>

"የህወሃትና የኦነግ ብልፅግና አመራሮች አማራን ለመቀራቀት ቢላና ሹካ ይዘው በአንድ ጠረቤዛ የተቀመጡ ናቸው...!" (መስከረም አበራ)

“የህወሃትና የኦነግ ብልፅግና አመራሮች አማራን ለመቀራቀት ቢላና ሹካ ይዘው በአንድ ጠረቤዛ የተቀመጡ ናቸው…!”

መስከረም አበራ


[አማራ በዚህ ድርድር ካልተወከለ “መዋጋቱን ተዋግተሃል፣ መሞቱንም ሞተሃል፤ አሸንፈሃልም። ነገር ግን የፖለቲካ ስራ መስራት አቅቶህ በድርድር ላይ መወከል አልቻልክም” በሚል ነው በታሪክ የሚመዘገበው።]

*… ብልፅግና እኮ ቤተ መንግስት የገባ ኦነግ ነው። ታዲያ እንዴት ሆኖ ነው የአማራ ጥቅም በኦነግ በኩል የሚከበረው?

በዚህ ድርድር የአማራ ተወካይ ይኑር ስንል፣ በድርድሩ የአማራ ችግር በሙሉ ይፈታል እያልን አይደለም። ይሄም የአማራ ህዝብ ችግር በዋናነት የሚመነጨው ከሀሰት ትርክት እና ከህገ መንግስት ስለሆነ ነው።

ነገር ግን በድርድሩ አማራ መወከሉ ሁለት ችግሮችን ይፈታል።

አንዱ አማራ መሪ የለውም የሚለውን የህወሃትንና የኦነግን ትርክት በመስበር፣ የአማራ መሪና ተደራዳሪ ይፈጥራል። ሁለተኛው ህወሃት ባለ ጊዜ በነበረበት ሰዓት በጉልበት የወሰደበትን የወልቃይትንና የራያን ጉዳይ ፊት ለፊት ተከራክሮ ለማስመለስ ይጠቅመዋል። ለዚህም ነው የአማራ ህዝብ በኦነግ ብልፅግና እና በህወሃት ተደራዳሪዎች አያተርፍም የምንለው።

የህወሃት እና የኦነግ ብልፅግና አመራሮች አማራን ለመቀራቀት ቢላዋ እና ሹካ ይዘው የተቀመጡ ናቸው። አንዳንድ አውቆ አበድ አማሮች ደግሞ አማራ በብልፅግና በኩል እንደተወከለ ቀድፍረት ሲናገሩ እሰማለሁ። ብልፅግና እኮ ቤተ መንግስት የገባ ኦነግ ነው። ታዲያ እንዴት ሆኖ ነው የአማራ ጥቅም በኦነግ በኩል የሚከበረው?

አሁን እየተባለ ያለው አማራ መዋጋቱን ተዋግተሃል፣ መሞቱንም ሞተሃል። አሸንፈሃልም። ነገር ግን የፖለቲካ ስራ መስራት አቅቶህ በድርድር ላይ መወከል አልቻልክም ነው እየተባለ ያለው።

Filed in: Amharic