>

የአፄ ቴዎድሮስ  በውጭ ዜጎች አንደበት...! (መካሻ ድንቁ)

የአፄ ቴዎድሮስ  በውጭ ዜጎች አንደበት…!

መካሻ ድን

ሔነሪ ፕላንክ ፦ በተለያዩ ቦታዎች እየሰፈሩ ንፁህ አየር መሳብ የሚወዱ፤ማንበብ የሚወዱ፤ ልዩ የማስታወስ ችሎታ ያላቸው ከወራት በፊት ከአመታት በፊት ለተላከላቸው ደብዳቤዎች በትክክል አስታውሰው መልስ የሚሰጡ፤ ማልደው መነሳት የሚወዱ፤

~

ዱፋታን፦ አፄ ቴዎድሮስ ድሆችን ራሳቸው እየተቆጣጠሩ ይጠብቃሉ፤ ድኳናቸው በተተከለበት ሁሉ የድሆችን አቤቱታ ማደመጥ ይወዳሉ፤ ሁሌም ስራ ከመጀመራቸው በፊት የድሀን አቤቱታ ይሰማሉ፤ በጉዞ ላይ በሳምንት በሺሆች የሚቆጠር ብር ለድሆች ይሰጣሉ፤

~

ሔነሪ ብላንክ ፦ በምግብ በኩል የማይስገበገቡ በቀን አንዴ ብቻ መብላት የሚወዱ በጾም ወቅት እንጀራ ህምእህል ወጥ በፍስክ አሳና የስጋ ወጥ ይበላሉ፤

~

ዎልዲሜር ፦ አንድ ቀን ከአፄ ቴዎድሮስ ጋር በየባላገሩ ስንዘዋወር አንዲት ደሀ ሴት ምንም ልብስ ያለበስች አጋጠመን ንጉሱም ከበቅሏቸው ወርደው የለበሱትን ሸማ እና በርከት ያለ ገንዘብ ሰተው ሰደዷት

~

ፕላውዴን ፦ የባሪያ ንግድን አጥብቀው የሚቃወሙ ናቸው ፣የተሸጡ ባርያዎችን እሳቸው እንደገና እየገዙ ነፃ ያወጧቸው ነበር ፣

~

ዎልድሚር፦ ብዙ መቶ ባሪያወችን ነፃ አስወጥተው እነዚህን ወጣቶች ጥበብ እና ሀይማኖት አስተምራቸው የሚያስፈልገውን ሁሉ የምችለው እኔ ነኝ ብለውኛል

~

ሄነሪ ፕላንክ፦ አፄ ቴወድሮስ ሽጉጣቸውን በትራሳቸው ሳያደርጉ። እና የተለጓመ መሳሪያ ከአጠገባቸው ሳያስቀምጡ አይተኙም ነበር።

Filed in: Amharic