣው የኦሮሞ ወረራ

(ጌጥዬ ያለው
በወራሪው ኦሕዴድ-ብልፅግና መሀንዲስነት በወለጋ በአማሮች ላይ እየተፈፀመ ያለው የዘር ማፅዳት ዛሬም እንደቀጠለ ነው። በሶስት  ወራት ውስጥ የተገደሉ አማሮችን ቁጥር እንደናሙና ወስደን ስናሰላው በሳምንት በአማካኝ 60 አማሮች ይገደላሉ። ከሰሞኑ በምስራቅ ወለጋ 18 አማሮች በግፍ ተገድለዋል፤ 42 አማሮች ታግተዋል። ከሟቾች መካከል አንዱ በአካባቢው የተከበሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ቄስ ናቸው። ግፈኞች ከገደሏቸው በኋላ አንገታቸውን እና ብልታቸውን ቆርጠው በፌስታል በመክተት ሆዳቸው ላይ አስቀምጠው ተገኝተዋል። ይህ የተለመደ እንጅ የሚገርም አይደለም። ከዚህ ቀደምም የመረሩ የጭካኔ አይነቶችን ሰምተናል። ለአብነትም ከጅምላ ጭፍጨፋ አምልጠው ደብረብርሃን የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ የደረሱ የወለጋ  አማሮች የሟች ቤተሰቦቻቸው ደም በገዳዮች እንደ ዉሃ ሲጠጣ እና ስጋቸው ተዘልዝሎ ሲበላ ማየታቸውን ማስታወስ በቂ ነው። ለዚህም ነው በቄሱ ላይ የተፈፀመው ድርጊት ዘግናኝ ቢሆንም እምብዛም ያላስገረመን። እዚህ ላይ ኦሮሞ ለመጀመሪያ ጊዜ የፅሁፍ ታሪክ እንዲኖረው ያስቻሉትን የአባ ባህርይ አባባል መጥቀሱ ጭካኔው የአባት መሆኑን ያስረዳል። አባ ባህርይ የኦሮሞ የጭካኔ ጥግና የባህርይው እንስሳዊነት አስደንቋቸው መፅሀፋቸውን እንደፅሀፉ ጠቅሰዋል። ይህንኑ የ16ኛው ምዕተ አመት እንቅስቃሴ ዛሬም ስጋ ለብሶ ከእነ ሙሉ ቁመናው እያየነው ነው። ልዩነቱ በዚያ ዘመን የኦሮሞ ቀዳሚ ጠላት ተደርጎ የተፈረጀው ሲዳማ በመሆኑ ወረራው “ሲዳሞን ግደል” በሚል መጠሪያ ነበር ሲዘምት የነበረው። በገዳዮች እሳቤ ሲዳሞ ኦሮሞ ያልሆኑ ማንኛቸውንም ኢትዮጵያውያን ያጠቃልላል። በዚህ ዘመን ደግሞ በጠላትነት የተፈረጀው አማራ በመሆኑ “ነፍጠኛን ስበር”  በሚል መርሆ ኦሮሞ ያልሆኑትን ሁሉ የማፅዳት እንውስቃሴው ከተጀመረ እነሆ አራት አመታት አለፉት። ለጊዜው አማራው የወረራ እንቅስቄሴውን የሚገታ ስለመሰለው በትር ቢያበዛበትም ቀጣዩ የዘር ማጥፋት እንቅስቃሴው ኦሮሞ ባልሆኑት ላይ ሁሉ በየተራ ይቀጥላል። እስከ አሁንም ቸል የተባሉት ከአንድ ወር ዘመቻ የዘለለ አያደክሙንም ከሚል እሳቤ ነው። ለዚህ ያመች ዘንድ ደቡብ ኢትዮጵያ አስቀድሞ ተሸንሽኗል። ትግሬ ዘላቂ ጦርነት ውስጥ እንዲኖር ብልፅግናው ወስኖለታል። ሶማሌውን ቢቻል ለማጥቃት ባይቻል ለመሸኘት ኦሕዴድ ፈራሁ ተባሁ ማለት የጀመረው ገና ለማ መገርሳ ሳያኮርፍ ነበር። የሙስጠፋ ኡመር ክፍለ አገዛዝ አልሸባብን በመከላከል ሰበብ ከሀገረ ሶማሊያ ጋር በመደራደር ከወዲሁ ሀገርነት እንዲሰማው ቦይ ተቀዶለታል።
