ኤርሚያስ :-ተሻሽሎ የቀረበው የበረከት እና የሴኮ ቱሪ ቨርዥን
አሸናፊ
ወያኔ መራሹ ኢሐዴግ ግፎችን በማጋለጥ ከፍተኛ ውለታ ከዋለልን መካከል ግንባር ቀደሙ ኤርሚያስ ነው። የተንኮላቸው ጥግ ተተርትሮ መጨረሻው አልጋ ላይ አብረህ የምትተኛው ባለትዳርህ ድረስ እንደሚደርስ ያረጋገጠልን ሰው ነው። አዲስ ነገር ጋዜጣ በተወሰነ መልኩ የህወሀት መራሹ ተንኮል አይናችንን ብትገልጥልንም እንደ ኤርሚያስ ግን ራቁታቸውን ያስቀራቸው የለም። በተለይ ቀድመን ነቅተን ሌላውን ለማንቃት የምንጥር ሰዋች እኛን ለማመን ይከብዳቸው ነበር። የኤርሚያስ መጽሀፍ ግን የወያኔን ግፍ ያረጋገጠልን ምርጥ ማስረጃ ነበር። ያነበበ አወቀ ያወቀ ተጠቀመ በሚለው መርህ አባሎቻቸውን አስክረን ግራ እንዲገባቸው ከማድረግም በላይ በነፉሳቸው ነው የተጫወትንባቸው። ስንቱን ጓደኛ መሳይ ተላላኪ ካድሪ ልኩን ያሳየንበት የኤርሚያስን መጸሀፉ አንብበን ነው። ከዚያማ እንኳን ሲነኩን ሲዞሩን ባነንባቸው። ለዚህ ውለታው ኤርሚያስ ከፋ ያለ አክብሮት አለኝ።
ወደ ተነሳሁበት ነጥቤ ልመለስ ። ኤርሚያስ የለውጡ ሰምን ዶ.ር አብይን ወደላይ በመስቀል ግንባር ቀደሙ ነበር እንደውም በተወሰነ መልኩ የዶር አብይ መካሪ እንደሆነ በጽንፈኞቹ አቤቱታ ይቀርብበት ነበር። ትንሽ ከረም አለና ውሎ አዳሩ በእግሩ ያልቆመውን የአብይ መንግስት ልክ 27 አመት እንደቆየው ህወሀት መራሹ መንግስት ይነርተው ጀመር። ቀጠለና ከጎኑ ያልቆሙቱን የሙያ አጋሮችን ስም ማጥፋት ተያያው።
አንድ ብሎ ህገመንግስቱን ቀዳዶ ይጣለው አለ። አይ አሁን ባለበት ሁኔታ ይሄን ማድረጉ በተለይ ለኦነጋዊያን እና ለህወሀት መንገድ መስጠት ነው ሲባል። መሳደብን ቀጠለ ። ከረም አለና አዲስ አበባ ቤቴ ዜማ ጀመረ ኦሮሙማ ሆነ ትርክቱ ።እስክንድር ደጋፊ ነኝ ብሎ ታኮ ኢትዬጵያዊ ነኝ የሚለውን ለመሳደቢያ ተጠቀመበት። ከዚያ ምርጫ ላይ አነጣጠረ ። ምርጫ ላይ የተሳተፉትን ያጥረገርግ ገባ። በስድብ ሲሞሸልቀው የከረመውን ልደቱን ሀሳብ ገዝቶ የሽግግር መንግስት አቀንቃኝ ሆነ ። ትህነግን ከትግራይ ህዝብ ጋር አንድ አድርጎ በጦርነት አይሸነፉም ስለዚህ ሽግግር መንግስት አይነት ጭውቴም ጀመረ በአስራ አምስት ቀን መቀሌ ሲገባ ጀኖሳይድ አጀንዳ ስቦ ቁጭ አለ። እንደውም ጦርነቱን አብይ እንደጀመረው አይነት መረጃ መሳይ ይዞ ይተነትን ጀመር። ትንሽ ቆየና የኢትዬጵያ መንግስት ወደ አማራ ክልል ሲገባ ተሸንፎ ነው እያለ ይንደቀደቅ ጀመር ።ትህነግ እስከ ሰሜን ሸዋ የሰራችውን ግፍ ማንሳት አይፈልግም። ግን ደግም የአብይ ለመቃወም የጠቀመው ከመሰለው አውቆ ነው የአማራን ህዝብ ሒሳብ ማወራረጃ ያደረደረገው ይልሀል።
ከረመና መንግስት በማይቆጣጠረው ሀገር ስልክም ባንክም መብራትም መስጠት አለበት እያለ እየዬ ሆነ እረ እንዴት ሊሆን ይችላል ሲባል ጀኖሳይድ ይልሀል ። በየቀኑ ብርሀኑን አንዳርጋቸውን ኑአሚንን አለማሪያምን አብይን ሙስጠፌን የቀረው የለም ከነ ርዪት ጋር አጀንዳ በመቀባቀል ማዋረድ ። ትናንት ጀግና ሲለው የነበረውን ዛሪ ከኔ ጋር ሀሳብ አልገጠመም ብሎ ማዋረድ ነው ስራው::
