” ይድረስ ፍትሕ አለ ለምትሉ ባለሥልጣናት እና ጋዜጠኞች እንዲሁም ዜጎች !! ”
…ሦስት ህፃናት ልጆቼ ታግተውብኛል...
በይድነቃቸው ከበደ
እድሜያቸው በ30ዎች መጀመሪያ ላይ አካባቢ የሚገኙ በአንድ የውሃ ፋብሪካ እና በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ ግለሰብ ቦርድ ብለው ባቋቋሙት እና ቦርዱ ተጠሪነቱ ለማን እንደሆነ ሚስጥር በሆነ በግል ንግድ ስም ተመዝግበው የሚገኙ ድርጅቶች ውስጥ ለአጭር ጊዜ ማለትም ከሁለት ወር ባልበለጠ ጊዜ አባል እና በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ባልደረባ ተደርጌ በቆየሁባቸው ጊዜያት ፤
እጅግ አሳፋሪ እና አስነዋሪ ከፍተኛ የማጭበርበር ድርጊት ብሎም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝግቦ በሚገኘው ኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ቢሮን በማጭበርበር እንዲሁም የመንግስት ተሿሚዎችን መንግስት ደሞዝ እየከፈላቸው ያሉን ለግል ድርጅታቸው ደርበው በደሞዝ በመቅጠር ከቀረጥ እና ታክስ ጋር በተያያዘ ከፌደራል ገቢዎች ግብር እና ታክስ ስወራ በተጨማሪ በወንድሞቻቸው ሰም የባንክ ሂሣብ በመክፈት የፋብሪካ የሽያጭ ገንዘብ ማሽሽ …….ወ.ዘ.ተ ፤
በዚህ ጽሁፍ ተገልፆ የማያልቅ ጉድ በተጨባጭ በማየቴ እና መረጃ በማግኘቴ የሀገራችን ህግ ለምን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ግለሰቦች በዚህ የኑሮ ውድነት ከሚንገላቱ መንግስት ከእንደዚህ አይነት በቢልየን ከሚያንቀሳቅሱት እና የህዝብ እና የመንግሥትን ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ ግለሰቦችን የሚያጭበረብሩትን ገቢ አይሰበስብም አንደ ማሣያም ይሆናል በሚል ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ፣ ለገቢዎች ሚኒስቴር ፣ ለጉምሩክ ኮሚሽን ፣ እንዲሁም ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አመለከትኩ ጥቆማም አቀረብኩ ።
በመሆነም ይህንን ጥቆማ በማቅረቤ እና በገቢዎች ሚ/ር ሰሜን ምዕራብ አ/አ ቅርንጫፍ ተሽከርካሪ በዕዳ ምክንያት በቁጥጥር ስር ስለዋለባቸው ብቻ ከ ሦስት ከተሞች ፖሊስ ፍጹም የሀሰት ክስ በመፈብረክ ከህግ ውጭ የማሠሪያ እና የማደኛ ወረቀት ማውጣታቸው ሳያንስ አንድ ህገወጥ የፖሊስ አባል የቡድን አባል የሆነበት የደብዳቢ እና የነፍሰ-ገዳይ ቅጥር በአንድ የሀሰት ኢንጂነር በሚል በጋዜጣ ባለቤት በደብዳቤ ብቻ ማዕረግ ያገኘ ግለሰብ ከባለሀብቱ ጋር በመቀናጀት ፤
ለአስደብዳቢ እና ለአስገዳይ ቡድን ፎቶዬ እንዲበተን ከመደረጉም በላይ ከታች በምስሉ የምትመለከቷቸውን ሦስት ህፃናት ልጆቼን ከተፋታን የቀድሞ ባለቤቴን በመጠቀም ሙሉ ለልጆቼ ማሣደጊያ የተውኩትን ንብረቴን እንዲሁም ካልሲ እና ጫማ እንዃን ሣያስቀሩ የመኖሪያ አካባቢ ሰውሁሉ በተሰበሰበበት በውሃ ፋብሪካው ኮንቴነር የጭነት ተሽከርካሪ ጭነው ከሦስት ህፃናት ልጆቼ ጋር ቡራዩ በሚገኘው የውሃ ፋብሪካው ባለቤት በሚስቱ ስም በሚገኝ ቪላ ልጆቼ አባታችንን እያሉ ከጠዋት ማታ እያለቀሱ ታግተው ይገኛሉ ።
በመሆነም ይህን ከዚህ በላይ የጠቀስዃቸውን እና ተጨማሪ የቪዲዮ ቅጂ ፣ የድምጽ ቅጂ ፣ የጽሁፍ ፣ የሰነድ እና የሰው ማስረጃ ከበቂ በላይ ያለኝ በመሆኑ ለማንኩበት እና ስለእውነት በሀገራችን ህግ እና ስርአት እንከበር እሰራለሁ ወይም እየሰራሁ ነኝ የሚል ማንኛውም አካል የሀይማኖት አባቶችን እና ተቁዋማትን ጨምሮ ዳኝነታችሁን እጅግ በከበረ ተማጽኖ አለምናለሁ ።
ቴዎድሮስ
ሞባይል 0911-20 02 50