ወለጋ የአማራ መታረጃ ቄራ የሆነው ወራሪው ኦሕዴድ-ብልፅግና አማራን በማጥፋት ኢትዮጵያን የመበተን ብሎም የራሱን ሽራፊ ሀገር የመመስረት አላማ ስላለው ነው።   ከወራት ወዲህ ደግሞ ጭፍጨፋ እና ወረራው ከወለጋ ወደ ሸዋ ተስፋፍቷል። በተለይም በምዕራብ ሸዋ፣ በምስራቅ ሸዋ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ የኦሮሞ ወራሪ ሰራዊት አዳዲስ የጦር መሰረቶችን በመገንባት ላይ ይገኛል። ቡድኑ በኢትዮጵያ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት በሽብርተኝነት ቢፈረጅም ኦሕዴድ ከባንኮች እና የጦር ማሰልጠኛ ማዕከላት በተጨማሪ  ሙሉ ከተማ ከፍቶ እየሰጠው አንድ ጥይት ሳይተኩስ መቆጣጠር ጀምሯል።
ይህ ወራሪ ቡድን ከሰሞኑ በአማሮቹ በእነ አፄ ዳዊት እና በእነ እምዬ ምኒልክ የእጅ ሥራ በአዲስ አበባም መስፋፋት ጀምሯል። ለመዲናዋ ወጣቶች አገልግሎት ይሰጣሉ ተብለው የተገነቡ የንግድ ሸዶችም የኦነግ ሰራዊት ማሰልጠኛ እና የጦር መሳሪያ ማከማቻ ሆነዋል። ውስጥ አዋቂ የመረጃ ምንጮች እንዳረጋገጡት በተለይም በአምስት ቦታዎች የጦር ታላላቅ የጦር ማዕከላትን ገንብቷል። እነርሱም፦ በለቡ ሃይሌ ጋርመንት፣ በአቃቂ ወረዳ 6፣ በኮዬ ፈጨ ወረዳ 9፣ በየካ አባዶ እና በፈረንሳይ ለጋሲዮን የሚገኙ ናቸው። በኮዬ ፈጨ የሚገኘው ማዕከል ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመሳሪያ ድጋፍ ተደርጎለታል። ይኸውም የፖሊስ ኮሚሽኑ አባላት የታጠቁትን ጠመንጃ “ጠፋብን” በማለት ለኦነግ ጦር ያቀብላሉ። “እንዳይደገማችሁ” በሚል የይስሙ ትችት ይታለፋሉ። ይህ የዕለት ከዕለት ተግባራቸው ሆኗል። ነገሩ ውስጡን ለቄስ ነው! በአንፃሩ የአማራ ተወላጅ የፖሊስ አባላት ከፕላስቲክ በትር በቀር መሳሪያ እንዳይታጠቁ ተከልክለዋል። ይህ አዲስ አበባ ዳርቻ በሚገኙ የተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ገቢራዊነቱ ቀጥሏል።
ለአዲስ አበባ ወጣቶች የተሠሩ የንግድ ሸዶች ሰው እንዳይቀርባቸው ዙሪያቸውን ታጥረውና ከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ እየተደረገላቸው የኦነግ ጦር ማሰልጠኛ ሆነዋል። እንቅስቃሴው ሲጀመር የቴኳንዶ ስፖርት ሥልጠና በሚል ሽፋን ቢሆንም ከሰሞኑ ግን ወታደራዊ እንቅስቃሴው በገሀድ እየታየ ነው። አሸባሪው የኦነግ ጦር በመሀል ከተማ ውስጥ እንደ ሕጋዊ ድርጅት፤ ያውም መንግሥታዊ ሥልጣንን በተቆጣጠረው አገዛዝ እየታገዘ ሥልጠናውን ቀጥሏል። አዲስ አበባን እንደ ባግሕዳድ ማለትስ አሁን ነበር!
ለወታደራዊ ስልጠና እያገለገሉ ካሉ የንግድ ሸዶች መካከል ሀና ማርያም፤ ወረዳ 11፤ ቆጣሪ ትምህርት ቤት ጀርባ የሚገኘው ሸድ ይጠቀሳል። ጀሞ አንድ መድኃኔዓለም አካባቢ የሚገኙ ቤቶች ተመሳሳይ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየተደረጉባቸው ነው።
በቱሉ ዲምቱ ኦሮሞዎችን ሰብስበው የሚያሰለጥኑት ትግርኛ ተናጋሪ ወታደሮች መሆናቸውን ስናስብ አማራን ለማጥፋት እየተደረገ ያለውን የእሳት እና ጭድ የርኩሰት ጋብቻ ያሳየናል። ይህ ሁሉ ስልጠና እና ወረራ አማራን ለማጥፋት ብሎም ኢትዮጵያን ለመበተን ያለመ ነው። ለመሆኑ የአማራ ጥላቻ እንዴት እና ከየት ተጀመረ?
