>

ታዴዎስ ታንቱ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ችሎቱ ሳይሰየም በከንቱ ተመለሱ (ጌጥዬ ያለው)

ታዴዎስ ታንቱ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ችሎቱ ሳይሰየም በከንቱ ተመለሱ

ጌጥዬ ያለው
ሐቀኛው ጋዜጠኛ እና የታሪክ ፀሀፊ ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ በቀጠሯቸው መሰረት ዛሬ ጥቅምት 14 ቀን ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ችሎቱ ሳይሰየም ቀርቷል። በአምስት ተደራራቢ የሽብር ክሶች የቀረበባቸውን የሀሰት ክስ እየዳኘ የሚገው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ያልተሰየመው በቀደመው ክርከር ላይ ከዳኞች በቃል የተነገረው ቀጠሮ ለጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚል ቢሆንም ዳኞቹ ዛሬ ሲጠየቁ ግን “ለጥቅምት 15 ነው የቀጠርነው” በማለት ስለካዱ ነው።
ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ቀጠሮው ለዛሬ ነው በሚል አዛዎንቱን ጋዜጠኛ ይዟቸው ቀርቦ ነበር። በተመሳሳይ ጠበቆቻቸውም ቀርበዋል። ሆኖም ከላይ በተጠቀሰው ምክንያት ችሎቱ ሳይሰየምና መዝገቡም ሳይገለጥ በከንቱ ደክመው ተመልሰዋል። ይህም የግፍ እስረኛውን የተፋጠነ ፍትሕ የማግኘት መብት በእጅጉ የሚጎዳ ነው።
Filed in: Amharic