የጦርነትም የሰላምም ዕዳ ከፋዮች ሆነን እስከመቼ
ቴዎድሮስ ሀይለማርያም
1. በተደጋጋሚ ተክደናል
ሆድ ይፍጀው ብለን ትተነው እንጂ ብልፅግና ባለፉት ሶስት የትግራይ ወረራዎች ወቅት በተደጋጋሚ ያለሀፍረት ክዶናል። በጦርነቱ ሂደት በህልውና ዘመቻው የተሰለፈውን ኃይላችንን በግንባርም ከጀርባውም እያሴረ ፣ በሰሜን ስንፋለም በደቡብ ወገናችንን እያስጨፈጨፈ የጅብ ወዳጅ ሆኖብናል። ጦርነቱ በአስተማማኝ ድል እንዳይቋጭ በማሴር የህዝባችንን መስዋዕትነት ከንቱ አድርጎብናል።
2. ከምር ተንቀናል ወያኔ/ትህነግ በተፈጥሮውም ፣ በርዕዮቱም ፣ በግብሩም የአማራ ደማዊ ጠላት ነው፡፡ ሆኖም የብልፅግናን ያክል ምራቁን የተፋብን የለም። መሪዎቻችንን ፣ ጀግኖቻችንን ፣ አንቂዎቻችንን እየገደለና እያጋዘ ፣ ተቋማቶቻችንን በምንደኞች እያሰረገና እያፈረሰ ፣ ህዝባችንን እየከፋፈለና እያባላ እግር ተወርች አስሮናል። የትግሬ ወራሪ ሲዳከም እየደገፈ ፣ ኦነግ/ሸኔን በገፍ እያሰለጠነና እያስታጠቀ እረፍት ነስቶናል።
3. አሁንም ከጀርባ ተወግተናል የሰላም ድርድሩ አያገባችሁም ፣ ከልቅሶ በላይ ምንም አታመጡም ተብለናል፡፡ ሰላሳ ዓመት በፈረቃ ሲያጠቁን የነበሩት አማራ ጠሎች እየተደራደሩብን ፣ የወገኖቻችን እንባና ደም ሳይደርቅ በገሀድ እንደገና እየተቃቀፉብን ነው። ህዝባችን የጦርነትም የሰላምም ብቸኛው ዕዳ ከፋይ እንዲሆን ተፈርዶበታል። በምንም መንገድ እርቃናችንን ልናለባብሰው አንችልም ። ዝምታውን ሰብረን እንደ ህዝብ አስቸኳይ መፍትሔ መፈለግ አለብን።