አማራን የማጥፋቱ ውጥን የአድዋ ድል ከወለደው አዲሱ የዓለም ፖለቲካ የሚጀምር መሆኑን ታሪክ ያስረዳናል። ጣልያን ኢትዮጵያን ለመውረር እና ቅኝ ግዛቷ ለማድረግ በመጣች ጊዜ በ1888 ዓ.ም. አድዋ ላይ በእምዬ ምኒልክ ሰራዊት ድል ሆና ስትመለስ ከፍተኛ ቂም የቋጠረቺው በአማራው ላይ ነበር። ጉዳዩም የኢትዮጵያ እና የጣልያን ጉዳይ ከመሆን አልፎ በመላው ዓለም የሚኖሩ ጥቁሮች እና ነጮች ፖለቲካ ሆነ። የአድዋ ድል ነጮች ከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ እንዲያላጋቸው አድርጓል። ለፓን አፍሪካንዝም ንቅናቄዎች ችቦ ሙሉ ወጋገን አብርቷል። ነጭ በጥቁር መሸነፍ እንደሚችል፤ ጥቁርም በዓለም ዙሪያ ዘሩን አስከብሮ በእኩልነት መኖር እንደሚችል እምዬ ምኒልክ አሳይተዋል። በመሆኑም ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በርካቶች ጸረ አማራ ትርክትን በጠንሰስ ጀመሩ። ይህ ሁሉ የሆነው ጣልያን በኢትዮጵያ ተሸነፈች ከሚለው ጥቅል የአውሮፓ እና የአሜሪካ ጋዜጦች ጀርባ ነው። ጥላቻው የተጀመረው የተሸነፉት ኢትዮጵያ ከሚለው ጥቅል ስም በተጨማሪ በትክክልም በአማራ መሆኑን አጥንተው ስለደረሱበት ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስን ከመንበሩ አስነስታ ያዘመተቺው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም የድሉም ሆነ የጥላቻው ተጋሪ መሆኗ አይዘነጋም። ከዚህ እሳቤ የመነጨው የመጀሪያው አማራ ጠል ሰነድ አንድ ኦስትሪያዊ ፈረንጅ የፃፈው መፅሐፍ ነው። ይህንን ሰነድ ጣልያን በከፍተኛ ደረጃ ስትጠቀምበት ቆይታለች። ልጆቻቸው፣ ባሎቻቸው፣ ወንድሞቻቸው እና አባቶቻቸው አድዋ ላይ ያለቁባቸው ጣልያናውያንን እንባ ማበሻ አድርጋዋለች። የእምዬ ምኒልክን በሕይዎት አለመኖር አጢና፤ ቂሟን አጠጅታ ከአርባ አመታት በኋላ ኢትዮጵያን ለመውረር ስትመጣ በተናጠል አማራውን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለማጥፋት የመርዝ ጭስ ሳይቀር ታጥቃ ነበር። በአምስት አመቱ የወረራ ጊዜዋም  ኢትዮጵያን በአምስት ጠቅላይ ግዛቶች ሸንሽና ስትወር “የጋላ እና ሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት” ብላ ባዋቀረቺው ክፍለ ግዛት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 800 ሺህ አማሮችን “መጤናችሁ” ብላ አባራለች። ዛሬ የተስፋፋው በየ’ክልሉ’ አማራን የማፈናቀል እና የማሳደድ  እንቅስቃሴ የተጀመረው በዚያን ጊዜ ነው። ኦስትሪያዊው ደራሲ እና ፋሽስት ጣልያን በቅብብሎሽ ያስፋፉት ጸረ አማራ ትርክት በሃይማኖት ሰበብ በኢትዮጵያ ዘመን አመጣሽ ትምህርት ቤት ተገንብቶለት ሀገር በቀል ወራሪዎችን መፍጠሩን ቀጠለ። ትምህርት ቤቱ በአዲስ አበባ እና በሌሎች አካባቢዎች እንዳይከፈት ማዕከላዊ መንግሥቱን የሚመሩት ንጉሠ ነገነሥት