>

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ  ጸረ ሀይማኖት ንግግር አንድምታው...! (አክሊሉ ደበላ)

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ  ጸረ ሀይማኖት ንግግር አንድምታው…!

አክሊሉ ደበላ


“የአይሁድና የአረብ ስም ሀገር እየወሰዱብን ነዉ። ሀገራችንን አጥለቅልቋል። እነዚህ ሃይማኖቶች ከኦሮሙማ በላይ እንዳልሆኑ ሊታወቅ ይገባል” ይገኝበታል።

*.. ቤተክርስቲታኗ “የምታጠምቃችሁ ኦሮሙማችሁን፣የኦሮሞ ማንነታችሁን ልታጠፋባችሁ፣መጠሪያችሁን ቀይራ የሰሜኑ ልታደርግባችሁ ነዉ”

ክልል ይዞ እንደ ሀገር እህት ማድረግም ነገ የታቀደ አገር አፍርሶ በፍርስራሹ ላይ ክልልን አገር የማድረግ ሰይጣናዊ ሴራ መኖሩን ያሳያል

የመጀመሪያዉ ነገር ኦሮሚያን እንደ ሀገር የመግለፅ አዝማሚያዉ “ሀገር እየወሰዱብን…ከኦሮሙማ አይበልጡም” በሚሉት ማጫፈሪያ ተንፀባርቋል። የሀገሪቱ ህግ በክልልነት የሚያዉቀዉ መሆኑን ማስታወስ መልካም ነዉ።

ሁለተኛዉና ወደ ሃይማኖታዊ ጉዳዩ ስንመጣ፦

በአረብ የተገለፀዉ የእስልምና በአይሁድ የተገለፀዉ የክርስትና ስሞች መሆናቸዉን እንረዳለን። ነገሩ በተወሰነ መልኩ የዛሬ ንግግር ብቻ ሳይሆን የትናንትም ፍትጊያ ያለዉ ነዉ። በኦሮሚያ ክልል ያሉትን የብዙ ቦታዎችን የሥም ለዉጥ አምጥተዋል። በዋናነት ኢላማ የተደረጉት ግን በኦርቶዶክስ ቅኝት ተሰይመዋል የተባሉት ቦታዎች ናቸዉ። ለምሳሌ ደብረዘይት፣ናዝሬት፣ዝዋይ ወዘተ። እነዚህ ሁሉ ዛሬ መጠሪያቸዉ ተቀይሯል። ውስጣዊ ምክንያቱ በሚጠሉት ሃይማኖት ቅኝት የመሰየማቸዉ ነገር ሲሆን ዉጫዊ ምክንያቱ ግን ኦሮሙማን ማለምለም ስለተፈለገ የሚል ነዉ። ይሁን ተባለ።

ነገር ግን በሀገር ወራሪነት፣ በማንነት አፍራሽነት የሚከሷትን ቤ/ክ በዚህ ብቻ ሊያሳርፏት አልፈቀዱም። ደርሰዉ ለትዉልዱ “የምታጠምቃችሁ ኦሮሙማችሁን፣የኦሮሞ ማንነታችሁን ልታጠፋባችሁ፣መጠሪያችሁን ቀይራ የሰሜኑ ልታደርግባችሁ ነዉ” እስከ ማለት ደረሱ።ማጉረምረሙ ግን አልቀረም።  “,ታዲያ የስም ጉዳይ ሲመጣ እንዴት የኦርቶዶክሱ ብቻ ታያችሁ? ሌላዉስ በቁራን ስም ሲጠራ ኦሮሙማዉን ተነጠቀ ለምን አላላችሁም?”  የሚል ማጉረምረም ከኦርቶዶክሳዉያኑ ተሰማ።

እንግዲህ ይህን ታሳቢ አድርገዉ ይሆናል ሁለቱንም ኢላማ ማድረጋቸዉ። ግን በንግግራቸዉ ውስጥ የሳቱት አንድ መሠረታዊ ስህተት አለ። “እነዚህ ሃይማኖቶች ከኦሮሙማ አይበልጡም” የሚለዉ ትልቅ ስህተት ነዉ።

እኔ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ነኝ። በሀገር አንድነት አምናለሁ። ነገር ግን ከሃይማኖቴ የሚበልጥብኝ ምንም ነገር የለም። እንኳንስ ኦሮሙማ ኢትዮጵያዊነቱ ራሱ ከኦርቶዶክስነቴ በታች ናቸዉ።

ይህ የአማኝና የፈጣሪ ግንኙነት በፖለቲካ ይሁንታ የሚፈጠር ሳይሆን የሕይወታችን መሠረታዊ ዉል ነዉ። ስለዚህ ኦሮሙማዉ ከሃይማኖቶቹ በታች መሆኑን ቢረዱ ጥሩ ነዉ።

ሌላዉ ጉዳይ፦

ለምን በዚህ ልክ ብሄርተኝነታቸዉን የሃይማኖት ተቃርኖ አድርገዉ ማላተም እንደፈለጉ አይገባኝም። በኦሮሙማ ስም አሁን ኢላማ የሚያደርጉት ሰዎች እናመልካለን የሚሉት የሃይማኖት መንገድ አለ ማለት ነዉ? ኦሮሙማስ ምንድነዉ? ከምድራዊነት ወደ ሰማያዊነት የተሸጋገረ ፅንሰ-ሀሳብ ነዉ? ወይስ ይህ ሁሉ አጀንዳ መፍጠሪያ ነዉ?

ኦርቶዶክሳዉያን ነገሮችን ሁሉ እንመረምር ዘንድ ግድ የሚለን ጊዜ ላይ ነን!

https://fb.watch/gqowKPX28C/

Filed in: Amharic