ኤርሚያስ ከጦርነቱ በፊት የነበረው የፕሮፓጋንዳ ስትራቴጂ ወያኔን ጀግና ማድረግ ጦርነት እንደማይጠቅም መደራደር ወሳኝ እንደሆነ ከዚያ ውጭ በአማራ እና በአብይ መንግስት መካከል ልዪነት መፍጠር ነበር። ፋኖ ተገደለ ሞተ አማራ በየቦታው ታረደ ሀገር ደከመች አልቃይዳ ገባ ሱዳን መሪት ወሰደች እየዬ ነው ማጠንጠኛው ኦሮሙማ የአብይ መንግስት ሀገር ሊበትን ነው ይልሀል።
የፕሮፓጋንዳው አላማ የአብይ መንግስት ቅብልነት እንዳይኖረው ማድረግ ነው። ዘመነኛ ካሴ ጀግና ይልሀል ለምን ከአብይ ተቃራኒ ስለቆመ። መአዛ አንበሳ ይልሀል።ጎበዜ ጀግና ይልሀል። ኢትዮጵያ ቢያሳጣውም ደንታ የለውም አብይን ከመቃዋም ወደ ኋላ አይልም። ፓለቲካ አልገባውም እንዳልል የጉርምስና ዘመኑን የፈጀበት ነው። ግራ ያጋባል።
ሰላም ዋና ነው ብሎ አብይ ሰላም አይፈልግም ይልሀል ። ወያኔ ያስቀመጠችው ቅድመ ሁኔታ አይታየውም። እራሱን በአብይ ቦታ አድርጎ የቱን መመለስ የቱን መተው እንዳለበት መናገር አይፈልግም ። ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ባንክ ይለቀቅላቸው ይላል። የወያኔን ባህሪ እያወቀው። ስልክ ዋና ነው ይልሀል ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ያለስልክ እንደሚኖር እያወቀው። መቼም እያሸበረ ገንዘብ ስጡት መብራት ስጡት ስልክ ስጡት የሚባልለት ሀገር ትፍረስ የሚለው ወያኔ ጠፍቶት ከይደለም። ብቻ የትግራይ ህዝብ ተበደለ ይልሀል ልክ አማራጭ እንዳጣ። ልንገርህ ያሁላ ግፍ ተሰርቶበት የወሎ ህዝብ ዛሪም ከትግራይ ወንድሞቹ ጋር አብሮ ይኖራል። አዲስ አበባ አያት ሀያሁለት አራብሳ ጀሞ አዳማ ነቅሎ የመጣው የትግራይ ህዝብ አይታየውም። ቢያንስ የትግራይ ህዝብ ሌላ አማራጭ እንዳለው አይታየውም። ህወሀት አሸንፋ አዲስአበባ ብትገባ የሚመጣው ስርአት አይታየውም ። ሌላው ህዝብ እነሱን ከማጥፋት ውጭ አማራጭ እንደሌለው አይታየውም። ይችን ከአብይ ድክመት ጋር ለውሶ ኢትዮጵያ ሊያሳጣን ይውተረተራል። 85% አብይን ይሳደባላ ወያኔ እንዳይባል10% ህወሀት ይሳደባል። አስገራሚ ነገር እኮ ነው። ከረመና አብይ በዚህ ጦርነት አሸናፊ የለም አለ ብሎ ከአውድ ውጭ ተርጉም የአማራ ህዝብ አትዋጋ እያለ ይቀሰቅስ ጀመረ ፍኖ ታስሮ ምናምን እያለ ቀወጠው። ቆቦ ስትያዝ እልል በቅምጤ አለ ። ወያኔ ባለበት ስትቆም ስትወቃ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣት አለቀ ይልሀል። ኤርትራ ከአብይ ጎን በመቆሟ ኢሳያስ ላይ ኡኡ ነው ። ትህነግ ኤርትራ እና ኢሳያስ ላይ ያላትን አቋም ለደቂቃ ማሰብ አይፈልግም። ቢያንስ ሚሳኤል እንደተተኮሰባቸው እራሳቸውን የመከላከል መብት እንዳላቸው ማሰብ አይፈልግም። አሁን ደግም ወያኔ ከሞተች የሀይል ሚዛን የሚያስጠብቅ የለም ፋኖ አለቀልህ ይልሀል ።
ታዲያ ይህ ሁላ ሲጠቃለል የኤርሚያስ አላማ ምንድን ነው ብለህ ብትጠይቅ በኢትዮጵያ ስም የተሸፈነ የወያኔ የአማርኛ ፕሮፓጋንዳ ክፍል መሪ ሆኖ ታገኘዋለህ። አላማው እንደ ቀድም አለቆቹ የሴኮን እና የበረከትን ስራ አሻሽሎ በተቃዋሚ ካባ ለብሶ ወደ ቀድሞ ስራው በመመለስ ወያኔን መርዳት ነው ። አዋን ኤርሚያስ ወደ ህወሀት የኮሚኒኬሽን ስራው ከተመለሰ ወራቶች ተቆጥረዋል ።አሁን ኤርሚያስ የተሻሻለ የበረከት እና የሴኮ ቨርዥን ነው።
ግን ያተርፉ ይሆን?