ባስተላለፉት መመሪያ መሰረት የኢትዮጵያ ነገሥታት ከለከሉ። ሆኖም ዘወትር ከጠላት ጋር ማበር መለያቸው የሆነው የትግራይ መኳንንት ንጉሠ ነገሥቱን ሸሽገው በአድዋ አንድ የሚሽነሪ ትምህርት ቤት አስገነቡ። እድሜ ጠገብ የወያኔ ባለሥልጣናት በአብዛኛው የዚህ አስኳላ ፍሬዎች ናቸው። ከእነ ስብሀት ነጋ የቀጥተኛ ትምህርት ጀምሮ እስከ አብይ አሕመድ ድረስ ከትምህርት ቤቱ በመነጨ ጸረ አማራ አመለካከት ጠያይም ጣልያናውያን ተፈለፈሉ።
የትግሬ ወንበዴዎች በለስ ቀንቷቸው ምኒልክ ቤተመንግሥት ሲገቡ በተራቸው ዛሬ የኢትዮጵያን ሀገረ መንግሥት የተቆጣጠሩትን የኦሮሞ ኩታራዎች በጦር ምርኮኝነት ያዙ። ምርኮኞችን ተሰብስበው ሸዋ፤ ደራ ላይ ኦሕዴድ-ን መሰረቱ። ኦሮምኛ ተናጋሪው ወያኔ መሆኑ ነው። በዚህ ሁሉ የታሪክ ሂደት ከትውልድ ትውልድ እየተቀባበሉ የተማሩት አማራን እንዴት መጥላት፣ ማጥቃት ብሎም ማጥፋት እንደሚቻል ነው። በሚሽነሪ በቀጭን መስመር ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ ሲሰራጭ አማራን የመጥላት ፖለቲካ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ የውርጋጥ ተማሪዎች እንቅስቃሴ በሩ ወለል ብሎ ተከፍቶለት ገባ። ሃይማኖት አልቦነት፣ የባህል ወረራ፣ የቋንቋ ድምሰሳ ተስፋፋ።  በይፋ አማራን በጠላትነት የፈረጁ ድርጅቶችም እንደ አሸን ፈሉ። አማራው ስለሌሎች መብት መከበር የባርያ ነፃ አውጭ ድርጅት ሲመሰርት አጥፊ ድርጅቶች በላዩ ላይ ሰለጠኑበት። በውጭ ወራሪዎች እየታገዙ ኢትዮጵያን፣ የንጉሠ ነገሥት መንግሥቷን እና ሃይማኖቷን ከመበጥበጥም አልፈው ቤተመንግሥቱን ተቆጣጠሩ። እነኝህ ጸረ አማራ ሃይሎች ሥልጣን ይዘው ማጥቃት ከጀመሩ እነሆ 48 አመት ሞላቸው። ደርግ ፊውዳል እያለ በከስክስ ጫማው የረገጠው አማራ፤ወያኔም ከመግደል አልፎ ትምክህተኛ እያለ በወሊድ መከላከያ ክኒን አመከነው። የመከኑትን ሳይጨምር ከስድስት ሚሊዮን በላይ አማሮች በወያኔ በግፍ መገደላቸውን ጥናቶች ያመለክታሉ። ይህ ቁጥር ከዛሬው የትግሬ ጠቅላላ ቁጥር ጋር የሚስተካከል ነው፤ከአዲስ አበባ ድምር ኗሪ ጋር ይቀራረባል። ከሀረሪ አንፃር ሲሰላ ከ2 ‘ክልል’ በላይ ይወጣዋል።
የህዝብን ትግል ጠልፎ በክህደት የእምዬ ምኒሊክን ቤተ መንግስት የተቆጣጠረው ምርኮኛው የኦህዴድ ቡድንም ነፍጠኛ እዬለ አማራውን በጅምላ እየጨፈጨፈው ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ የአማራን ህዝብ መሪ አልባ እና ድርጅት አልባ ለማድረግ ብሎም የሚያርፍበት ግዛተ መሬት እንዴይኖረው እየተሰራ ይገኛል። ይህ ሀገር መስራች ጠቢብ ህዝብ አውራ የሌለው ንብ ሆኖ፤አውራ ባለው የዝንብ መንጋ እየተነደፈ ነው። በመሆኑም ከዚህ የመጥፋት አደጋ ለመትረፍ ፈፅሞ ያልጠፉ መሪዎቹን መጠበቅ ይኖርበታል። ቀዳሚው ተግባር ከስልሳ ሚሊዮን የሚበልጡ አማሮች መሪ የሆነውን አርበኛ ዘመነ ካሴን በአስቸኳይ ከግፍ እስር ማስፈታት ነው።
Filed in: Amharic